የመብት ተሟጋችና የዩንቨርስቲ መምህር የሆነው “ፕረዚዳንቱን ተችቷል” በሚል በህገወጥ መንገድ ለአንድ ዓመት ያለቅጣት ውሳኔ በእስር እንዲቆይ መደረጉ በአከባቢው ቅሬታ ፈጠረ

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ መምህር መለሰ አብረሃም የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ መምህር እንዲሁም የሀዲያ ሚዲያ ኔትወርክ ሚዲያ መስራች ሲሆን በሀገረ-ህንድ የዶክትሬት ትምህርቱን እየተከታተለ ካለበት ለምርምር ሥራ ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሰ በኋላ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑትን አቶ እንደሻው ጣሰውን “በማህበራዊ ሚዲያ ተችተሃል” በሚል ለአንድ ዓመት ሙሉ ያለ ፍርድ ቤት የቅጣት ውሳኔ በእስር ቤት እያሳለፈ እንደሚገኝ ቤተሰቦቹ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጧል።

ቤተሰቦቹ መለሰ ከታህሳስ 2016 እስከ ግንቦት 2016 ዓ.ም ለ6 ወራት ያለምንም ክስ በሆሰዕና ማረሚያ ታስሮ እንድቆይ ከታደረገ በኃላ በ100 ሺ ብር ዋስ ተለቀው እንደነበር ተናግሯል።
ከእስር ስወጣ ወደ ህንድ ለመሄድና በማረሚያ ቤት በእስር ሆኖ የሰራውን የጥናት ውጤት አስረክቦ ለመመለስ ጉዞ ጀምሮ ኤርፖርት ገብቶ ሙሉ ህደቱን ካለፈ በኃላ ቀድሞ ከሀገር እንዳይወጣ እግድ ተቀምጦበት ስለነበር ማለፍ አትችልም ተብሎ መመለሱንም አክለዋል።
ከዛ በኃላ በሁለተኛ ቀንም በክልሉ ፕረዚዳንት እንዲታሰር ተደርጎ በመጀመሪያ ወደ ሆሳዕና ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በግዜ ቀጠሮ ስመላለስ ቆይቶ የነበረውን በዋስ ለመልቀቅ ከጫፍ መድረሱን ያወቀው የክልል ፍትህ ቢሮ ዐ/ህግ ጉዳዩን ወደ ሀዲያ ዞን ከፈተኛ ፍ/ቤት ማዞሩን ቤተሰቦቹ አስረድቷል።
ከፈተኛ ፍ/ቤቱም የቀረበበት ክስ የዋስትና መብት የማያስከለክል መሆኑን ጠቅሶ በ200 ሺህ ብር ዋስ እንድፈታ በማዘዙ ቤተሰብ የፍርድቤቱን የባንክ አካውንት ቁጥርና የመዝገብ ቁጡር ለመቀበል ሄዶ እዛው እያለ ከህግ ውጪ የከፍተኛ ፍ/ቤት ፕረዚደንት በፍጥነት ወደ መዝገብ ቤት በመዝለቅ የመለሰ አብረሃምን መዝገብ ስጡኝ በመለት መዝገቡን ተቀብሎ በቢሮው አስቀምጦ መውጣቱን ቅሬታ ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንደለ መለሰ ለ4ተኛ ግዜ በመታሰሩ የሀዲያ የሁሉም ጎሳዎች ባህላዊ መሪዎችና የሁሉም የሀይማኖት አባቶች በመሆን ወደ ክልሉ ርዕሰ-መስተዳደር አቶ እንደሸው ጣሰው ቢሮ ሄደው መናገራቸውን ተናግሯል።
በዕለቱ የርዕሰ መስተዳድሩ ዋና አማካሪ የሆኑትን አቶ ንጉሴ አስረስን አግኝተው ተወያይተው አቶ ንጉሴ ለሀዲያ ሽመግሌዎችና የሀይማኖት አባቶችን “የመለስን ጉዳይ ሀላፊነት የምትወስዱት ከሆነ ደብዳቤ ጽፋችሁ መለሰም ደብዳቤ ጽፎ ይዛችሁ ኑ” ብለው እንደነበር ገልጿል።
ሽመግሌዎቹም “ቀጥታ ወደ ሆሳዕና ማረሚያ በመውረድ መለስን አስጠርተው ይህንኑ ነግረውት ከዝህ በኃላ በምድያ ሥራ ከክልሉ መንግስት ጋር ግጭት ውስጥ የሚያስገባ ነገር ውስጥ እንደማትገባ ለኛ ቃል ግባልን፣ ይቅሪታ ጠይቀህ ወደ ትምህርትህ ህድ አሉት። መለሰ “እኔ ያጣፈሁትና ያላወኩት ነገር ካለ ይቅርታ ይደረግልኝ” ብሎ ለክልል መንግስት ደብዳቤ ጽፎ ለሽማግሌዎች ሰጣቸው ብለዋል።
ሽማግሌዎቹም ደግሞ ሀላፊነት ወስደው ጉዳዩን እንደሚያዩ ገልጸው ጽፈው አንድ ላይ ለክልሉ ፕሬዚዳንት አማካሪ ሰጡት። እሱም ደብዳቤዎችን ለክልሉ ፕሬዚዳንት ማስረከቡን ነገሯቸው፣ እንጠራችኋለን ብሎ ሸኛቸው። ከዚያ ወድህ በተደጋጋሚ ሽመግሌዎች ቢሄዱም ከበረ እንዳያልፉ ጠባቂዎች እየከለከሏቸው ይይመለሳሉ” ሲሉ ቤተሰቦቹ በምሬት ይናገራሉ።
በዚሁ መሀል የሀድያ ዞን ከፈተኛ ፍ/ቤት መለሰን በዋስ እንድወጣ መፍቀዱን የተገለፀ ቢሆንም የክልል ፕሬዚዳንት ለዐ/ህጎችና ለደኞች በቀጥታ ስልክ እየደወለ እንዳትፈቱት እንደምላቸውና እምቢ ካሉ ስራቸውን እንደሚያጡ እያስጠነቀቃቸው እንደሆነ ከአንደበታቸው የሰማነው” በሚልም ቤተሰቦቹ የሁኔታውን ውስብስብነት በመግለፅ ለልጃቸው ፍትህ እንዲሰጥ ጠይቋል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
Ethiopia #Hadiya #gurage
በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው
በማህ