በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ የአባላት መዋጮ የባለሥልጣናት ገቢ ምንጭ እየሆነ እንደሆነ ተጠቆመ!

ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደቡብ ኢትዮጵያ የአመራር ብልሽት መገለጫዎች በከበሩ ማዕድናት፤ በኮንትሮባንድ፤ በከተማና በገጠር በኢንቨስትሜንት መሬቶች እንደሆኑ በመረጃ አስደግፈን ለሕዝብ ይፋ ማድረጋችን ይታወቃል።
አሁን ደግሞ ከፓርቲው ውስጥ አዋቅ አባላት በደረሰን መረጃ የአመራሩ ስብዕና ደረጃ ምን ያህል እንደወደቀ ያስረዳናል። ከአባላቱ የመጣውን መረጃ እንደሚከተለው አቅርበናል።
”እኛ የደቡብ ኢትዮጵያ የብልፅግና ፓርቲ አባላት የበለፀገች፣ ኅብረብሔራዊ ማንነቷ የዳበረና አንድነቷ የተጠናከረ ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ ባለን ቁርጠኝነትና ይኽንን ለመተግበር በመደመር አስተሳሰብና በአንድነት ቅኝት በመነሳት ልናያት የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ ለመገንባት የእያንዳንዳችንን ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን በመረዳት የበኩላችንን ሚና ለመጫወት በከፍተኛ ቆራጥነት ተሰባስበን ለመታገል የፓርቲው አባል መሆናችን የሚታወቅ ነው።
ምንም እንኳን አድስ በተደራጀው ክልላችን እኛ አምነን እንታገልለታለን ብለን የገባነው ፓርቲ በተወሰኑ ግለሰቦች የተያዙ ተናጠል ዐቋሞችን የፓርቲው በማስመሰል የሚንቀሳቀስ ብሆንም በፓርቲያችን ተስፋ ሳንቆርጥ የአባልነት ግዴታችን እየተወጣን እንገኛለን።
ደቡብ ኢት/ያ ክልል ተብሎ አድስ በተደራጀዉ ክልል ዉስጥ እንደ ክልል የክልሉን ህዝብ አስተባብሮና አንድ አድርጎ ከምንም በላይ በህግና በአሠራር በላይነት ለመምራትና ፍትሃዊ መልካም አስተዳደር የሰፈነበት፣ ለህዝቦች አግላይና ከፋፋይነት ስሜት የማይሰማበት እኩል የሚስተናገዱበት ክልል እንዲሆን አድርጎ ለመምራት በአገራችን ብልፅግና ፓርቲ የተደራጀ የደቡብ ኢትዮጵያ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በክልላችን ተከፍቶ በአጠቃላይ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ የሚደርስ ከተለያዩ ማህበረሰብ የተወጣጣ የፓርቲ አባልነት ተቀብሎ የተቀላቀለ ዜጋ እንዳለ ይታወቃል።
ከዚህ አባላት ቁጥር ዉስጥ 60% ወይም በአሃዝ ሲሰላ ከ670,000 በላይ የአባል ቁጥር ይዞ የሚገኘዉ የዎላይታ ዞን ነው። ይህ ቁጥር በቀድሞ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ጊዜም ከሌሎች ዞኖች ጋር ሲነፃፀር ከዚህ ቁጥር ከፍ ያለ ቁጥር ይዞ በመስመር ላይ ሆኖ የሚታገል ዞን እንደሆነ ተጨባጭ የትግል አመጣጥ ታርክ ይመሰክራል።
በወቅቱ ዴኢህደን የሚባል ድርጅት ይሄን ሰፍ አባላት ቁጥር በመያዝ በመስመር ላይ ሆኖ የሚታገለዉ የወላይታ ህዝብ የተለያዩ በድርጅት ክንፍ የሚመሩ እና ዘዉትር የህዝቡ መልካም አስተዳደር ጥያቄ የሆኑ ጉዳዮችን ከመፍታት ይልቅ ጭፍን ፍረጃ በመምረጡና አባላቱንና የአባል አመራሩን በሴራ መንገድ በአመፃ ግምገማ በምል በቡድን አደረጃጀት እየፈረጀ ከመስመርም እያስወጣ በመሄዱ በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ በቁጥር ከፍተኛ የሆኑ የመንግስት ሠራተኛ አባላትና ሌሎች ማህበረሰብ አባላት ድርጅቱን ጠልቶና ለቆ እንዲወጣ አድርጎታል።
ይሁን እንጅ አሁን ለዉጡ በወለደዉ ብልፅግና ፓርቲ በፓርቲ የተወለዱና ፓርቲዉን በወለዱ ቁርጥ ቀን ልጆች እየተመራ በአፍርካ በቁጥር ከፍተኛ አባላት ያለበት ፓርቲ ሆኖ ሊመጣ ችለዋል።
ይሁን እንጅ የፓርቲዉ ትልቁ ሞጎስና ስኬታማነቱ የመጀመሪያዉ በራሱ በፓርቲ አባላትና አመራር ታማንነት አትርፎ ደጋፍዉንና መላዉ ህዝብን ለልማት፣ ለመልካም አስተዳደር ማስፈን፣ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ፣ ለህግ በላይነት መረጋገጥ፣ ለአብሮነትና ለወንድማማችነት መረጋገጥ፣ የነጠላ ቡድን ትርክትን በማክሰም የወል ትርክት የማስረፅ እንዲሁም ሠላምና ፀጥታ ሥራን በአባሉ ግምባር ቀደምትነት በማከናወን ዘመን የማይሽረዉን ሥራ መስራት የአንድ ፓርቲ ጠንከራ መሠረቱና ህልዉና ነዉ።
በመሆኑም ፓርቲያችን ብልፅግና በአገር ደረጃ ይህን ዉጥን አስቀምጦ የምንቀሳቀስ ቢሆንም አድስ በተደራጀዉና የፓርቲያችን እውነተኛ ዴሞክራሲያዊነት መገለጫ በሆነዉ በደቡብ ኢት/ያ ክልል ከፓርቲዉ ክብርና አስፈላጊነት በላይ አድርጎ ራሳቸዉን በሚቆጥሩ እና በሚንቀሳቀሱ በፓርቲ ማዕከል አመራሮች በተፈፀመዉ ብልሽት ምክንያት የደቡብ ኢት/ያ ክልል ህዝቦች የዘዉትርና የቆዩ የተለያዩ ጥያቄዎችን ይመልሳል የተባለዉ ፓርቲ እጣ ፈንታዉ የደኢህዴን ወቅት አባላት የወሰዱት እረምጃ እጣ ፈንታ ለመሆን ከጫፍ ላይ ደርሷል።
ለዚህ ዋና ማሳያዉ በአሁኑ ሰዓት የየወሩ የአ/አደር አባል፣ የመንግስት ሠራተኛ አባል እና የተማሪ አባላት የሚሰበሰበዉ ሀብት ደረሰኝ የማይሰጥና በየሩብ ዓመቱ ለአባላት ሪፖርት እየቀረበ የማይመራ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በኑሮ ወድነት እየተጠበሰ ለፓርቲ አባልነት ካለዉ ዉግንና ከሌለዉ ኑሮ የሚደረገዉ መዋጮ በተጨባጭ በክልሉ ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች ለብልሹ ሥራና ለብክነት እየተዳረገ እንደሆነ በማስረጃ ተደርሶበታል።
ለማሳያነት ያክል በክልሉ ፓርቲ ጽ/ቤት ለአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ብቻ ከፓርቲው መዋጮ ከተሰበሰበው በጀት በሦስት ወር ዉስጥ አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሰማንያ ሺህ ብር ለአንድ ሆቴል መስተንግዶ ክፍያ መፈፀሙ ክልሉ እዉነት ባለበትነት ባለዉ በፓርቲ አመራር እየተመራ ነዉ ወይ ለሚለዉ ጥያቄ መልስ ያልተገኘለት እንዲሆን አድርጎታል።
አሁንም ለዚህ ሰዉ ከመንግስት በጀት ደግሞ ከአራት ወር በፊት በአራት ሚሊዮን ብር የተገዛና የተሠራ የመኖሪያ ቤት ዕቃ ተሟልቶለት የተከራየለትን ቤት ሙሉ ዕቃዉን ምንም በማይታወቅ መንገድ ጭኖ ከወሰደ በኃላ ሌላ እቃ ከዛ ከፍ ባለ ዋጋ እንዲገዛ እና ሌላ ቤት ተቀይሮ ክራይ እንዲያዝ ትዕዛዝ ማስተላለፍ ይገኝበታል።
በተጨማሪም የፓርቲ አመራሮች በአ/ምንጭ ከተማ በአንድ ሆቴል ብቻ ለሩብ ዓመት ለመስተንግዶ የተጠቀሙበት ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ የሚከፈሉበት ሲታይ ፓርቲዉን ሊያገጥም ያለዉ የሀብት ብክነት ብቻ ሳይሆን የሀብት ሁሉ ምንጭ የሆነዉ አባላት እጥረት ጥሎ መሄድ ሊገጥም እንደምችል በርግጠኝነት የፓርቲው የዉስጥ ተቆርቋርዎች ያስረዳሉ።
አሁን ደግሞ ለፓርቲው ህንፃ ግንባታ በሚል ሌላ የመብያ አጀንዳ በመቅረጽ በአብዘኛው ያለ ደረሰኝ ቀሪ ደግሞ ትክክለኛ ይሁን ፎርጅድ በማይታወቅ ደረሰኝ አባል የሆነም ያልሆነው ህዝባችን በቀን ምድር እየተዘረፈ ይገኛል።
በመሆኑ የዚህ ክልል የህገ ወጥነት ተግባር ግዝፈትና አድራጎት ህጋዊና ለዚህ ህገ ወጥ ሥራ በተፈቀደላቸዉ አካላት የሚከዉን እንዲመስል ያደረገ ብሎም ክልሉ በመንግስት እና በፓርቲ ሥርዓት የመመራት ጉዳይ አላስፈላግ ተደርጎ የተደራጀ ክልል ነዉ አስብሎታል በህዝብ ዘንድ፤ ይሄና ከዚህ እጅግ የከፉ የፓርቲና የመንግስት ህልዉና በክልሉ አሁን የሚደረጉ የአመራር ብልሽቶች ልክ እንዲታሰብ አድርጎታል።
ይሄና የተለያዩ በክልሉ በየተቋሙ ዉስጥ ያሉ ብልሽቶችን የሚያሳዩ ተጨባጭ ሠነድ አስፈላግ ከሆነ የሚለጠፍ ይሆናል። ስናጠቃልል እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ችግሮች በአጋጣም በጥቆማ መረጃ የተገኘባቸው ነው እንጅ ብልሽቱ ከፍ ያለ እንደሆኑ የሚጠበቅ ስሆን ለብልሽቱ መንስኤው የአባላት መዋጮ የገለልተኛ አካላት ኦዲት ሪፖርት በየደረጃው ላለው አባላት እየቀረበ ያለመሆንና ለከፈለንበት ደረሰኝ የማይሰጥ በመሆኑ የግለሰቦች መጫወቻ አድርጎታል።
በመሆኑም ክልሉ ትክክለኛ የብልፅግና ፓርቲ ቁመና እስክይዝ ድረስ የፓርቲ እና ሌሎች መዋጮች መክፈል ለግለሰቦች ቀለብ እንደሆነ ታውቆ ማስተካከያ እንድያደረግ ለብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ጥሪያችንን በአክብሮት እናቀርባለን ”።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏 #Ethiopia #southethiopiaregion