የዎላይታ ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል የካንሰር ምርመራ አገልግሎት በይፋ መጀመሩን አስታወቀ።
ሆስፒታሉ “በቅርቡ የፓቶሎጂ ላቦራቶሪ / ስነ-ደዌ ላቦራቶሪ / የካንሰር ምርመራ አገልግሎት በቅርቡ እንጀምራለን ብለን ባሳወቅነው መሠረት በይፋ መጀመራችንን ለማሳወቅ እንወዳለን” በሚል በዛሬው ዕለት ገልጿል።

በተጨማሪም “ከሌሎች የሕክምና ተቋማት ናሙናዎችን ተቀብለን የምሠራ ሲሆን፤ ወደ ሆፒታላችን ለፓቶሎጂ ምርመራ ናሙናዎችን ስትልኩ ከታች በተቀመጠው ፖሊሲ መስፈረት መሠረት አሟልታችሁ እንድትልኩ ለማሳሰብ እንወዳለን” ብሏል።


“ከተጠቀሰው ፖሊሲ ውጪ የሚመጡ መሥፈርታችንን የማያሟሉ ናሙናዎች ተቀባይነት ስለማይኖራቸው ተቋማት ይህንን ከግንዛቤ እንድታስገቡ በትህትና እንገልጻለን” ስል ሆስፒታሉ አስረድቷል።
“ይህንን የምናደርገው ተገልጋዮችን ከ አላስፈላጊ የምርመራ ወጪ እና እንግልት ለማዳን እንዲሁም የላቀ የህክምና አገልግሎትን በተሟላ ሁኔታ ለመስጠት ያስችለን ዘንድ ነው” በሚል ምክንያት አስቀምጧል።
የዎላይታ ሶዶ ክርስቲያን አጠቃላይ ሆስፒታል ከተለያዩ ሀገራትና ሀገር ውስጥ የተሰበሰቡ እውቅ የጤና ባለሙያዎች በሚሰጠው ህክምና አገልግሎቶች ከአፍሪካ ከሚገኙ አስር ሆስፒታሎች መካከል አንዱ ሲሆን በዛሬው ዕለት የተጀመረው የካንሰር ህክምና አገልግሎት መስጠት መጀመሩ በሀገሪቱ ጤና አገልግሎት ዘርፍ የራሱን ሚና እንደጫወት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከሆስፒታሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏