1000030613

ሰበር ዜና

ም/ርዕሰ መስተዳድሩ በባላሃብቶች ታጅቦ ፍ/ቤት ከመቅረቡ በተጨማሪ ለህግ ተገዢ ላለመሆን ላደረጉት ሙከራና እንቢተኝነት ሀምሳ ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በሰሩት የሙስና ተግባር ህጋዊ የሆነው ማራ ማይነርስ የተባለ ድርጅት ከፍተኛ በደል መድረሱን በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ፒያሳ ምድብ ችሎት ታህሳስ 15/2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 በዋለው የሙስና ክስ መዝገብ አመላክቷል።

በዚህ ችሎት የክልሉ ዉሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊና በም/ር/መ/ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪ ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ በአስገዳጅ ፍ/ቤት ትእዛዝ በችሎቱ ቀርቦ ምላሽ መስጠቱ ተሰምቷል፡፡

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህግና ሕገ መንግስታዊ አሰራር የለሌለው አደገኛ ማፈያ ቡድን የሚመራ ክልል መሆኑን የማራ ማይነርስ ድርጅት ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ማስረዳቱን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሌቦችና በኮንትሮባንዲስቶች የሚመራ ክልል ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ ይህ የማፍያ ቡድን በክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት የሚመራ እንደሆነ ምንጮች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጧል።

ፍትህ ለማግኘት እስከ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ድረስ አቤት ብሉም ምላሽ የሚሰጥ አካል በመጥፋቱ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ የከፈተው ‘ማራ ማይነርስ’ የተባለ ድርጅት በጋሞ ዞን ቦሮዳ ወረዳ ቦታ ተረክቦና በካዳስተር አስመዝግቦ ጥናት ሲደረግ ከፍተኛ የማዕድን ክምችት መኖሩ መረጋገጡን የተረዱ የክልሉ ሙሰኛ አመራሮች በአንድ ጀምበር እነሱ የተካተቱበት አዲስ ማህበር በማደራጀት ማራ ማይነርስ ለተባለ ድርጅት በተሰጠው ቦታ ላይ ደርበው በማደራጀት ወረቀቶች ላይ ስርዝ ድልዝ በማድረግ ከስይስተም ውጭ በማኑዋል በመስራት ለራሳቸው መውሰድ መቻላቸው ህገ ወጥ መሆኑን የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት የፒያሳ ምድብ ችሎት ባቀረቡበት የክስ መዝገብ መነበቡ ታውቋል፡፡

ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ ፍ/ቤቱ የላከውን መጥሪያ ላለመቀበል በማስቸገሩ በፌደራል ፖሊስ ተገድዶ በአማካሪው በኩል የክስ ይዘትና መጥሪያ የደረሳቸው በመሆኑ ከፍተኛ አስፈጻሚ አካል ሆኖ ለህግ ተገዢ ላለመሆን ላደረጉት ሙከራና እንቢተኝነት 50000 ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል፡፡

ሆኖም በህገ ወጥ መንገድ ባደራጃቸው ባለሃብቶች የታጀበው ችሎት ፍትህ ናፋቂና ጠያቂ በሆነው ድርጅትና ጠበቃቸው ላይ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡

በፍ/ቤቱ ጠንካራ አቋም የደነገጠው ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ ደጋግሞ እኔ የክልል ም/ቤት አባል ነኝ ያሉት ሲሆን ፍ/ቤቱም የህዝብ ውክልናና ሃላፊነት ካለህ እንዴት ወንጀል ትፈጽማለህ በማለት ስርአት ማስያዙን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሙስና ወንጀል መረጃዎች በድምጽና በሰነድ ተደራጅቶ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ከሆነበት ጊዜ አንስቶ ህገ ወጥ ተግባራቸውን ህጋዊ ለማድረግ ያለእንቅልፍ የምሰሩ ኢንጅነር አክልሉ አዳኝ በቅርቡ ለክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ በተሳሳተ መንገድ ሀሳብ አቅርቦ ካስወሰነ በኋላ የጋሞ ዞንና የቦረዳ ወረዳ መዋቅሮቹም የህገ ወጥ ተግባራቸው ተባባሪ ሆነው የክልል አስተባባሪ አቅጣጫ ነው በማለት ያለማመንታት ተቀብለው ፈጽመዋል፡፡

ክልሉ በአደገኛ ማፈያዎች ኔትወርክ የሚመራ ስለመሆኑ በቂ ማሳያም ነው ተብሏል፡፡የምደረአንፃር “በማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንት በሕጉ መሠረት በቅድሚያ አንድ ባለሀብት የማዕድን ቅኝት (Exploration) ሕጋዊ ፈቃድ ከእነ coordinate ነጥቦች ጋር ከተሰጠ በኋላ፣ የፀደቀ የአዋጭነት ጥናት ሰነድ፣ የአከባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ጥናት ሰነድ፣ የማልማት አቅም፣ የንግድ ምዝገባ ሰነዶች ከቀረቡ በኋላ አስቀድሞ የተፈቀደው ይዞታ መጠን ሊቀነስ እንደማይችል ሕጉ ይደነግጋል።

ነገር ግን ባለሀብቱ የማምረት አቅሙ ደካማ ከሆነ፣ በራሱ ፍላጎት ይዞታው ይቀነስልኝ የሚል ጥያቄ ካቀረበ፣ በአከባቢው ማህበረሰብና ሥነምህዳር ላይ የከፋ ጉዳት የምያደርስ መሆኑ በጥናት ከተረጋገጠ፣ ከይዞታው ሊቀነስ ይችላል።

ከዚህ ውጭ ከልማታዊ ባለሀብት ቀንሰው፣ በጥቅም ትስስር ለሌላ ግለሰብ ወይም ድርጅት ማስተላለፍ ሕጉ አይፈቅድም።

ሆኖም ከሕጋዊ አሰራር ውጭ ከማራ ማይነርስ ተቀንሶና እላዩ ላይ ሌላ ማህበር ተመስርቶ የነበረው ህገወጥ አሰራር በተመለከተ በፌደራልም ሆነ በክልል ደረጃ የፍርድ ቤት ክርክር ሂደት እያለ ህግን በመጣስና የፍርድቤት ትዕዛዝ በመተላለፍ ከህጋዊ ማህበር በህገወጥ መንገድ ለሌሎች ለማስተላለፍ የተፈለገበትን የቢሮ ኃላፊው ማብራሪያ እንዲያቀርቡ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን አጥብቆ በመያዙ ድንጋጤ ውስጥ የምገኙት የክልሉ ም/ር/መስተዳድር አክልሉ አዳኝ ከእሳቸው ጋር ተሳፍሮ የሄዱ የአዲሱ ማህበራቸው አባል የሆኑ ባለሃብቶች ጋር ምክክር በማድረግ የማራ ማይነርስ ድርጅት ጋር ለመደራደር እስከዛሬ በአዲስ አበባ እየተማጸነ እንደምገኝ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡

በባለሃብቶች የታጀበው ችሎት ጠንካራ ክርክር የተደረገበት ሲሆን በስይስተም የተሰራውን ቀይሮ በማኑዋል ለማስተካከል የተደረገው ጥረት ምንም ያህል ፍትህን ለማዛባት የሚደረግ ሙከራ ቢሆንም ጊዜውን ጠብቆ እውነቱ መውጣቱና ሙሰኞች ተገቢውን ቅጣት ማግኘታቸው እንደማይቀር አመላካች ነው እያልን የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጉዳዩን እስከመጨረሻው ተከታትሎ መረጃ እንደሚያቀርብ ከወዲሁ ይገልጻል፡፡

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southernethiopia