“ርዕሰ መስተዳድሩ በቅዱስ ሲኖዶሱ የተፈቀደው የጎፋና ባስኬቶ ዞኖች ሀገረ ስብከት እንዳይደራጅ አስከልክሏል” በሚል የሀይማኖት አባቶች ከፍተኛ ቅሬታ አቀረቡ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የአቶ ጥላሁን ከበደ የፖለቲካ ሴራና ኃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት እየከፋ መምጣቱንም አባቶቹ ጠቁመዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከአባ አልያስ የጋሞ አከባቢ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር በፈጠሩት የጥቅም ትስስርና ሀይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት በቅዱስ ሲኖዶሱ የተፈቀደው የጎፋና ባስኬቶ ዞኖች ሀገረ ስብከት እንዳይደራጅና ምዕመናን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት ማስከልከሉን የሀይማኖት አባቶች አክለው ተናግረዋል።
“ጠያቂ ያጣው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ሀይማኖታዊ መንግስት ምስረታ ብዙዎችን ለእስራትና ለእንግልት እየዳረገ ነው” ሲሉም ቅሬታ አቅርቧል።


“በከፋፋይነትና ከፋፍሎ በማጋጨት ስልጣን ላይ መቆየት እንደምቻል እንደሚያምኑ የሚገለፅላቸው አቶ ጥላሁን ከበደ በክልሉ ውስጥ የምኖሩ ህዝቦች መካከል ጥላቻን በመዝራት ጥርጣሬና መከፋፈል ከፈጠሩ በኋላ ፊቱን ወደ ኃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት አዙሯል” ሲሉ አንዳንድ የአከባቢው ኦርቶዶክስ ሀይማኖት እምነት አባቶችና ተከታዮች ገልጸዋል።
አቶ ጥላሁን ከበደ በእያንዳንዱ ዞን አጀንዳ በመወርወር ዞኖችን እርስበርስ እና በውስጣቸውም አንድ እንዳይሆኑ ቡድኖችን በማደራጀት ለክልሉ ህዝብ ዕዳ መሆናቸውን በርካቶች እንደሚያውቁ ቀደም ሲል መዘገባችን ይታወቃል።
“በዚህም አላማቸው እንደተሳካ በደስታ ስገልፁ ነበር። አገላለጹን በብልጽግና ፓርቲ ሽፋን አደረጉት እንጅ” ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች።
“በቀጣይ ኃይማኖታዊ ጣልቃ ገብነትን በማስፋፋት ኃይማኖታዊ ግጭትን በመቀስቀስ ክልሉን ለመበተን እንደቁልፍ አጀንዳ ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ይገኛልም” ብሏል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ እምነት የቀድሞ የጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብኬት የጎፋና ባስኬቶ ዞኖች ምዕመናን ባነሱት ጥያቄ መሠረት ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥያቄውን ተቀብሎ በሁለት ሀገረ ስብኬቶች እንዲደራጁ በ2016 ዓ.ም ወስኗል።
“ሆኖም በፎቶ መመልከት እንደምቻለው አቶ ጥላሁን ከበደ ከአባ አልያስ የጋሞ አከባቢ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጋር በፈጠሩት የጥቅም ትስስርና ሀይማኖታዊ ጣልቃ ገብነት በቅዱስ ሲኖዶሱ የተፈቀደው የጎፋና ባስኬቶ ዞኖች ሀገረ ስብከት እንዳይደራጅና ምዕመናን መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት አስከልክሏል” በሚል የሀይማኖት አባቶች ቅሬታ አቅርቧል።
እነዚህ የእምነቱ ተከታዮች ኃይማኖታዊ ጥያቄአቸውን በመያዝ ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ አቤት ለማለት ሲንቀሳቀሱ አቶ ጥላሁን ከበደ ለክልሉ ፖሊስ ቀጥታ ትዕዛዝ በመስጠት ምዕመናን መንገድ ላይ በማገት በበረሃ በረሃብና በውሀ ጥም እንዲቀጡ ማድረጋቸውንም በቅርቡ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መዘገቡ የሚታወስ ነው።
“አቶ ጥላሁን ከበደ ዘርፈብዙ ብልሽቶችን ያለ ከልካይና በማን አለበኝነት የሚፈጽመው ለግል ጥቅምና ለቡድኑ የፖለቲካ ሴራ ስኬት እንጂ ለብዙሀኑ እንዳልሆነ ለማንም ግልጽ ነው” ስሉ በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው ጠቁመዋል።
“በዚህ ግለሰብ ቅጥያጣ ብልሽት ክልሉ ወደ አላስፈላጊ ግጭትና መከራ ሳይገባ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ማበጀት አለበት” በሚልም ጥሪ አቅርበዋል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏 #Ethiopia #southethiopiaregion