“በዘመናት ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ በህዝቡ ላይ ሴራ እና የግፍ ፍዳ እየፈፀሙ ካሉ ከክልሉ ገዥዎች ጋር የስውር ዉል በመግባት ህዝቡ ድምፅ የሚሆንልኝ የራስ ፓርቲ አለኝ ብሎ ቢጠብቅም ምንም ድምፅ ላለማሰማት የገቡትን የጥቅም ዉል በማክበር ዝምታ መርጠዋል” – ከተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የተዉጣጡ አባላት

በጉዳዩ ዙሪያ ለዎህዴግ፤ ዎብን እና ዎህነን የፖለቲካ ድርጅቶች የተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የተዉጣጡ አባላት አስቸኳይ የትግል ጥሪ አቅርቧል።
ከተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የተውጣጡ አባላት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ያቀረበው የትግል ጥሪ በተመለከተ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዛሬው ዕለት የላኩትን መልዕክት እንደሚከተለው አቅርበናል።
“ሀገር የፖለቲካ ዉጤት ስለሆነ በደንብ የማይሰራ የፖለቲካ ሥርዓት ያለዉ ሀገር እጅግ ለብዙና ለተወሳሰቡ ችግሮችና ለከፍተኛ ቀዉስ ይዳረጋል፡፡
ሁላችንም እንደምንገነዘበዉ የፖለቲካ ግቡ ለምንታገለልት ህዝብ የተሻለ ሁኔታን መፍጠር ነዉ፡፡ የተሻለ የፖለቲካ ሥርዓትን የገነቡ ሀገራት ለዚህ ደረጃ የደረሱት ከራስ ጥቅም በላይ ፖለቲካን ለጋራ ጥቅም ማዋል በቻሉ ፖለቲከኞቻቸዉ ነዉ፡፡
በዎላይታ ዞን የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መስፈርት አሟልቶ የተመዘገቡ ሶስት የተፎካካሪ ፓርቲዎች የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ዎህዴግ)፤ የዎላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ (ዎብን) እና የዎላይታ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ዎህነን) ናቸዉ፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች ከአላማቸዉ አንፃር የዎላይታ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ፤ ፓለቲካዊ እና ህጋዊ መብቶችን በማንም ሰጭነትና ከልካይነት ሳይሆን በህግና አሠራር ብቻ የማስከበር ሁሉ አቀፍ ትግል እንደምያደርጉ ይጠበቃል፡፡
ይሁን እንጅ ድርጅቶችን የሚመሩ ግለሰቦች ዎላይታ ህዝብ ከፓርቲዉ የሚጠብቀዉን ትልቁን ዓላማ በሳተ መንገድ ህዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብት ረገጣ፣ ፖለቲካዊ መብት ረጋጣ፣ የኢኮኖሚ መብት ረገጣ፣ የፍታሃዊነትና እኩል ተጠቃሚነት መብት ረገጣ፣ የመሰማትና የመደመጥ መብት ረገጣ… ወዘተ በዘመናት ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ እየደረሰበት በህዝቡ ላይ ሴራ እና የግፍ ፍዳ እየፈፀሙ ካሉ ከክልሉ ገዥዎች ጋር የስውር ዉል በመግባት ህዝቡ በዚህ ፍዳ ጊዜ ድምፅ የሚሆንልኝ የራስ ፓርቲ አለኝ ብሎ ቢጠብቅም ምንም ድምፅ ላለማሰማት የገባዉን ጥቅም ዉል በማክበር ዝምታ መምረጣቸዉ በጣም የሚያሳዝን ተግባር ነዉ፡፡
ምንም እንኳን የዎላይታ ህዝብ ስምና የትግል ዓርማ ይዞ ያልተደረጁ ግን በየቦታዉ ስለዎላይታ ህዝብ ግፍና ጭቆና የመረራቸዉ ልጆች ባልተደራጀ ሁኔታ የየግላቸዉ መግለጫና የሀሳብ ትግል እያሰሙ ይገኛሉ። ይህ በተበታተነ መልኩ የሚደረግ ትግል ደግሞ ተጨባጭ ዉጤት እንደማያመጣ ግልፅ ነዉ፡፡
ስለሆነም እነዚህ በዎላይታ ስም ተደራጅቶ የዎላይታ ህዝብ ስቃይና መከራ ምንም የማይመስላቸዉ በአሻጥር የዎላይታ አከባቢን በተጠና እና በተደራጀ መንገድ እያሰቃዬና እያጠቃ ካለዉ በአቶ ጥላሁን መራሹ ብልፅግና ፓርቲ ጉርሻ በማግኘት አይቶ እንዳላዬ ሰምቶ እንዳልሰማ ዝምታ የመረጡ የዎላይታ የፖለቲካ ድርጅቶች ከዎላይታ ህዝብ ጋር ካለዉ ፓለቲካዊ ዉል አንፃር ትግሉ በሚፈልገዉ ጊዜና ሁኔታ ትግሉን በተደራጀ መልክ ያለመምራት ታርካዊ ስህተት ነዉ፡፡
በዚህ ሰዓት ዎላይታ ህዝብ ለመብቱና ለህጋዊ ጥቅሙ የሚታገል የራሱ ፓርቲ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የ3ቱም ፓርቲዎች ሥራ አስፈጻሚዎች በጋራ በመሆን የዞኑንና ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ በመገምገም ዎላይታ ህዝብ ላይ የተቃጣዉን ሁሉ አቀፍ ጭቆና ማምከን የሚችል ከጋዜጣዊ መግለጫ የዘለለ አፋጣኝ ወቅታዊና ሰላማዊ የትግል ስትራቴጅ በመቀየስ ህዝቡን ከፊት ሆናችሁ እንድትመሩ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን! የስኬት ተጋሪ፤ በችግር ጊዜ ተወሻቂ ዓይነት የትግል ስልት ልቆም ይገባል!!!
ከተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ከተዉጣጡ አባላት የተላከ የትግል ጥሪ!
ታህሳስ 7፣ 2017 ዓ.ም
ዎላይታ ሶዶ፤ ኢትዮጵያ
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏