ባለሀብቶቹ አቶ በላይነህ ክንዴ እና ዳኜ ዳባ የተባሉ ግለሰቦች ከፍተኛ የመንግስት አመራር ጋር በመመሳጠር በዎላይታና ሲዳማ አዋሳኝ አከባቢ የሰው ህይወት የጠፋበት ግጭት እንዲከሰት ቀጥታ ድጋፍ ማድረጋቸው ተረጋግጧል።
በአከባቢው ለሚፈጠረው የፀጥታ ችግርና የመሬት ወረራ ዋናው መንግስታዊ ድጋፍ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ እጅአዙር ድጋፍ እንደሆነም ምንጮቻችን ጠቅሷል።

የብልጽግና ከፍተኛ አመራሩ የራሱንና የቡድኑን ጥቅም ለማስጠበቅ ከዚህ በፊት የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳደሪ በነበረበት ወቅት ታጣቂዎችን ወደ አባያ ብላቴ እያስገባ ቀጠናውን ውጥረት እንዲነግስ እና ለዘመናት ተዋልዶ ተጋምዶ የኖሩ የሲዳማ እና ዎላይታ ሕዝብ ደም እንዲቃቡ ያደረገ እና እያደረገ የሚገኝ ግለሰብ መሆኑም ተገልጿል።
ባለሃብት ዳኜ ዳባ አባያ ብላቴ ከሚያለማው 500 ሄክታር ውስጥ 200 ሄክታሩ በምስጢር የተያዘው በሲዳማ ክልል ክፍተኛ አመራሩ በአቶ አብርሃም ማርሻሎ እና በቤተሰቦቹ ሲሆን በዚህ ምክንያት የመሬት ወረራ አባያ ብላቴ የተፈፀመ ያለው፡፡
አቶ በላይነህ ክንዴ በአባያ ብላቴ ቀበሌ የማገኘውን 550 ሄክታር የእርሻ ኢንቨስትመንት ይዞታ ካርታ እና ውል ከዎላይታ ዞን የወሰደ ቢሆንም ሌላ ተደራቢ ውል ከሲዳማ ክልል ሎክ አባያ ቀበሌ በመውሰድ ላለፉት ሦስት ዓመታት ዓመታዊ የመሬት መጠቀሚያ ኪራይ እና የገቢ ግብር ለሎክ አባያ ወረዳ እየከፈለ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ከትናንት በስቲያ የተቀሰቀሰው ግጭት ከመፈጠሩ ከሰዓታት በፊት የታጠቁ ልዩ ኃይሎችን ከሎክ አባያ ወረዳ መሬራ ቀበሌ የአቶ በላይነህ ክንዴ ተሽከርካሪዎች ግጭቱ ወደተከሰተበት ቦታ ስያመላልሱ እንደነበረ በአከባቢው የሚኖሩ ዓይን እማኞች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጠዋል።
“ጥቃቱ በተፈፀመበት ቀን ጥቃት አድራሽ ወታደሮች በበላይነህ ክንዴ እርሻ ውስጥ ባለው ምግብ ተመግበው፣ የእርሱ መኪኖችን ለዘመቻ ተጠቅሟል፣ የአብራም ማርሻሎ ወንድም በመኪናው ውስጥ ሆነው ኦፕሬሽን ሲመራ ነበር” ሲልም የአይን እማኝ ሁኔታውን አክለው ገልጿል።
አንድ ሔክታር ለም መሬት ብርቅ በሆነበት በአበላ አባያ ወረዳ ብላቴ ቀበሌ ቢሊዮን የሙዝ ዘለላ ለዘመናት የሚያሳፍስ 550 ሔክታር የእንቨስትመንት መሬት አቶ በላይነህ ክንዴ የተባሉት ባለሀብት ለ45 ዓመት ለማልማት በሊዝ መረከባቸውን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ በተጨበጠበት ከባለሀብቱ በኩል በተለያየ ግን ለበርካታ ሚዲያ መሬቱ የሚገኘው ዎላይታ ውስጥ መሆኑን የሚቃረን ተደጋጋሚ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ እንዲሁም ቦታው ከሲዳማ ጋር ያልተቋጭ የወሰን ውዝግብ ያለበት እንደመሆኑ በጉዳዩ ላይ የሚመለከተው አካል ማብራሪያ እንዲሰጥበት በተደጋጋሚ ቢጠየቅም እስከዛሬ ዝምታን መርጠዋል፡፡
የቀድሞ አባያ እርሻ ልማት ይዞታ 1,262 ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 500 ሄክታር ይዞታን ለ25 ዓመት፣ አንድ ሄክታርን በ500 ብር ሂሳብ አከራይተዋል። (ዎልማ ለመንግስት ዓመታዊ የመሬት መጠቀሚያ ኪራይን በአንድ ሄክታር 1,000 ብር ይከፍላል፤ 500 ብር ከስሮ)። ነገር ግን ለአቶ ዳኜ ውል ይኑረው እንጂ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አልተሠራም፣ ወሰኑ አይታወቅም፣ ጎርፍ ያልገባበትንና አሲዳማ ያልሆነውን ቦታ በሙሉ እያማረጠ ሲያርስ ነበር። ይሁን እንጂ በ2014 ዓ.ም አንድ ዓመት ብቻ ከአባያ ወጣቶች ጋር በመጋጨቱ (የጉልበት ሠራተኛን፣ ጥበቃንም ጭምር ከኦሮሚያ ጭኖ በማምጣቱ) ከ2015 ጀምር ሥራ አቁመዋል።
ለችግሩ እንደመንስኤ የሚሆነው የዎላይታ ልማት ማህበር 1262 ሄክታር ይዞታን የሚያስተዳድርና የሚያለማ መዋቅር ቀርጾ፣ በየዘርፉ ሠራተኛ መቅጠር ሲገባው የድሮ አባያ እርሻ ልማት ጥበቃ የነበሩ 8 ሽማግሌ ጠባቂ ውጪ አንድም ሠራተኛ አልቀጠረም፤ ከሲቢክ ማህበራት ዘርፍ 3 ባለሙያ ደርቦ እንዲሠራ በማድረጉ ይዞታው ዳዋ ለብሶና መክኖ ተቀምጧል። ይህንን ምቹ ሁኔታን የተመለከቱ ሴራኛ አመራሮችና ባለሀብቶቹ ተመሳጥሮ በየቀኑ በከፍተኛ ፍጥነት ወረራ እያካሄዱ ይገኛሉ።
በዚህ ሁሉ መሀል ባለሀብቶቹ አቶ በላይነህ ክንዴ እና ዳኜ ዳባ የተባሉ ግለሰቦች በዎላይታና ሲዳማ አዋሳኝ አከባቢ ግጭቱ እንዲከሰት ቀጥታ ድጋፍ የመሬት ወረራ ዋናው መንግስታዊ ድጋፍ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ ጋር በመሆን በአከባቢው ከፍተኛ ውጥረት እንዲፈጠር እያደረጉ ይገኛሉ።
እስካሁን የክልሉን ህዝብ ከጥቃት የመከላከል
ኃላፊነት ከመወጣት በተቃራኒው በእጅአዙር ድጋፍ በመስጠት የተባበረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስካሁን ዝምታ የመረጠ ሲሆን በተፈጠረው የግጭት ጠመቃ ዎላይታ በኩል ሶስት የአከባቢው ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን ተጨማሪ የሰው ህይወት ሳይጠፋ የሚመለከተው አካል ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Sidama