1000030197

በቁጫ የዎላይታ ዲቻ መለያ በመልበስ የጋሞ ሕዝብ ሞራል ነክታችኋል” በሚል በርካቶች እየታሰሩ መሆኑ ተገለፀ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል “የዎላይታ ዲቻ የስፖርት ክለብ መለያ ልብስ ለብሳችኋል፣ የጋሞን ሕዝብ ሞራል ነክታችኋል” በሚል ለጋሞ ሕዝብ መብት እንቆረቆራለን የሚሉ የአርባምንጭ ባለስልጣናት የሚያስተባብሯቸው ቡድኖች በቁጫ ሕዝብ መዋቅሮች ውስጥ በሚደግፉት የስፖርት ክለብ ምክንያት ብቻ የማሰር፣ የመደብደብና ከቤት ንብረት የማፈናቀል ዘመቻ ጀምረዋል” ሲል የቁጫ ህዝብ ደሞክራሲያዊ ፓርቲ አብራርተዋል።

ፓርቲው በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ “በርካታ ወጣቶች ከእነ ማሊያቸው ተይዘው ልብሶቻቸውን አስወልቀው ራቁታቸውን እንዲቀሩ በፖሊስ በማስገደድ የለበሱትን ማሊያዎች ነዳጅ አርከፍክፈው ሰው በተሰባሰበበት የማቃጠል እርምጃ ወስደዋል” ብሏል።

“የአንድ ክለብ ደጋፊ መሆን አለመሆን ግለሰባዊ መብት ነው። የእኔን ክለብ ካልደገፍክ ብሎ ማስገደድ የትም የለለ ነው። ክለብህ ውጤታማ ሲሆን ስፖርት ይጣራል፤ ብዙ ደጋፊም ይኖርሀል። ስፖርት አለምን ባስተሳሰረበት በምንኖርበት ሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን የራሱን ማንነት በታላቁ ቁጫ ህዝብ ቁጫዊ ማንነት ካልጫንኩ በሚለው እና የዛን አከባቢ ገፅታ እያበላሸ የቆየው በሁሉም ዘንድ የሚታወቀው ጎጠኛ ፅንፈኛ ቡድን እያከናወነው ያለው ይህ ተግባር ህገወጥ እና እጅግ አሳፋሪ ነው። ሸፍጡ የህዝቦችን ፖለታካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር ለማቋረጥ ሲሰራ የቆየ ቢሆንም እኛም ስንታገለው እና ስናጋልጠው የቆየነው ጉዳይ ነው” በሚል ጠቁሟል።

“ዋናው ዓላማቸው ግን ከስፖርት ዘለል ያለ መሆኑን ልብ ይሏል። ይኸውም ታላቆቹን የቁጫን እና የዎላይታን ህዝቦች በደም፣ በአጥንት፣ በጀግንነት እና በታላቁ እና ህያው ታሪካቸው ያላቸውን አንድነት ለመበጣጠስ የሚያደረጉት የቆዬ የጥላቻ ዘር ፍሬ በመሆኑ በዜጎች እና በአጎራባች ሕዝቦች ላይ ፀረ-ሰላም አጀንዳዎችን በመፍጠር አከባቢውን የስጋት ቀጠና ለማድረግ የሚደረገውን ሀይ ባይ ያጣውን ፖለቲካዊ ሴራ አጥብቀን እናወግዛለን” ብሏል።

ሰሞኑን በቁጫ ወረዳ የዎላይታ ዲቻ መለያ ለብሳችኋል በሚል ከታሰሩት 72 ወጣቶች ጋር በተያያዘ፤ ለሚዲያ ዘመቻ መረጃ ስታቀብሉ ነበር ያሏቸውን ግለሰቦች ያለ በቂ ምክንያትና ያለ ፍ/ቤት እውቅና፤ በአመራሮቹ ትዕዛዝ መሰረት እየታፈሱ መሆኑን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከአከባቢው ነዋሪዎች አረጋግጧል።

ይህን ተከትሎ ፍርድ ቤት ያለመቅረባቸውና በቤተሰብ እስካሁን ያልተጎበኙ መሆናቸውን ጭምር እየወጡ ባሉ ተጨማሪ መረጃዎች መሰረት ለማረጋገጥ ተችሏል።

የሠላምበር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ጭምር በስራ ገበታ በማስተማር ሂደት ላይ እያሉ ከሚሰሩበት ትምህርት ቤት በተማሪዎች ፊት ተይዘው ወደ ሠላምበር ከተማ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውንም ለማረጋገጥ ችለናል።

ይሄንን በዞኑ በየጊዜው በዞኑ በተደራጀ ሁኔታ የሚፈፀሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ተከትሎ በርካቶች በአከባቢው ሽማግሌ የተባሉ ግለሰቦች ላይ ጥያቄ ማንሳት ጀምሯል።

እነዚህ የጋሞ አባቶች አይደሉም ሚዲያ ጠርቶ በዎላይታ ላይ የጥላቻ መግለጫ ስሰጡ የነበሩት? 300 የሚደረስ ሰው ሸራ በተባለ አከባቢ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት የተጨፈጨፉት ?

ከ400 በላይ ትግራዋይን ምዕራብ አባያ አከባቢ ከታሠሩበት አውጥቶ የረሸነው የጋሞ ወጣትና አባቶች አይደሉም?

ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ለመግባት ለመወጣት የሚሸማቀቁባት (የዲቻ መለያ ለብሰሃል ተብሎ የምታሰርባት) አርባምንጭ ከተማ ላይ እነዚህ አባቶች ምን ሰሩ? ሰላም ስላሳጡ ነው? የሚል ሙግት እያሰሙ ይገኛሉ።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏 #Ethiopia #southethiopiaregion