ተጠሪነታቸው ለክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑ ተቋማት ርዕሰ መስተዳድሩ በሚገኝበት ከተማ እንዲሆን ህጉ የሚያስገድድ ቢሆንም በህገወጥ መንገድ ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ ቅድመዝግጅት መጠናቁቀ ተገለፀ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢምግሬሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክልሉ መቀመጫ በሆነችው ዎላይታ ሶዶ እንዲከፈት የተቋሙ ማኔጅመንት በመወሰን፣ በኦንላን የዎላይታ ሶዶ ስም ከተመዘገበ በኋላ ከነሃሴ ወር 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ ለመከራየት እንቅስቃሴ ተጀምሮ እነደነበር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል
ነገር ግን በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጫና ተቋሙ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በአርባ ምንጭ ከተማ እንድከፍት ውሳኔ በማስቀየራቸው፣ በአርባ ምንጭ ከተማ የቀድሞ ስታትስቲክስ ግቢን ለኢምግሬሽን ጽ/ቤት እንዲውል ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ እንደሚገኝ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከታማኝ ምንጭ መረጃው ደርሷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ከርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ተጽፎ የወጣው ሰርኩላር ደብዳቤ እንደሚያመላክተው ማንኛውም ዓይነት ስብሰባ፣ ጉባኤ፣ ስልጠና፣ ፎረም፣ ወዘተ ሴክተሩ/ቢሮው ባለበት ከተማ/ማዕከል እንዲደረግ ቀጭን ትዕዛዝ ተላልፏል።
ሰሞኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድሩ እነ ዶ/ር ቀለሙ ደስታን ጨምሮ የተለያዩ ታዋቂ የዎላይታ ተወላጆችን በቢሮአቸው ጠርተው ያናገሩ ሲሆን “በአርባምንጭ ከተማ ልማትና ዕድገት ሕዝባችሁ ለምን ይቀናል፤ የአርባምንጭ ከተማ አመራር በራሳቸው ሀብት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ከጀመሩ በኋላ ድጋፍ ስለጠየቁን የክልሉ መንግስት እየደገፈ ይገኛል፣ ነገር የዎላይታ አመራሮች ምንም ሳይጀምሩና ሳይጠይቁን እንዴት ምን እንርዳቸው?” ማለታቸውን ከተሳታፊዎች መረጃው ደርሶናል።
ተጠሪነታቸው ለክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑ ተቋማት ርዕሰ መስተዳድሩ በሚገኝበት ከተማ መከፈት እንዳለበት በደንቡ የፀደቀ ቢሆንም ሕግን በመጣስ በማንአለብኝነት ወደ ሌላ ከተማ ማዛወር ፍጹም ተገቢነት የሌለው አምባገነነዊ አሠራር ማሳያ እንደሆነ በርካቶች አስተያየት ይሰጣሉ።
ባለፈው ግንቦት ወር 2016 ዓ.ም የኢፌዲሪ ኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መዲና በሆነችው ዎላይታ ሶዶ ከተማ ሥራ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እንደነበር ይታወሳል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መዲናዋ ዎላይታ ሶዶ ከተማ ዓለምአቀፍ አገልግሎቶችን የሚሹ ተገልጋዮች፣ ኢንቨስተሮች፣ ቱርስቶች፣ ባለስልጣናት፣ ዲፕሎማቶች፣ NGOs፣ ወዘተ የሚያዘውትሩባት ከተማ ሆናለችና ICS አገልግሎት መጀመር ፋይዳው የጎላ ይነገራል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏 #Ethiopia #southethiopiaregion