የድንጋይ ከሰል ምርት ከባለሀብቶች ጋር ለመቀራመት ሲባል ለማዕድን ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት ለንፁህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት በመነፈጉ ህብረተሰቡ ችግር ላይ መውደቁ ተጠቆመ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በየደረጃው የምስተዋለዉን የንፁህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት ተደራሽነት ችግር ባለመቅረፍ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዳይሆን መደረጉን በቀረበው መረጃ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
የክልሉ ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ የንፁህ መጠጥ ዉሃ አቅርቦት ተደራሽነት በማስፋፋት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንድሆን ከማድረግ ይልቅ በማዕድን ዘርፍ የድንጋይ ከሰል ምርት ከባለሀብቶች ጋር ለመዘበር ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ በደቡብ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዞኖች የሚቀርበው ቅሬታ አመላካች ነው ተብሏል፡፡
በየቦታው የተጀመሩ የንጹህ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክቶች ቢሮው በቂ ድጋፍና ክትትል ባለማድረጉ እንደ ሀዉልት ቆመዉ እንደቀሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለንጹህ መጠጥ ውሃ ከተለያዩ ፕሮጀክቶች የመጣ ገንዘብ አመራሩ ለዉሎ አበልና ነዳጅ እያዋለ በመሆኑና ለፕሮጀክቶች ድጋፍ የተገኘ ተሽከርካሪ ፕሮጀክቶችን ከመደገፍ ይልቅ በማዕድን ፍለጋ ከባለሀብቶች ጋር በመዞር እንደምገኝ ታውቋል፡፡
የጥራት ደረጃውን ባልጠበቁ ማሽኔሪዎች በመገንባቱ በየጊዜው የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በተመረቁ ማግስት አገልግሎት የማይሰጡ ሆኖ ይገኛሉም ተብሏል፡፡
ቢሮው ፕሮጅክቶች ካሉባቸው ዞኖች ጋር በቅንጅት ባለመስራቱ፣ የዉሃ ተቋማት ጥገና ስራ ባግባቡ ባለመደረጉ፣ ለፕሮጀክቶች የሚመጡ እቃዎች ፎርጅድ በመሆናቸዉ የተነሳ ዘርፉን ዉጤታማ ማድረግ እንዳልተቻለም ተጠቁሟል፡፡
ለአብነትም
- የቦዲቲ ከተማ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት
- የላስካ ከተማ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት
- ሳዉላ ከተማ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት
- ከሌ ከተማ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት
- የቀይ አፈር ከተማ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት
- የጊዶሌ ከተማ መጠጥ ዉሃ
- የቡልቂ ከተማ መጠጥ ዉሃ ፕሮጀክት ተጠቃሾች ናቸው ተብሏል፡፡
እነዚህ ፕሮጀክቶች ለዘመናት ቆመዉ የቀሩ ስሆኑ ቢሮው በማዕድን ዘርፍ ሙሉ ጊዜውን ሰጥቶ ያለእረፍት ከምሰራ የንፁህ መጠጥ ዉሃ ጉዳይ የህይወት ጉዳይ እና ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር ችግር በመሆኑ ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ሲባል ለንጹህ መጠጥ ውሃ ተግባር ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏