1000029570

የዎላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ በዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ላይ የሀሰት ዘመቻ ማስከፈቱ ተገልጿል።

በዞኑ ፓርቲ ፅህፈት ቤት ይመራል የተባለው ይህ ዘመቻ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በተከታታይ በአከባቢው በተጨባጭ መረጃ እና ማስረጃ በማስደገፍ በሚያወጣቸው ዘገባዎች ምክንያት ያጣውን ህዝባዊ አመኔታ ለመመለስ ያለመ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

በአሁኑ ወቅት በአከባቢው ከፌደራል በተለይም በክልሉ መንግሥት በኩል በግልፅ እየተስተዋለ የሚገኘውን ኢፍትሐዊ አሰራር እና ብልሹ አሰራሮችን በተመለከተ እያገለጥን ያለነውን የሚዲያ ስራ በበጎ ተመልክቶ ማስተካከል ሲገባቸው በተቃራኒው በዞኑ የሚገኙ ሁሉም መዋቅር የብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ ዘርፍ አመራሮችንና ባለሙያዎችን በማሰማራት የጥላቻ ዘመቻ መጀመራቸውን ተገንዝበናል።

ከዋናው ላኪዎች ተልዕኮ የተቀበለው የዎላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ዘውዱ ሳሙኤል በተባለ ግለሰብ ቀጥታ ትዕዛዝ ሰጥቶ በዞኑ ሁሉም መዋቅር የሚገኙ የፓርቲ ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊዎች አማካይነት ፅሁፉ ተዘጋጅቶ ከ1 ሺህ በላይ የውሸት ፌስቡክ አካውንት በመጠቀም እንዲያሰራጩት በቴሌግራም እና በዋትስአፕ ግሩፕ ፈጥሮ በጋራ በተደራጀ ሁኔታ ዘመቻ መጀመራቸውን ተጨባጭ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ይሄው በአሳፋሪ ሁኔታ ትልቁን የህዝብ፣ የመንግሥት እና የፓርቲውን ኃላፊነት ወደጎን በመተው በአከባቢው ላይ ተጨባጭ የሚታዩ ክፍተቶችንና የህዝብ ፍላጎት መሠረት በማድረግ ወደ ህዝብ እያደረስን የምንገኘውን እንደ መልካም አጋጣሚ ወይንም እንደ ግብዓት በመጠቀም ማስተካከል ሲገባቸው በመንግሥት በጀት የሀሰት ፌስቡክ አካውንት በማስከፈት ዘመቻ ጀምሯል።

ከዘመቻው መካከል “የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ባለቤት ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ በስደት በሚኖርበት ሀገር ወንጀል ሰርቶ አምልጦ በፖሊስ እየተፈለገ ነው፣ ወደ ስደት ሲወጣ በኢትዮጵያ የሰው ምስት አስረግዘው ኮብልሏል፣ ባለበት ሀገር በማበድ መንገድ ወጥቷል፣ ከአሸባሪዎች ጋር እየሰራ ነው” እንዲሁም የተለያዩ ለሚዲያ የማይመጥኑ የስም ማጥፋት እና ለህዝብ ሁለንተናዊ ለውጥ የሚደረግ የሚዲያ ስራ እንዳይሰራ ለማሸማቀቅ ሙከራ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ከተለያዩ የሀሰት ፌስቡክ ገፅ ከተፃፉ ፅሁፍ ለማረጋገጥ ችለናል።

ከሁለት ዓመት ጀምሮ በሚዲያ፦ በአከባቢው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ማንሳትና መጠየቅ፣ የመንግስት አሰራር ክፍተቶችን መናገርና መተቸት “እንደ ጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ ማሰራጨት ህዝብን በመንግስት ላይ ማነሳሳት በሚል” በፀጥታ መዋቅርና ፍርድ ቤቶች ላይ ጫና በማድረግ ከህግ አካሄድ ውጪ በተደጋጋሚ ለእስርና ለእንግልት፣ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲሁም ከየትኛውም ተቋም ድጋፍና ለሚዲያ አገልግሎት ከዞንና ክልል መረጃ እንዳይሰጥ መከልከሉን ተከትሎ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከኢትዮጲያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የሚዲያ ስራ በሕጋዊነት ለመስራት የሚያስችል ፈቃድ ያለው ቢሆንም በጫና ዋና መቀመጫ የሆነው ዎላይታ ሶዶ ቢሮ ዘግቶ መደበኛ ስራውን ከስደት ሀገር ሆኖ እየሰራ እንደሆነ ይታወቃል።

በመሆኑም በአከባቢው ሆኖ ሚዲያው በነፃነት የመስራትና የፖለቲካ ልዩነት ሀሳብ ያላቸው ግለሰቦችና ተቋማት በህዝብ ጉዳይ ላይ የማወያየት ሆነ ሀሳብ እንዲገልፁ ዘገባ የመስራት ሁኔታ ዝግ መሆኑንና ጫና መድረሱ ታሳቢ ተደርገው የአከባቢ ጉዳዮችን በሚዲያ በተለያዩ መንገዶች በነፃነት ለመስራት የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት እየሰራን ያለነውን መቋቋም ያልቻለው እና እንደበፊቱ በቀላሉ በማሰር ማስቆም የተሳነው ይሄው ቡድን በአሁኑ ወቅት የከፈተው የውሸት ፌስቡክ ዘመቻ በአላማችን ፀንተን ይበልጥ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በጥንካሬ እንድንሰራ መልካም ዕድል የሚፈጥር እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ ለማሳወቅ እንወዳለን።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ኤዲቶሪያል ቦርድ

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita