መነሻውን ከዎላይታ ያደረገው ከኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር የኃይል አቅርቦት መጀመሩ ተጠቆመ

ይሄው ለኢትዮጵያ በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ የኢትዮ ታንዛኒያ የኃይል ሽያጭ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ያስችላልም ተብሏል።
የምስራቅ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ሀይዌይ (East Africa Electric Highway) ፕሮጀክት አካል የሆነውና በግቤ 3 ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ከዎላይታ ላሾ ኃይል ማከማቻ ቀጥታ ወደ በኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት መጀመሩን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ፕሮጀክቱ #የኢትዮጵያ፣ የኬንያና የታንዛንያ የሀይል መሰረተ ልማት አካል መሆኑን የጠቆመው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ የተጀመረው የኃይል ማስተላለፍ ሥራ ሙከራ በስኬት መከናወኑን ጠቁሟል።
የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ የሙከራ ኃይል አቅርቦት መጀመሩ የኢትዮ ታንዛኒያ የኃይል ሽያጭ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ያስችላል ተብሏል።
የምስራቅ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ሀይዌይ ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ትስስር በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል መከናወኑን ያወሳው ሚኒስቴሩ የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ክፍል በኬኒያና በታንዛንያ መካካል የተዘረጋው የኃይል አቅርቦት ትስስር መስመር መሆኑን ጠቁሞ ይህ የኤሌክትሪክ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተጠናቆ የሙከራ ኃይል አቅርቦት ጀምሯል ብሏል።
የኃይል ትስስሩ ኢትዮጵያን ያላትን የታዳሽ ኃይል አቅርቦት በማስፋፋት የአረንጓዴ የኤሌክትሪክ ኃይል ግብይትን በቀጠናው እንዲስፋፋ ሚና እንድትጫወት ያስችላል ያለው ሚኒስቴሩ በመጀመሪያዎቹ የግብይት ዘመናት በዓመት ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንድታገኝ ያስችላታል ሲል ገልጿል።
ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ የተዘረጋው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ የኤሌክትሪክ መስመር ባለ 400 ኪሎ ቮልት ኃይል ማስተላለፊያ መሆኑ ተጠቁሟል።
ለፕሮጀክቱ የአለም ባንክ፣ የአፍሪካ ልማት ባንክና የፈረንሳይ የልማት ፋይናንስ ተቋም ድጋፍ ማድረጋቸውን አመላክቷል።
እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ መንግስት አሁን ለታንዛኒያ ከሚሸጠው የኃይል አቅርቦት በተጨማሪ ለኬንያም ከዚሁ በግቤ 3 ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ከዎላይታ ላሾ ኃይል ማከማቻ ቀጥታ በመሸጥ በአመት ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ እያገኘ እንደሆነ ይታወቃል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏