ርዕሰ መስተዳድሩ “ከፋፋይ አሰራርን በመዘርጋት የገዛ ፓርቲዉንና የፌደራል መንግስት የማደናገር” ተግባራቸዉን አጠናክረዉ መቀጠሉ ተገልጿል።

“በባለፉት አምስት ዓመታት በሀገራችን የተመዘገበዉ ዉጤቶች እንደሚያመለክተዉ ሀገር መሪ እንደሚፈልግ፤ መሪዉ ደግሞ ሀገርና ህዝብን ከአድማስ ባሻገር በከፍታ እይታ ባልተለመደ መንገድ ይመራል፤ ያሻግራል፤ ለሀገርና ለህዝብ ብልፅግና ይተጋል፤ ባልተለመደ መንገድ፣ ባልተሞከረ አድማስ ይጓዛል፣ ይመራል” በሚል የለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አስተባባሪዎች በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጿል።
“በተቃራኒዉ ደግሞ የክልላችን ርዕሰ መስተዳድር አምኖ የሾመዉን የፓርቲዉን መሰረታዊ ዕሳቤዎችን ባፈነገጠ መልኩ ከፋፋይ አሰራርን በሚዲያ በመቀባት ፓርቲዉንና የፌደራል መንግስት የማደናገርና የማታለል ተግባራቸዉን አጠናክረዉ ቀጥሏል” ሲሉ ከሷል።
እነኚህ ከፍተኛ የብልጽግና ፓርቲ አመራር ደረጃ የሚገኙ የለውጥ አቀንቃኝ አስተባባሪዎች “የሆነ ሆኖ የሚንከተለዉ የብልፅግና ፓርቲ መርህና እዉነተኛ የአቶ ጥላሁን ከበደ ተግባራት ንፅፅር በትንሹ እንደሚከተለዉ መመልከት ይቻላል” በሚል አስረድቷል።
“የብልፅግና ፓርቲ መርህ👇
-መደመር
-ይቅርታ
-ጥላቻን ወደ ፍቅር፣
-አግላይነትን በአካታችነት
-መገፋፋትን ወደ ወንድማማችነት
-መለያው እውነት፣ እውቀት፤ ጥበብ
አቃፊነት
-ኅብረ ብሔራዊ አንድነት
-ዕዳን ወደ ሚንዳ
-መተባበር
ቢሆንም የአቶ ጥላሁን ከበደ ተግባር በተቃራኒው 👇
-በመከፋፈል፣
-ቅመኝነት
-ከፍቅር ወደ ጥላቻ
-ከአካታችነት ወደ አግላይነት እሳቤ
-ወንድማማችነትን ወደ መገፋፋት
-መለያዉ ሰሬኝነት፤ አሉባልተኝነት፤ ፍረጃ
-ገፊነት እና ቆርጦ መጣል
-ለአንድ ብሄር ወይም አካባብ
-ሚንዳን ወደ ዕዳ
-ቡድንተኝነት ወይም መተርተር ነው” ሲሉ ገልጿቸዋል።
በመጨረሻም “ከሾመዉ ብልፅግና ፓርቲ የበላይ ሆኖ በፓርቲዉ ዕሳቤ ሳይሆን በራሱ ስሜት ብቻ በድፍረት ክልሉን እየገዛ የሚገኝ ታርካዊ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር” በሚል በመግለፅ በቅርቡ መንግስት በኢፍትሐዊነት አድሏዊ አሰራር ምክንያት ክልል ወደ ባሰ ቀውስ እንዳይገባ ማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ የጀመረውን የቅድመ ምርመራ ሁኔታ ከጉዳዩ አሳሳቢነት አንፃር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።