1000030624

የዎላይታም ሕዝብ በተደጋጋሚ የሕወሓትና የኦነግ ሸኔ ተባባሪ እየተባለ በብዙ የፈደራልና የክልል ብልጽግና ሹማምንት ተከሷል፣ ከፋኖ ጋር ይሰራል ተብሎም ተከሷልና ይሄ ከምን የመነጨ ነው?

ህዝቡ ማንም የሰጠዉ ተልዕኮ ኖሮ ሳይሆን መንግስት መመለስ ያለበት ሐቀኛ እና ሕገመንግሥታዊ ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ላለመመለስ ለምን የዳቦ ስም ይሰጣል ?በሄዱበት ቦታ ሁሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ስለህዝቡ ውሸት ለምን ያወራሉ ለምን ሀቅ ይደብቃሉ ? ለእነኚህና መሰል ጥያቄዎች የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ፖለቲካ ወጌሻ መደበኛ ጥንቅር ምላሽ እንደሚከተለው አቅርቧል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ማዲያ፦ አገዛዙ የዎላይታን ሕዝብ ለምን በተከታታይ በሐሰት ይከሳል፣ ከሕወሓትም፣ ከኦነግ ሸኔም፣ ከፋኖም ጋር ለምን ይፈርጃል ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እንግዲህ የሐሰት ክስ ለኢትዮጵያ ፖለተካ አዲስ ነገር አይደለም በተለይ መንግስት ትርጉም ያላቸዉን የፖለቲካ ጥያቄዎች የሚያነሱ አካላትን በሐሰት ሲከስ ኖሯል በኢትዮጵያ ታሪክ። በኢህአዴግ ጊዜም ለምሳሌ ግለሰቦችን አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸዉ እያሉ ማሰር የተለመደ ነው በሐሰት።

ለምሳሌ እንደነ በቀለ ገርባ አይነት ሐቀኛ ፈደራሊስት ፖለቲከኞችንም ሳይቀር የሐሰት ምስክር በማዘጋጀት ፍርድ ይበየንባቸዉ ነበረ። በተለያዩ ግለሰቦችም ላይ ዶክመንተሪ በሐሰት እየተፈበረከ ይሰራ ነበር። አሁን የብልጽግናን ለየት የሚያደርገዉ ሕዝብን በሐሰት በጅምላ መክሰስ መጀመሩ ነው።

ለምሳሌ ከትግራይ ጦርነት በፊት “የትግርኛ ተናጋሪዎች” እየተባለ እጅግ አደገኛ የሆኑ በማረሚያ ቤት ተሰሩ የተባሉ ወንጀሎች በዶክመንተሪ መልክ በቴሌቪዥን ተሰራጭተዋል። የዎላይታም ሕዝብ በተደጋጋሚ የሕወሓትና የኦነግ ሸኔ ተላላኪ እየተባለ በብዙ የፈደራልና የክልል ብልጽግና ሹማምንት ተከሷል፣ ከፋኖ ጋር ይሰራል ተብሎም በዶክመንተሪ ተከሷል። እዉነታዉ መንግስት መመለስ የማይፈልጋቸዉ ሐቀኛ እና ሕገመንግሥታዊ ጥያቄዎች የዎላይታ ሕዝብ አሉት እንጂ ማንም የሰጠዉ ተልዕኮ ኖሮ አይደለም።

በነገራችን ላይ ይህ ብቻ አይደለም የአሁኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ በፌደሬሽን ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ከአወዛጋቢው የዎላይታ ሕዝበ ዉሳኔ በኃላ በተደረገ መድረክ ላይ በዎላይታ ላይ ሐሰተኛ ክስ በሕገወጥ መንገድ ፈብርኮ “እንደዉም በዎላይታ በተካሄደው ሕዝበ ዉሳኔ ሕዝቡ መታወቂያ ተከልክለን ነበር የኖርነዉ፣ አሁን ለሕዝበ ዉሳኔ ሲሉ አደሉ የሚል መረጃ ነው ያገኘነው” ብሎ ዋሽቷል።

እርሱ በሕጋዊነት መረጃ ማግኘት የሚችለዉ ከዎላይታ ዞን ብቻ ነው። የዎላይታ ዞን ደግሞ በሠጠዉ መግለጫ ዉስጥ እንደዛ አይነት ነገር የለም። ይህ የሐሰትና የጥላቻ ክስ ከግለሰቡ አልፎ የብልጽግና ፓሪቲም ተጠያቂ መሆን እንዳለበት ግልጽ ነው።

ይህን ለማስረዳት አንዴ ወደሁዋላ ልመልሳቹ ለዉጡን ያመጣዉ አንዱ ህወሀት በኦሮሚያ ክልል ከኦህዴድ መዋቅር መዉሰድ እያለበት፤ የራሱን መረብ ዘርግቶ የሐሰት መረጃ እየተቀበለ በፈደራል መንግሥት ዉሳኔ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል የሚለዉ ነበር። ብልጽግና ይህን አሰራር አስቀራለዉ ብሎ ነበር፤ ነገር ግን እነ አቶ ጥላሁን ከበደ የሐሰት መረጃ እየፈበረኩ በዎላይታ ሕዝብ ላይ ሴራ ሲጎነጉኑ ነበር።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እነዚህ እና የመሳሰሉት በተለይም ሕዝብ ላይ ያነጣጠሩ የሐሰት ክስና ፍረጃዎች ምክነያታቸዉ ምንድነው ? ተጽዕኗቸዉስ ምን ድረስ ነው ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ ምክንያቱ ፖለቲካዊ ግብ ነዉ፣ ማሳነስ የሚፈለጉ ብሔሮች አሉ፥ ቂም በቀል እየተፈጸመባቸው ያሉ ብሔሮች አሉ። በዋናነት ሐገሪቷን የሚመሩ ኃይሎች ካላቸዉ አላማ ይነሳል፣ በተለይ እነዚህ አይነት ሕዝብ ላይ ያነጣጠሩ ክስና ፍረጃዎች የበላይ አካላት ሳይፈቅዱ ይደረጋሉ ብሎ ማሰብ ቀልድ ነው። አላማዉ ክፉ ይሁን እንጂ ደረጃና አይነቱ ይለያያል በተለያዩ ሕዝቦች ላይ።

ተጽዕኖዉ ዘርፈ ብዙ ነው፤ በዋናነት በቀጥታ ከመንግሥት መዋቅሮችና ከመንግሥት ጋር በቅርበት በሚሰሩ አካላት ጀምሮ፣ በተዘዋዋሪ ወደ ግል ዘርፎችም ይዘልቃል። ሕዝብን ተጠርጣሪ ያደርጋል፣ ቦታ እንዳይሰጠዉ ያደርጋል፣ የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች በዛ አቅጣጫ ሥራቸዉን ይከዉናሉ።

በተጨባጭ ግን ነገሩ የዎላይታ ሕዝብ በመንግሥት መገፋቱንና እንደተገፋ እንዲቀጥል ፍላጎቶች መኖራቸዉን ያሳያል። ለምሳሌ በሁሉም ቦታ ጦርነት ሲካሄድ፣ በቀጥታ ከጦርነቱ ጋር የማይያያዝ ሕዝብ የሚከሰስበት ከሆነ፤ ተፈርጆ ከሚጎዳዉ በተጨማሪ፣ ጦርነቶቹ በሚያመጧቸዉ የአሰላለፍ ለዉጥም እየተጎዳና እየተገፋ እንዲሄድ ያደርጋል። ጉዳቱም ከፖለቲካ ዉክልና መነፈግ፣ ተደማጭነት መነፈግ እና የኢኮኖሚ ጥቅም መነፈግ ያስከትላል። የሕዝብን ገጽታና ስምንም ያጠለሻል።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ በጦርነቶች ጊዜ ሕዝብ ፈርጆ ከጎዱ በኃላ የሰላም ስምምነት ሲፈረምስ ያንን ሕዝብ ዞር ብሎ አለማዬት ልክ ነው ?

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ የሚገርመዉ እሱኮነዉ ቀጥታ እንደሚታኮስ ቡድን ደርበዉ ይቀጡሐል፣ የሰላም ስምምነት ሲመጣም በተለይ ዎላይታን ገፍቶ የመቀጠል ፍላጎት አለ ያ የትም የሚያደርስ አይመስለኝም። በቀጥታ ጦርነት በሚካሄድበት ሰላም ሲመጣ በተመሳሳይ ተፈርጀዉ የተሰቃዩ የዎላይታ አይነት ሕዝቦችንም ጉዳይ ማየቱ ተገቢ ነው።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ እንደወትሮው ሁሉ ፈቃደኝነት አሳይተው በተነሱ ጉዳዮች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ትንታኔ ስለሰጡን በሚዲያችን እንዲሁም በውድ ተከታዮቻችን ስም እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን።

✅ ፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና፦ እኔም አመሰግናለሁ።

🎙💻 ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ፦ መልካም። ዳግም በሌላ ጉዳይ እንደምንገናኝ ተስፋ እናደርጋለን።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Tigray #Amhara #Oromo

ማሳሰቢያ ለውድ አንባቢያን፦ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በዚሁ “የፖለቲካ ወጌሻ” መደበኛ እንግዳ ዝግጅት ጠለቅ ያለ ልምድና ክህሎት ካለው ፖለቲካ ጉዳዮች ተንታኝ በፕሮፌሰር ማሪንዶስ ጦና ( የብዕር ስም ) ጋር ቆይታ በማድረግ ያቀረበ ሲሆን ከዚህ በፊትም በተለያዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች እንዳቀረብነው የሚታወስ ነው። በቀጣይም በሌሎች ጉዳዮች እንደምንመለስ በአክብሮት እንገልፃለን።