“ለገዥዎቻቸዉ ሎሌ ለወከሉት ህዝብ ገዥ የሆኑ የብሄሩ የፌደራል አመራሮች በቅርቡ የስንብት ደማቅ የክብር ሽልማት ተሰጧቸው ቢሆንም ከዎላይታ ዞን ፓለቲካ ጠልቃ ገብነት እንዲወጡ” ይደረጋል !?


ከለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አስተባባሪዎች በአከባቢያዊ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የሚከተለውን ዝርዝር ማብራሪያ ልኳል።
“የዎላይታ ብሔረሰብ ለመብቱና ለክብሩ እንዲሁም ለሁለንተናዊ ብልፅግና ዘመናትን የተሻገረ ተጋድሎ እያደረገ ይገኛል፡፡ ባህልንና ታሪክን የማሳደግ፣ ሀገራዊ ሀብትን እና ፖለቲካዊ ዉክልናን በፍትሐዊነት የማግኘት እና ራስን በራስ ማስተዳደር ዋናዉን የህዝብ ጉልበት ከአካባቢዉ የተፈጥሮ ሐብት ጋር አቀናጅቶ በመምራት የህዝቡን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ሥራ አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ከሁሉም በላይ ካለበት የመሬት ጥበትና የአካባቢዉ ሐብት ሊሸከም ባለመቻሉ ወደ መላዉ አገሪቱ ያለማቋረጥ በመፍለስ ላይ ያሉ ታዳጊዎች እና ወጣቶች ጉዳይ አሳሳብ ደረጃ ላይ ከደረሰ ሰነባብቷል፡፡
ይሄ ዉስብስብ የዞኑ ሁኔታ በተለያዩ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ በተላይም የአካባቢዉ ተወላጆች በጋራ በመሰባሰብ አንዳች ፍቱን መፍትሄ የሚሆን ሀሳብ ማመንጨት የሚጠበቅ ዋና ተግባር ነበር፡፡
በተቃራኒዉ አቶ ጥላሁን ከበደ እና አቶ ዓለማየሁ ባዉዲ በተጠነሰሰዉ ሴራ አመራሩ ከህዝቡ ሰቆቃ በላይ የግሉ ስልጣን አሰክሮ እርስ በርስ መጠፋፋት ፖለቲካ ላይ በማተኮሩ ከመቼዉም ጊዜ በላይ የህዝቡ ህልዉና አደጋ ላይ ወድቋል፡፡
የዚህ ፅሁፍ ዋና ዓላማ ግለሰቦችን ለማጥላላት ሳይሆን ይሄን ተግባር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የፈፀሙ አካላት ራሳቸዉን ፈትሸዉ ወደ እዉነተኛና ህዝብን ማዕከል ለሚያደርግ አስተሳሰብ እንድመለሱ ስሆን በተጨማርም ብዙም መረጃ ያላገኙ ወጣቶች በጭፍን ከመደገፍና ከመቃወም በመዉጣት በትክክለኛ መረጃ ላይ መሰረት በማድረግ ወቅቱን የሚመጥን ትግል እንድያካህዱ ታስቦ ነዉ፡፡
የዎላይታ ፖለቲካ ስብራት የገጠመዉ ከ34 ዓመታት በላይ በተለያዩ የሥልጣን ኮርቻ ላይ የቆዩ እና በዕድሜ ሸምገል ካሉ ከዞኑ ተወላጅ አመራሮች የፖለቲካ በላይነት በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስተር በሆኑት በክቡር በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እጅ ስወድቅ ነበር፡፡
የዎላይታ ዞን ሁለተኛ አስተዳዳሪ የነበሩትና በዎላይታ ተወዳጅ የነበሩት አቶ ፍሬዉ አልታየ ከፍ ያለ እይታ ያላቸዉ በመሆኑ ተሹመዉ ብዙ ሳይቆዩ የዞኑን ገጽታ ከፍ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎችን በማቀድ ወደ ተግባር ማስገባት ችለዋል፡፡
ለአብነትም በልማት የዎላይታ ጉተራ አዳራሽ ያስጀመረ ስሆን ከሁሉም በላይ ከሲዳማ ጋር የነበረዉን የድንበር ግጭት በመፍታት የዎላይታ ህዝብ እንዳይደፈር የተወጣዉ ጀግንነት መቼም ከዎላይታ ህዝብ የማይረሳ ተግባር ነዉ፡፡ ብሆንም በፌደራል ከሚገኙ ከብሄሩ አመራሮች በተከታታይ ጣልቃ-ገብነት ምክንያት አቅሙን አሟጦ እንዳይጠቀም አድርጎታል፡፡
ከእሳቸዉ ህልፈት በኋላ በፖለቲካ በብቃቱና በደፋርነቱ የሚታወቁ አቶ አማኑኤል ኦቶሮ የዞኑ አስተዳዳር ሆኖ ተሾሙ፡፡ እሳቸዉም የተጀመረዉን የጉተራ አዳራሽ ግንባታዉን የማጠናከር፤ የዎላይታ ብሄር ዘመን መለወጫ የሆነዉን የግፋታ ፕሮጀክት በመቅረፅ ወደ ተግባር እንድገባ የማድረግ፤ የዎላይታ ሶዶ ከተማ 28 ኪሜ ዉስጥ ለዉስጥ የአስፋልት ሥራ የማሰራት፤ የዎላይታ ዞን አስተዳደር ባለ 4ት ወለል ግዙፍ ህንጻ የማሰራት፤ በዞኑ ከመንደርተኝነት የተላቀቀ የአመራር ሥርዓት እንድኖር አመራሮች ከትዉልድ ወረዳ ዉጭ የመመደብና በፖለቲካ ብቃታቸዉ በተለያዩ መድረኮች የዎላይታ ስም ከፍ ያደረጉ አመራሮች ስብስብ እንድኖር በማድረግ የህዝቡ ክብርና ጥቅም ከመቼዉም ጊዜ በላይ ከፍ ያደረጉ መሪ ነበሩ፡፡
እሳቸዉ የዎላይታ የልማት አርበኛ እና የፖለቲካ መሀንድስ የነበሩ ግን በተግባራቸዉ ልክ ዕዉቅና ያላገኙ አስተዳዳሪ ነበሩ፡፡ ምንም እንኳን ተግባራቸዉ ለዎላይታ ህዝብ ከፍተኛ ጠቀመታ የነበረ ብሆንም አድስ አበባ ተቀምጦ እንደራሳቸዉ እርሻ ማሳ ለሚመለከቱ ሹመኞች ስላልተዋጠላቸዉ አባረሩት፡፡
ከአቶ አማኑኤል ኦቶሮ መነሳት በኋላ የዎላይታ ፖለቲካ የቁልቁለት ጉዞ ቀጥሎ እርስ በርስ መጠፋፋት ተፋፉሞ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ከጨወታዉ በማዉጣት በአምባሳደር ተሾመ ቶጋ፤ በአቶ ተክለወልድ አጥናፉ እና በአቶ ገብረመስቀል ጫላ የበላይነት የሚመራ የፖለቲካ ጨወታ ተጀመረ፡፡
የእነዚህ የተከበሩ ሽማግለዎች ፍላጎት ደግሞ የህዝብን አቅም ተጠቅሞ የህዝቡን ችግር መፍታት ሳይሆን ለእነሱ እና ለቤተሰቦቻቸዉ የሚያገለግል ሎሌ አአመራር መሾምና ማዘዝ ነዉ፡፡ በመሆኑም ዎላይታ አካባቢ ወደ ስልጣን መምጣትም ሆነ መነሳት የሚቻለዉ በፓርቲ አሰራር ሳይሆን በእነዚህ ቡድኖች በጎ-ፍቃድ ሆኗል፡፡ ስለሆነም ወደ ስልጣን ለመምጣትም ሆነ ለመቆየት ብቸኛዉ መንገድ ለእነዚህ ቡድኖች የመላላክ እድል ማግኘት ነዉ፡፡
ህዘብን ማዕከል አድርጎ ከፍ ባለ ዕይታ ልሰራ የሚችል ወጣት አመራር በሰበብ አስባቡ ማባረር፤ ማሳደድና ማሳሰር ዘዉትር ተግባር ሆነዋል፡፡ የፌደራል መንግስትም ለፌደራል ሆነ ለክልል የብሄሩ ተወካይ አስተያየት ስጠየቅ የሚጠቁሙት የራሳቸዉን ተላላክዎች በመሆኑ ስለዎላይታ ህዝብ ክብርና ፍትሀዊ ተጠቃሚነት አጀንዳ የሚታገል አመራር አጥተናል፡፡
በሙያዉ ተወዳድሮ እንደገባ ባለሙያ ቢሮ መግባትና መዉጣት የብሄሩ ዉክልና አልፋና ኦመጋ ያደረገ አመራር ስብስብ ተፈጥሯል፡፡ ከ200 ሺህ በላይ ወጣት ሥራአጥ፤ በየቀኑ የሚደረገዉ ጅምላ እስር፤ በየቀኑ በመዋጮ የሚሰቃየዉ ህዝብ፤ በፍተህ እጦት በየቢሮዉ ደጅ የሚዞረዉ ባለጉዳይ፤ ደመወዝ በወቅቱ የማያገኝ መንግስት ሠራተኛ፤ ትምህርት የማይማር ዜጋ፤ መድህኒት የለሌዉ ሀክም ቤት፤ በወባ ወረርሽኝ እየተቀጠፈ የሚገኘዉ ዜጋ፤ የግብርና ባለሙያ ድጋፍ የማያገኘዉ አርሶ አደር… ወዘተ አጀንዳ አይደለም፡፡
በ3ት ቡድን ተከፋፍለዉ ዞኑን የሚመሩ አስተባባሪ ኮሚቴ አባለት ዋና ተግባራቸዉ ለአርባምንጭ ስታድየም እና ለፓርቲዉ ህንፃ ድጋፍ መዋጮ መሰብሰብ፤ በአርባምንጭና በጅንካ ከተማ ኮርዴር ልማት ፎቶ በመነሳት በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨት ሆኗል፡፡
እነዝህ የግል ስልጣናቸዉ ከወከሉት ከዎላይታ ጥቅምና ክብር የበላይ የሆነባቸዉ በዎላይታ ህዝብ የሚነግዱ የብሄሩ ጋንግርን ናቸዉ፡፡ ሰሞኑን በክልሉ አድስ ሪፎርም ይካሄዳል በሚል ቅዤት በአስተባባሪ ኮሚቴ ለማስገባት አቶ ተክለወልድ አጥናፉ ቡድን እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡
ቁም ነገሩ ግን በያዙት ስልጣን አማካኝነት የፈቱት የትኛዉ የዎላይታ ችግር ነዉ? በየቀኑ ዎላይታን በወረዳና በከተማ በማከፋፈል አንድነቱን በመሸርሸር አቅም ብስ በማድረጉ ምን ይጠቅማል ? የዎላይታ ወጣት አመራሮችን በማሳደድ፤ ከሃላፊነት ከማስነሳትና ከማሳሰር ዉጪ ለህዝቡ ምን ፈየደ?
የዎላይታ ህዝብ ሰቆቃ አልፋና ኦሜጋ አድስ አበባ ለዘመናት በህዝብ ስም የተቀመጡ ሲሆን ህዝቡ እንደ ህዝብ እፎይታ የሚያገኘዉ የአድስ አበባዉ የብሄሩ ፖለቲከኞች እጃቸዉ ስያነሱ ብቻ ነዉ፡፡ ይሄ ልሆን የሚችለዉ የብልፅግና ፓርቲ እነዚህን ግለሰቦች አደብ ስያስገዛና ህዝቡ ደግሞ የስልጣኑ ባለቤት በመሆን ብቻ እንደሆነ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡
በመሆኑም ህዝቡ ህልዉናዉን የማስጠበቅና አንድነቱን የማፅናት ጉዳይ ጊዜ የማይሰጠዉ አንገብጋቢ በመሆኑ ለማይቀረዉ ትግል መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡ ይህንን ፍፁም ሰላማዊ ትግል የሚያስተባብሩ አካላት በቅርቡ መርሃ-ግብሩን ይፋ ያደርጋሉ፡፡”

ማሳሰቢያ- ማብራሪያው ከለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አስተባባሪዎች በአከባቢያዊ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የተላከ መልዕክት ነው።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏