
በውድድሩ የወላይታ ጦና ቦክስ ክሌብን ጨምሮ 6 ክሌቦች እንደሚሳተፉ ተገለጸ።
ወላይታ ጦና፣ ፌደራል ፖሊስ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ፣ ድሬ ከነማ፣ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን እና አካዳሚ በተለያዩ የክብደት ደረጃዎች ተወዳዳሪዎችን ማቅረባቸውን ከአዘጋጅ ኮሚቴ ከተገኘ መረጃ ተረጋግጧል።
የውድድሩ አዘጋጅ የወላይታ ዞን ስፖርት ምክር ቤት ሲሆን የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች ለእንግዶቹ ደማቅ የእንግዳ አቀባበል ማድረጋቸውን የወላይታ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ሰፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ አኮየ ጌካ ገልጸዋል።
አቶ አኮየ አክለውም ውድድሩ ዛሬን ጨምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ በመሆኑ በቆይታዉ ስፖርተኞች ምቹ ጊዜ እንደሚያሳልፉ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል።