ህብሰተሰቡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመጣው የኑሮ ውድነት እንዳይጎዳ ለመከላከል የተለያዩ መፍትሔ እርምጃዎች መጀመራቸውን የዎላይታ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ገለጸ።
መምሪያው ንፁህ የሱፍ ዘይትን ጨምሮ ሌሎች የፍጀታ ዕቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በጅንአድ በኩል ለመንግስት ሰራተኞች ማቅረብ መጀመሩን የመምሪያው ኃላፊ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም ተናግረዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች የተፈጠረው የዕቃዎች ዋጋ ውድነት ዜጎች ህይወታቸውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዳይመሩ አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጥሯል።
ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ እርምጃዎች የተወሰዱ ቢሆንም የተፈለገው ውጤት አለመገኘቱን ኃላፊዋ አክለው ተናግረዋል።
በመሆኑም ከተለያዩ የንግድ ተቋማት ጋር በመሆን ዕቃዎችን ቀጥታ ለሸማሾች የማቅረብ ስራ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
ከእነዚህም መካከል ዘይት፣ ስኳር፣ ሳሙናና ፉርኖ ዱቄት በአሁን ጊዜ የቀረቡ ሲሆን ቀጣይ የግንባታ መሣሪያዎችንም ለማቅረብ ዕቅድ ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
5 ሌትር ንጹህ የሱፍ ዘይት በ375 ብር ፣ 5 ኪ/ግ ፉርኖ ዱቄት በ324 ብር እና ሳሙናና የመሳሰሉ ዕቃዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ከጅንአድ ለመንግስት ሰራተኞች የቀረቡ መህናቸውን ወ/ሮ እታገኝ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል 74ኛው ዙር የፍጆታ ዕቃ ስርጭት በተመለከተ 7679 ኩንታል ስኳር በዳሞታ ወላይታ ገበረዎች ዩኒየን እና 383320 ሌትር ዘይት በወንዶ የንግድ ኩባኒያ በኩል የቀረቡ በመሆናቸው ህብረተሰቡ በየአካባቢው ወዳሉ ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት በመሄድ ገዝቶ እንዲጠቀም ወ/ሮ እታገኝ ጠቁመዋል ሲል የዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል።