“ካብኔዎች በሌሎች አከባቢዎች ስብሰባ ወይንም ፕሮጀክት ለመስራት ካቀዱ ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገቡ ይመስላቸዋል” – ጥናት

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአንድ አመት ተኩል እድሜ ከ80% በላይ ክልላዊና ሀገር አቀፋዊ ስብሰባ በአርባምንጭ ከተማ ብቻ ሲካሄድ እንደነበር አንድ ጥናት አመላክቷል።
አዲሱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ6 ማዕከል ተደራጅቶ በ6ቱም ማዕከል የክልሉ ቢሮዎች የሚገኙና የክልሉ አስተዳደርና ፖለቲካ ማዕከል ዎላይታ ሶዶ አድርጎ መደራጀቱ የሚታወቅ ቢሆንም የክልሉ ር/መስተደድር መቀመጫ አርባምንጭ እንደሆነ ሁሉም በአንድ አፍ የሚመሰክሩት ነው ይላል ጥናቱ።
አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ባለው አመራር የተካሄደው ይሄው ጥናት “በክልሉ 6ቱም ማዕከል የተደራጁ የቢሮ ኃላፊዎች በሙሉ በሚባል ደረጃ የክልሉን ፕሬዚዳንት ለማስደሰት በሚል ሁሉንም የክልሉን ካፒታል በጀት የክልሉ ፕሬዚዳንት ለሚፈልጉት ፕሮጀክት በአርባምንጭ ከተማ እንዲለማ ከማድረግ ባለፈ አንድም ከዞኑ ስብሰባ ውጪ በዲላ ክላስተር ተካሄዶ አያውቅም ሆቴሎችም ከዚሁ ስብሰባ ለከተማው በቂ ገቢ እያስገቡ አይደለም ሚዛናዊነቱ የተጠበቀ የስብሰባ ሆነ የበጀት የልማት ተደራሽነት የሌለው ክልል እንደሆነ የዲላ ግብርና ክላስተር 6% ያነሰ ክልላዊ ስብሰባ ማድረጉ ይገነዘባል” ሲል ያረጋግጣል።
“የክልሉ ፖለቲካና አስተዳደር ማዕከል 10% የክልሉ ማህበራዊ ክላስተር ጂንካ 2% የክልሉ ፍትህ ክላስተር ጎፍ ሳውላ ከተማ 1% ኮንሶ ካራት 1% በድምሩ አጠቃላይ 6ቱ ክላስተር 100% የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰረት ያደረጉ ስብሰባዎች ተካሂደዋል” ብሏል።
ጥናቱ እንደሚያረጋግጠው “ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው የክልሉ ር/መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደ ልማቶች ሁሉ ወደ አርባምንጭ ከተማ እንዲሆን ፍላጎት ስላላቸው የክልሉ ካቢኔም ስብሰባው አርባምንጭ ካልሆነ በሌሎች በክልሉ ክላስተር ከተሞች ካደረጉ ከአቶ ጥላሁን ከበደ ጋር ግጭት ውስጥ የሚገቡ ይመስላቸዋል” በሚል እንደሆነ ምክንያት ያብራራል።
“ስብሰባዎች ለምን ፍትሃዊነት የላቸውም ብቻ ሳይሆን አርባምንጭ ከተማ ላይ የተካሄዱ የክልሉ ፍሬ አልባ ስብሰባዎች ከ80% በላይ ናቸው አንድ አመራር በማዕከሉ በሳምንት አንድ ቀን አይገባም ባለጉዳይ ሲመጣ አርባምንጭ ሄዷል ነው የሚባለው ይህ ደግሞ ከፍተኛ ሀብት በነዳጅ በአልጋ በምግብ እየባከነ አዲሱ ክልል ለአንድ አከባቢ ዕድገት ሲሳይ እየሆነ ነው፤ ለዚህ ሁሉ ለማሳያነት በአንድ ቀን በአርባምንጭ ከተማ የተካሄዱ ሶስት ስብሰባዎችን በመረጃ አስደግፈን አቀረብንላችሁ” በሚል ያክላል።
“አቶ ጥላሁን ከበደ ሌሎች ከተሞችም በተለይ የክልሉ ክላስተር መቀመጫዎች በክልሉ በጀት ሊለሙ ይገባል ለአርባምንጭ ከተማ ልማት 500 ሚሊዮን ብር ያለ ካብኔ ውሳኔ የተሰጠው ለማዕከላቱም ሊሰጥ ይገባል። በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ሜዳ 19ኛ የብሔረሰብች ቀን መከበሩ ቀድሞ እየታወቀ በበአል ስም የተወሰደው ለሁሉም ከተማ መሰጠት አለበት” በሚል ይጠቁማል።
በጥናቱ ቀሪ 5ቱ ማዕከላት በቂ ሆቴል የለም በሚል ሰበብ ሁሉም ስብሰባ በአንድ ማዕከል መሆን የለበትም ፍትህ ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ለ5ቱ ማዕከላት ፍትህ በወሬ ብቻ ለሚያልቅ ከበቂ በላይ የሆነ የክልሉ ሀብት እየባከነ ነው ፍትህ ለውስን የክልሉ ሀብት ብክነት ከፍተኛ መሆኑም ተመላክቷል።
ከጥናቱ በተጨማሪ በጉዳዩ ዙሪያ በክልሉ ሀብት ብክነትና አንድ ማዕከል ብቻ እንዲለማ በርዕሰ መስተዳድሩ ከፍተኛ ፍላጎት አዲሱ ክልል በቅርቡ ወደ ለየለት ትርምስና ብጥብጥ ሊያመራ እንደሚችል አንድ የክልሉን ፖለቲካ በቅርበት የሚያወቅ የሚድያችን ተከታይ አስረድቶናል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏