1000031283

የዎላይታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ስነ ልቦናዊ፤ ስነ ምህዳራዊ መጎሳቆል ከመቼ ይጀምራል? ዎላይታ በምኒልክ ወረራ ወቅት በተለይም የአጎራባች ግዛቶች አቀባበል ምን ይመስል ነበር ? – ከፈረንሳዊ አይን ምስክርነት

      (ክፍል ሁለት)

ይህ ጸኁፍ በ1896 ዓ.ም ምኒልክ ዎላይታን ሲወር አብሮት የተጓዘው ፈረንሳዊ ጸሃፊና የአይን ምስክር የነበረው ጀግ #ቫንደራሂም /J.G Vanderhem የዕለት ማስታወሻ ሲሆን ስማቸው በምህጻረ ቃል የተገለጸ ዶክተር D.M ከተረጎመው የተወሰደ ነው፡፡

ጹሑፉ ጉምቱ የዎላይታ ባህል አዋቂና ምሁር ለነበሩት ለክቡር ዶክተር ዘብድዎስ ጫማ በነጻ የተሰጠ ስጦታ አንደነበር በትርጉሙ ላይ ተብራርቷል፡፡

ጸሃፊው ስለ ዎላይታ እንደጻፈው ከወረራው በፊት ዎላይታ በፖለቲካው መስክ በራሱ ንጉስ ራሱን በራሱ የሚያስተዳደር ግዛት ነበር። ዎላይታ በኢኮኖሚው በለምነቱና በልምላሜ የሚታወቅ በመሆኑ ዎላይታዎች በምግብ ራሳቸውን ችለው ይተዳደሩ ነበር፡፡

በባህል ደግሞ ዎላይታዎች ድንቅ ባህልና ቅርስ አንዲሁም የራሳቸው የእምነት ተቋማት ነበራቸው፡፡ ዎላይታዎች እጅግ በጣም በጀግንት የአቢሲኒያ ወታደሮች ስለተቋቋሙ ንጉሳቸውን ጦና በቀላሉ ለመያዝ አልተቻለም፡፡
በስነ ልቦና ዎላይታዎች ደስተኞች፣ በራስ የሚተማመኑ፣ ጀግና ተዋጊዎች፣ ስትራቴጂስቶች፣ ጠቢባን… እንደነበሩ እንመለከታለን፡፡

በክፍል አንድ ዎላይታ ከምኒክ ወረራ በፊት ምን ትመስል እንደነበር ተመልክተናል፡፡ በዚህ ክፍል የምኒልክ የዎላይታ ዘመቻ ሂደት ምን እንደሚመስልና የዎላይታ አጎራባች ግዛቶች አቀባበል በተመለከተ ተቀንጭቦ ቀርቧል፡፡ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የታሪክ ጥንቅር ላይ፦ ትርጉሙ ከዚህ በታች ቀርቧል መልካም ንባብ!

የምኒልክ የዎላይታ ዘመቻ ሂደትና የዎላይታ አጎራባች ግዛቶች አቀባበል ድፍን ሶስት ወራት ለዘመቻው ከፍተኛ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቶ የጉዞ ቀን ህዳር መጀመሪያ አካባቢ መሆኑ ገልጽ እየሆነ መጣ፡፡ አዲስ አበባ ካለወትሮ በበለጠ ሽር ጉድ በዛ፡፡ ከንጉሱ ጋር እንዲሄዱ የተጠሩት ጀኔራሎች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ፡፡ በጣም የተጠበቀውና ከሁሉም የላቀ እና ከራሱ ሰዎች ጋር 10000 (አስር ሺህ) ሰራዊት እንዲመራ የተመረጠ ራስ ሚካኤል ነው፡፡

ራስ ሚካኤል የጦር መሪ፣ የወሎ ኦሮሞች አገር ገዢ፣ የንጉስ ምኒልክ አማች፣ ደግሞም ሙስሊም፣ ታላቅ የባሪያ ውጪ ላኪ ነጋዴ፣ የሰበአዊ ፍጡርን በተከታታይ በኮንቮይ ወደ ቀይ ባህር ጠረፍ ከወሰደ በኋላ በእንግሊዝ ወይም በቱርክ መርከቦች አማካይነት ወደ የመን የሚልክ ነው፡፡ እሱ መጨረሻ ላይ ህዳር 1 ደረሰ፡፡

በሁለተኛው ቀን ማለቂያ የሌለው ጉዞ በሰልፍ ተጀመረ፡፡ ሴቶች በእግራቸው መጠጥ በገምቦ በጀርባቸው አዝለው፣ ማር ወይም ቅቤ ተሸክመው ከብቶችንና በጎችን እየነዱ ወደ መጀመሪያው ካምፕ አመሩ፡፡ በንግስት ጣይቱና በታላላቅ የቤተመነግስት አማካሪዎች ግፊት ህዳር 15 ቀን ጉዞ ተጀመረ…

ንጉሱ በሚያልፍባቸው በራሱ ግዛት የሚኖሩ አገረ-ገዢዎች ሁሉ ለንጉሱና ለሰራዊቱ ግብር እንዲያዘጋጁ አስቀድሞ ተነግሯቸዋል፡፡በኢትዮጵያ መንገዶች የሚሰሩት በሰው ጉልበት ነው፡፡ ይሄውም በደሃ ገበሬዎች ጉልበት (እጅ) ነው፡፡ እንጨቶችን ይቖርጣሉ፤ ግንዶችን ይነቅላሉ፣ ያቃጥላሉ፣ ወንዞችን ይሞላሉ፣ አፈር ይደለድላሉ፡፡ በጠላቱ (በወላሞ) አገር ግን ይህ ሁሉ የተከናወነው በራሱ በንጉሱ ወታደሮች ሲሆን በንጉሱ ጥብቅ ቁጥጥር ነበር፡፡

ይህን እስኪከወን ድረስ ለብዙ ሰአታት የጉዞአችን መስተጓጎል ግድ ነበር፡፡ እያንዳንዱ የስራ ድርሻውን ይወጣ ነበር፡፡ ይሄውም ድንጋይ ማንከባለል፣ የተቆረጡ እንጨቶችን መጎተት፣ የሳር ክምሮችን ወይም አፈር ማንሳት ሲሆን ንጉሱ በምሳሌነት ያሳዩ ነበር…

እያንዳንዱ የጦር መሪ እጅግ ብዙ ወታደሮችን ጋሻ አቀባዮችንና ለጌታው አስፈላጊ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን የተሸከሙትን፣ በቀላል ምግቦች የተሞሉ አገልግሎችንና መጠጥ የያዙ ገንቦዎችን ሁሉም በጨርቅ የተሸፈኑትን አስይዞ አስከትሏል፡፡

ሰራዊቱ ስርአት ያጣና ስነ ምግባር የጎደለው ነበር፡፡ ዓላማቸው በአጠቃላይ አንድ መሆን ነበር፤ ይሄውም አለቆቻቸውን ብሎም ንጉሱን መከተል ነበር፡፡ ይህንን ትዕዛዝ መወጣት ይቸግራቸው ነበር፡፡ ይህ እጅግ ብዙ ህዝብ ጠመንጃ፣ ጦር፣ ዱላ፣ ጋሻ፣ የድንኳን ማቆሚያ ዋልታዎች የተሸከመው ሲሆን አብዛኛዎቹም ፈረሳቸውን እየጎተቱ ይጎርፉ ነበር፡፡

ከዚህም በተጨማሪ እያንዳንዱ ወታደር ፈረሰኛ ወይንም እግረኛ በቀኝ ትከሻው ረጅም ከባድና በጣም ሹል ቆልመም ያለ ሰይፍ ከቆዳ በተሰፋ ሰገባ መያዝ ግድ ነበር…

ዘመቻው ከመጀመሩ በፊት ንጉሱ ለዋና ዋና የጦር ጀኔራሎች በወረራው ወቅት ምን የት እንደሚወር ምድብ ሰጥቷቸው ነበር…አለቆቻቸው በሚያርፉባቸው ቦታዎች ሁሉ ተከታዮቻቸው በፍጥነት መጠለያ መስራት፣ ድንኳን መትከል፣ ትንንሽ ጎጀዎችን በጭራሮ መቀለስና በእንሰት ቅጠል መክደን ነው፡፡

የሴቶች የስራ ድርሻ ግን ወደ ወንዝ መውረድና ውሃ መቅዳት፣ የማገዶ እንጨት መሰብሰብ ነው፡፡ በሰፈርን በሁለት ሰአታት ውስጥ መካከለኛ ከተማ የሚያክል ካምፕ እንደ ማዕበል በሚጎርፍ ሰራዊት ከመቅጽበት ይመሰረታል …

በቀጣዩ ቀን ወደ ጉራጌ ሀገር ገባን፡፡ ጀኔራል ጎቤ የጉራጌ ሀገር ገዢ ንጉሱንና ሰራዊቱን ሊቀበል ወደ ቆንዳሊት ሲመጣ በቅርብ የተወለደ አንበሳ ግልገል ይዞ መጣ፡፡ ወደ አዲስ አበባ ካመጡ በኋላ ንጉሱ ለሚስተር ቺፊንግስ ሰጠው፡፡ እሱ እኔ ፓሪስ ስመለስ ከእኔ ጋር በመርከብ ልኮ የነበረ ቢሆንም በባህር ረጅም ጉዞ ተጎድታ ስለነበረ ጃርዲን ዴስ ፕላንትስ ዙ ከደረሰች ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ሞተች፡፡

እሁድ ቀን ጉዞ ስላልተደረገ ፊታውራሪ ጎቤ ከ600 በላይ የሆኑ አብዛኞቹ ከወገብ በላይ ራቁታቸውን የሆኑ ገበሬዎች ጋር ሰልፍ ካደረገ በኋላ እንጀራ፣ ማር፣ ቅቤ፣ ጠጅ፣ ጥራጥሬ እና ብዙ ከብቶችን እየጎተተ ለንጉሱ አመጣ፡፡ ታላቅ ግብዣም አደረገ፡፡

ቀጥሎ ጫካማ ወደሆነው ማረቆ ግዛት ተሸገርን…. ህዳር 26 ወደ ደጃዝማች በጫት አገር ደረስን፡፡ እሱም የንጉሱ የአጎቱ ልጅ ነው፡፡ የዚህ ግዛት ቄሶች አስደናቂ የሆነውን የሀር ልብስ ለብሰው ንጉሱን በጭፈራና በመዝሙር ተቀበሏቸው፡፡ ደጃዝማቹ 120 በ90 ጫማ ርዝመትና ከፍታ ያለውን ትልቅ ዳስ እንዲሰራ አዞ ቀኑን ሙሉ እየበላን የዋልነውን ምግብ አመጣልን፡፡

በቀጣዩ ቀን ወይሮ ወንዝ ተሻግረን በካንባታ ተራራ ጥግ ባለውና ሰፊ ቦታ በሚሸፍነው ፍል ውሃ አጠገብ ሰፈርን፡፡ ይህ ተራራ በኢትዮጵያ መንግስትና በጠላት (ዎላይታ) መንግስት መካከል የሚገኝ የተፈጥሮ ድንበር ነው፡፡

ህዳር 30… ብዙ ጊዜዎቻችንን ያጠፋው ዎላይታዎች የቆፈሩትንና በከባድ ጎርፍ የተቦረቦሩ ጉድጓዶችን መሙላት ነበር፡፡ በመጨረሻ ለጥ ያለና ሜዳማ ወደ ሆነው ቆርጋ ላይ ደረስን፡፡ ይህ ቦታ ቀድሞ በዎላይታዎችና በአቢሲኒያ መካከል በርካታ ውጊያዎች የተደረገበትና በተዳጋጋሚ የአቢሲኒያ ወታደሮች ተሸንፈው የተመለሱበት ቦታ ነው፡፡

ዘረፋ፣ ወረራ በዎላይታ አገር እና የዘመቻው ፍጻሜ በኋላም ወደ አዲስ አበባ መልስ ቀጥሎም ከአዲስ አበባ በረሃውን አቋርጬ ወደ ጅቡቲ ያደረግሁት ጉዞ ታህሳስ 1 ቀን ከስድስት ሰአታት አሰልቺ ጉዞ በኋላ መሃል ጠላት ሀገር (ዎላይታ) ገብተን ካምፓችንን ተከልን፡፡

የራስ ሚካኤል ቀዳሚው ሰራዊት አስቀድሞ የተወራሪዎችን ቤት ማቃጠል ጀምሮ ነበር፡፡ በወረራው ጊዜ ንጉሱ በጦር ሜዳ መነጽር ተራራው ላይ ቆመው አሻግረው ይመለከቱ ነበር፡፡ በመጨረሻ ዎላይታ ቆንጦላ /ዳሞት ጋሌ/ደረስን፡፡ ውሃ ሊቀዱ ወንዝ የሚወርዱትን የአቢሲኒያ ሴቶች በጦር የሚያባርሯቸው ሰዎች ታስረው የሀገሩን ስፋት፣ ልማዳቸውን፣ ሐይማኖታቸውን መረጃ በግድ እንዲሰጡ ስለሚደረጉ ህይወታቸውን ለማዳን ሲሉ ተገድደው ይናገሩ ነበር …

ታህሳስ 15 ቀን ንጉሱ በዎላይታ የተገኘው ድል የልብ ልብ ስላገኘ ወረራውን የዎላይታ ድንበርተኛ ወደሆነው ወደ ገሙ (ቦሮዳ) ሀገር ለመቀጠል እቅድ ላይ እያለ የዚህ ሀገር አለቃ በቀጣዩ ቀን መጥቶ ለንጉሱ እጅ ሰጠ፡፡ በዚህን ቀን ምኒልክ የክቡር ዘውድ ደፍቶ በቀጥታ በውጊያ እየተሳተፈ በዊንቺስተሩ በ40 ሜት ርቀት ሆኖ ከረጅም ሳር ውስጥ ራሳቸውን ብቅ ለማድረግ የሚሞክሩትን ጠላቶቹን (ዎላይታዎችን) አነጣጥሮ እየተኮሰ በመግደሉ ደስታው ወሰን አልነበረውም፡፡

…. ይህ ከላይ በዎላይታ ታይምስ ታሪክ ጥንቅር ላይ የቀረበው ጽሁፍ በ1896 ዓ.ም ምኒልክ ዎላይታን ሲወር አብሮት የተጓዘው ፈረንሳዊ ጸሃፊና የአይን ምስክር የነበረው ጀግ ቫንደራሂም /J.G #Vanderhem የዕለት ማስታወሻ ላይ የምኒልክ የዎላይታ ዘመቻ ሂደት ምን እንደሚመስልና የዎላይታ አጎራባች ግዛቶች አቀባበል ምን ይመስል ነበር የሚለው ተቀንጭቦ የቀረበ ሲሆን ስማቸው በምህጻረ ቃል የተገለጸ ዶክተር D.M ከተረጎመው የተወሰደውን ለዛሬ ክፍል ሁለት አቀረብን ….. ክፍል ሶስት ይቀጥላል። በቀጣይ ክፍል ሶስት የምኒልክ ዘመቻ በዎላይታ ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ ኢኮኖሚያዊ ሰብአዊ፣ ቁሳዊና ሞራላዊ ጉዳት እንመለከታለን፡፡ በቅርቡ ይጠብቁ 🙏

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita #KingTONA #Minilik

ማሳሰቢያ፦ የፅሁፉ ዋና አላማ ትውልድ የራሱን ትክክለኛ ታሪክ እንዲያውቅና በተቃራኒው ሌሎች ብሄረሰቦች አባል የሆኑም ከላይ በታሪክ ጥንቅራችን ስላቀረብነው ብሄር ትክክለኛ ማንነት እንዲያውቁ ነው። ይሄው አካሄድ ደግሞ የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚገልጹት በውጤት ሲለካ፦ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ግንባታ ሂደት ላይ የራሱ የሆነ ከፍተኛ የሆነ በጎ ተፅዕኖ ማሳደር ይችላል። ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ- የሚዲያው ከፍተኛ አዘጋጅ