1000031570

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከገቢ የሚገኘውን ገንዘብ አሰራርን ጥሶ ከመዝረፍ ባሻገር ቢሮው ከ45 በላይ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ መቅጠሩ ተነግሯል።

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

የክልሉ ገቢ ቢሮ 88% በላይ ሰራተኞች የአንድ አከባቢ ሰዎች ብቻ እንዲሰሩ በመደረጉ በተለያዩ ዞኖች ላይ ያልተገባ ጫና በመፍጠር ላይ መሆኑንም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ በተጨማሪ በተለይም በዎላይታ ዞን፣ በጌዴኦ የሚገኙ ትላልቅ ድርጅቶች ግብር ከፋይ የሆኑ ባለሀብቶች ላይ ያለአግባብ ጫና በመፍጠር ፋብሪካዎች እንዲዘጉ፣ ባለሀብቶች እንዲታሰሩ እና እንዲሸማቀቁ መደረጉም ተገልጿል።

በክልሉ ከሁሉም መዋቅሮች ከግብር ከፋይ የተሰበሰበ ከፍተኛ ገንዘብ የተለያዩ ህገወጥ ዘዴዎችን በመጠቀም በክልሉ ርዕሰ መስተደድር አማካይነት ወጪ ተደርጎ እንዲወጣ ተደርጎ በኢፍትሃዊነት ለራሳቸው ለሚሉት ጥቅምና ፍላጎት መጠቀሚያነት እያዋሉ ስለመሆኑም የደረሰን ተጨባጭ የስነድ መረጃ ያመለክታል።

በተለይም የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ የስነምግባር ችግር ያለባቸው እንደሆነና የልጇን ባል ሾፌር በማድረግ ጭምር ከማህበረሰቡ እሴት ውጪ ባህሪ የሚያሳዩ እንዲሁም የሌሎች ብሄሮች ሰራተኛ አለአግባብ እንዲባረሩ በውድድርም እንዳይገቡ በማድረግ 88% በላይ ሰራተኞች የአንድ አከባቢ ብቻ እንዲሆኑ በማድረግ በተለያዩ ዞኖች የሚገኙ ግብር ከፋዮች ላይ ያልተገባ ጫና በመፍጠር ላይ እንደምትገኝ አንድ ሁኔታውን በቅርበት የሚከታተል አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተናግረዋል።

ከ 45 በላይ ስራተኞች የቢሮው የሰው ሀብት አመራሮችና ሰራተኞች ሳያውቁ በህገወጥ መንገድ በራሷ ፊርማ ብቻ ቅጥር መፈፀሟንም መረጃው አመላክቷል።

ለማሳያነት ከክልሉ ገቢዮች ቢሮ አመራርን ጨምረው አጠቃላይ 77 ሰራተኞች 88% ጋሞ፣ 6 የዎላይታ ተወላጆች (2 ሾፈሮች እና 4 ተራ ስራተኞች) እንዲሁም የተቀሩ ሰራተኞች 3%  የማይሞሉ ከሌሎች ብሄሮች እንደሆኑ ያገኘነው ተጨባጭ መረጃ ይጠቁማል።

ፌደሬሽን ምክርቤት ባፀደቀው ህግ መሠረት በክልሉ በአንድ አከባቢ የሚገኝ የፈደራል ተቋም ለክልሉ በማሳወቅ ለፌደራል ገቢዎች ከከፈለ በኃላ በፐርሰንት ወደ ተቋሙ ያለበት ዞን የሚላክ “የጋራ ገቢ ህግ” መሠረት መላክ የነበረበትን በርዕሰ መስተዳድሩ ትዕዛዝ ከግማሽ በታች እንዲሆን ማድረጓንና አለግባብ ገንዘቡ በህገወጥ አሰራር ወጪ እየተደረገ ስለመሆኑም ያገኘነው ተጨባጭ መረጃ ያመለክታል።

አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አመራር መረጃ ከሆነ በህጉ መሠረት፦ ከጋራ ገቢ ከፌደራል ለሚመለከታቸው ዞኖች ለክልሉ የተላከውን በቢሊዮን የሚቆጠር ከፍተኛ ገንዘብ አለአግባብ ለአርባምንጭ ስታዲየም ግንባታ፣ ለአደባባይ ግንባታ፣ ለተለያዩ መስተንግዶ፣ ለጋሞ ልማት ማህበር እንዲሁም ለግል ጥቅማቸው እያዋሉ እንደሆነና ኦዲት እንዳይደረግ በርዕሰ መስተዳድሩ ጫና መከልከሉንና እስካሁን ኦዲት ተደርጎ አለማወቁን አስረድተዋል።

በክልሉ ዎላይታ ዞን ከክልል ማዕከል ውጪ ባለው ዕቅድ 60% በመቶ በላይ ይይዛል፣ በ2016 በጀት አመት ዞኑ በክልሉ ከፍተኛ ገቢ ሰብስቧል፣ በዘንድሮው በጀት ዓመት ደግሞ 6.1 ቢሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ በ6 ወር አፈፃፀም ብቻ ከ 3.9 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ በአፈፃፀም ከክልሉ ከፍተኛ አፈጻጸም አሳይቷል፣ በተቃራኒው በዘንድሮ በጀት ዓመት ጋሞ ዞን 5 ቢሊዮን ለመሰብሰብ አቅዶ በስድስት ወር አፈፃፀም 1 ቢሊዮን ብቻ መሰብሰብ መቻሉን ከሪፖርቱ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጧል።

የመንግስት ስራተኞች ደመወዛቸውን በአግባቡ መክፈል እየተቸገሩ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ዞኖች የሚከፍሉትን ግብር ሰብስበው ለሰፈራቸው ልማትና ለግል ጥቅም እያዋሉ የሚገኙ የገቢ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ አለመነሽ ደመቀ በትናንትናው ዕለት በተጠናቀቀው ስብሰባ ላይ ጥብቅ የጥቅም ግንኘነት ያለውን የክልሉን ርዕሰ መስተደድር ገበና ለመሸፈን እንዲሁም በቢሯቸው ከሰሩት ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂነት ለማምለጥ “ዎላይታ ዞን ግብር አይከፍልም” በሚል የውሸት ክስ ማቅረቧን ተከትሎ በርካቶች ቅሬታ እያሰሙ ይገኛሉ።

ለግንዛቤ ያህል፦ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ገንዘብ በፋይናንስ ቢሮ አማካይነት ለሁሉም ዞኖቹ በህጋዊ ቀመሩ መሠረት ገቢ ማድረግ ሲገባው በተቃራኒው ያንን ህጋዊ ቀመር በመጣስ ገንዘብ በክልሉ እንዲቀር በማድረግ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር በመመሳጠር አለአግባብ ወጪ እንዲሆን ያደርጋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው