“ፕሬዝዳንቱ በትናንትናው ዕለት የጋሞ አባቶች በውድድር ላይ እያሉ በዎላይታ ላይ በ3ቱ አቅጣጫ የተለመደውን ጦርነት በማወጅ የስድስት ሰዎች ህይወት እንዲያልፍ በርካቶች እንዲቆስሉ አድርጓል” – የለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አስተባባሪዎች
የአቶ ጥላሁን ከበደ ሴራ መጨረሻው መቼ ይሆን?

“በመጀመሪያ ደረጃ ንፁህ የጋሞ አባቶች ለሠላም ባበረከቱት አስተዋፅኦ ላገኙት ዕውቅና እንኳን ደስ አሎት ደስ አለን ለማለት እንፈልጋለን። እንግዲህ ይህ ትልቅ ዕውቅና በመሆኑ እናንተ እያላችሁ የዛይሴ፤ የዶርዜ፤ የቁጫ እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን በሚድያ ብቻ የሠላም ተምሳሌት እየተባለ በእውኑ ዓለም እየተሰቃዩ መቀጠል የለባቸውም ብለን የሚናምን ስንሆን በተላይም ትክክለኛ ማንነት የማይታወቅ አፉ ቅቤ ተግባሩ ሰይጣን፤ በአፉ ብልፅግና በተግባሩ ሰይጣን የሆነው የአቶ ጥላሁን ከበደ የእናንተን ጭምብል ተጠቅሞ የሚያደርገውን አረመናዊ ድርግቱን ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል” በሚል የለውጥ አቀንቃኝ ከፍተኛ ባለስልጣናትና አስተባባሪዎች በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጿል።
“በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ በሀገር ደረጃ የጋሞ አባቶች በውድድር ላይ እያሉ አቶ ጥላሁን ከበዴ ዎላይታ ላይ ደግሞ በ3ቱ አቅጣጫ የተለመደውን ጦርነት ማወጁን ከምንጮቻችን አረጋግጠናል” ብሏል።
ለአብነት ሲገልፁ፦ “ይኼውም በሠላምበር እና አካባብያዋ የሚኖሩ ዎላይታዎች እንድፈናቀል፤ በዳሞት ፑላሳ የአቶ ገብረመስቀል ጫላ ጎሳ እና የአቶ ሳሙኤል ፎላ ጎሳ እንድጋጬ በማድረግ የ2ት ሰው ሞት እና የበርካታዎቹ ከባድ ጉዳት እንድሁም ሲዳማንና ዎላይታ በሚያዋስነው ድንበር የ3ት ሰው ሞትና የበርካቶች አካል ጉዳት ያስከተለ ግጭት እንድፈጠር አድርጓል” ስሉ አብራርተዋል።
ይህንን ተልዕኮ ለጋሞ ዞን ፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ለሆኑት ለአቶ መኮንን እና ለክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ለሆኑት ለፍሰሀ ጋረደው እንደተሰጣቸው ማረጋገጥ ተችሏል።
“ኮምነሽር ፍሳሃ ጋረደዉ የክልሉን ሠላምና ፀጥታ የመምራትም ሆነ የማስጠበቅ ሥራ ሀላፊነትም፣ ዝግጁነትም ሆነ ፍላጎት የለዉም፤ እሱ አቅሙንና ጊዜዉን ሰጥቶ የሚሰራዉ በዎላይታ ዉስጥ የራሱን አደረጃጀት ተጠናክሮ የምቀጥልበት እርካሽ ፖለቲካ ሥራ ዉስጥ ተጠደምዶ ነዉ ያለዉ” በሚል ተጠያቂ አድርጓቸዋል።
“ሲጀመር ኮ/ር ፍሳሃ ጋረደዉ ከዚህ ቀደምም በአዋሳ ከተማ የዎላይታ ተወላጆች ማንነትን መነሻ ያደረገ ጥቃት ሲፈፀም አይቶ እንዳላዬ ራሱንና ልጆቹን ይዞ አ/አበባ በመሸሹ ለዉለታዉ አ/አበባ ከተማ አስተዳደር ሹመት ተሰጥቶ ቆይቶ አሁንም ይሄን እሱ በስሜ ዎላይታነት የሚነግደዉን ህዝብ ለፍትህ እጦትና ለህይወት ማጣት ለመዳረግ ደቡብ ኢት/ያ የሚባል ክልል ሲዋቀር ከአቶ ጥላሁን ከበደ እና ከአቶ ተክለወልድ አጥናፉ ልዩ ተልዕኮ ይዞ ፖሊስ ኮሚሽነር ሆነዉ ተሹመዉ መጥተዋል” በሚል ሁኔታውን አስረድተዋል።
“ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የዎላይታ ዉስጥ ፖለቲካን በመበጣበጥና መረጋጋት እንዳይኖር በማድረግ የዎላይታ ህዝብ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ወድቀት ዉስጥ ሆኖ ለአቶ ጥላሁን ከበደ የእጁ ጦር መሣሪያ በመሆን እሱ የሚያሳድዳቸዉን የዎላይታ ጠቃሚ ፖለቲከኞችን በማፈንና በማሰር ተወጥሮ የዎላይታና የሲዳማ የድንበር ጉዳይ ለአንድ ቀንም እንኳን የህዝብ ሠላምና ፀጥታ ዘርፍ እንደምመራ ሰዉ ቅኝትም ይሁን ስምርት ሰጥቶ የፀጥታ ሁነታዊ ግምገማ አድርጎ አያዉቅም” በሚልም ተጠያቂ አድርጓቸዋል።
“ነገር ግን በሶዶ ከተማ ዉስጥ ያሉ ዜጎችን በየቀኑ የአቶ ጥላሁን ስዉር ተልዕኮን በመቀበል በማሰርና በማሰቃየት ሙሉ ጊዘዉን ያጠፋል፤ በዎላይታና ሲዳማ መካከል ያለዉ የድንበር አከባቢ ጉዳይ ፀጥታዉን በሚመራዉ አካል በልዩ ትኩረት ክትትል ተደርጎ ቢመራ ኖሮ ይሄን የህይወት ዋጋ የዎላይታ ህዝብ ባልከፈለ ነበር” ብሏል።
“ኮ/ር ፍሰሃ ጋረደዉ ለህሊና እና ለሙያ ዲስፕልን የሚገዛ ሰዉ መሆን የነበረበት ለአቶ ጥላሁን የመላላክና የኮንትሮባንድ ንግዱን በማጧጧፍ የአቶ ጥላሁን ከበደ ሴራ ዋና ዓላማ ህዝቡን በማማረር ወደ አመጽ ለማስገባትና የለውጡ አደናቃፊ ናቸው የሚለውን ድራማ ለማሳካት ነው። በአቶ ጥላሁን እና በአቶ ዓለማየሁ ባዉዲ ሴራ ምክንያት 38 ንፁሃን ዜጎች መጥፋቱን ህዝቡ እያወቀ በታጋሽነት ቀንና ማታ እንደፈለጋችሁ እንድትጨፍሩ አድርጓል” በማለት ገልጸዋል።
አስተባባሪዎቹ አክለው “ይህንን ታጋሽነት “ከሩቅ ስናያችሁ ጀግና ትመስሉን ነበር” ብሎ በየመጠጥ ቤት የሚያወራውን አቶ ዳዊት ገበዬሁንም ጭምር በሠላም አንከባክበን እያኖረ የሚገኝ ሲሆን በተደጋጋሚ ለፌዴራል መንግስት ጉዳዩን እንድያውቀው፤ እንድረዳና እንዲፈታ ጥረት ያደረግን ብሆንም መፍትሄ አልተገኘም” ብሏል።
“ሁላችንም እንደሚንገነዘበው ለትዕግስትም ልክና ገደብ ስላለው የሰው ህይወት ሳይጠፋ በዎላይታ ብሄር ላይ እየደረሰ ያለው ሁሉ አቀፍ በደል እንድቆም ጥሪያችንን እያስተላለፍን ለሞቱት ለንፁሃን ወንድሞቻችን ነፍሰ በሰላም ትረፍ እያልን ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን” መልዕክት ገልጸዋል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Sidama