“ንጹሀን ወገኖችን ያስገ’ደለ የዎላይታ ብቻ ሳይሆን የሲዳማ ጠላት ነው፣ ለሲዳማ ጠላት የለውም ጠላቱ አቶ አብርሃም ነዉ” – የሲዳማ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን
“በዛሬው ዕለት የሲዳማ ክልል አመራሮች መድረክ ተጀምሯል። በቀድሞዉ የደኢህዴን አዳራሽ ዉስጥ። ርዕሱ ደግሞ የክልሉ የ6 ወራት የድርጅት እና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸምና ወቅታዊ ጉዳዮችን መገምገም ይላል። የተጀመረው ደግሞ ቦና ወረዳ በመኪና አደጋ ህይወታቸው ላጡ ወገኖች የህሊና ጸሎት በማድረግ ነዉ” ስሉ አንድ የመድረኩ ተሳታፊ ከፍተኛ ባለስልጣን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ያደረሰው መረጃ ያመለክታል።

ወደ ሰነዱ ይዘት ሳይገባ አስቀድሞ “ወቅታዊ ሁኔታዎች” ላይ የጋራ አቋም መያዝ አለብን በማለት በሁለት ሀሳቦች ላይ አስቀድሞ ዉይይት ተደርጎ እንደነበር አስረድተዋል።
“ባለፈው ሳምንት ቦና ወረዳ በተፈጠረውና ከ71 ሰዎች በላይ ህይወት የቀጠፈው የትራፊክ አደጋ በተመለከተ “ክልሉ ዝምታ መርጧል፣ ክልላዊ ሀዘን ማወጅ አለበት ተብሎ የሚናፈሰዉ ነገር ዉጪና ሀገር ዉስጥ የሚገኙ ጥገኞች የሚያናፍሱት ወሬና የፖለቲካ ቁማር ስለሆነ አስፈላጊ ምላሽ መስጠት አለብን፣ ፕሬዝዳንቱ ጭምር ሄዶ አስቀብ አጽናንቷል፣ የድጋፍ አካዉንት ተከፍቶ ድጋፍ እየተደረገ ነዉ” የሚል ሀሳብም መነሳቱን አክለዋል።
በመድረኩ በሎካ አባያ ከዎላይታ ድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ጉዳይ ክልሉ ለምን መግለጫ አልሰጠም? የተፈጠረዉ ነገር ምንድነው ብሎ የሚጠይቅ ሰዉ መኖሩ ተገቢ ቢሆንም ከአቶ አብርሃም ጋር አያይዞ የዉስጥ ባንዳ ከዎላይታ ጠላቶች ጋር በማበር ጓዱን ከስልጣን መነቅነቅ ስለ ጀመሩ አመራሮች በአንድ አቋም መታገል አለባችሁ” በሚል አንድ አመራር አስተያየት መስጠቱን ተናግረዋል።
አክለውም “ይህ ነገር ሰፍቶ እስከ ፓርቲው ዋና ቢሮ ከደረሰ ጓዳችንን ልናጣው እንችላለን የሚል ሀሳብ በአስተባባሪ ኮሚቴ ቀርቦ አንዳንድ አመራሮች “የዎላይታ አክቲቪስቶች በማስረጃ ነዉ እየታገሉ ያሉት፣ ለኢንቬስትመንት የተሰጡ መሬቶችን በዞኑ በኩል እንደተሰጠ ጭምር በቂ መረጃ እያቀረቡ ነዉና በእኛ በኩል ምን አለ” የሚሉና ከአብርሃም፣ ከአባቱና ዘመድ አዝማዱ ጋር ተያይዞ በሎካ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ ሄክታሮችን በጸጥታ ሀይል ጭምር በመታገዝ እየተወረረ ነዉ የሚል ወሬ በህዝቡ ዉስጥ እየሰፋ ነዉና ሀሳቡን የመመከት ስራ መስራት አለብን” በሚል አመራሩ የድጋፍ አስተያየት መስጠቱንም የመረጃ ምንጫችን አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም እኚህ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ሰጪ አመራር፦ “አቶ አብርሃም ማርሻሎ ይህንን የሚፈጽሙት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን (ይርጋለም ዞን) የሰላም፣ ጸጥታና መልካም አስተዳደር መምሪያ ሀላፊ አድርጎ ባስቀመጠው በወንድሙ አማካኝነት በወታደር ጭምር ታግዞ ነዉ የሚል ወቀሳ በተጨባጭ የቀረበ ስሆን፣ ይህንን ችግር ሌላ ጊዜ በራሳችን መድረክ እናየዋለን አሁን ግን ለጠላታችን መጠቀሚያ ሳንሆን ከጓዱ ጋር መቆም አለብን፣ ሁሉም አመራር በአጠቃላይ ከአብርሃም ጎን እንደሆነ በማሳወቅ በዎላይታ በኩል የሚመጣዉን ጫና በተደራጀ መልኩ በፌስቡክ ዘመቻ፣ በሚዲያ ሰራዊት እንምራ በሚል ማሳሰቢያ ተዘግቶ ወደ ሰነዱ ንባብ እንደተገባ አንድ የስብሰባው ተሳታፊ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የገለፁት።
በአቶ አብርሃም ጉዳይ ላይ በሚነሳው አጀንዳ ላይ በመድረክ ከአብርሃም ጋር የነበሩት የክልሉ ፕረዚዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ አንድም አስተያየት ያልሰጡ ሲሆን ስለ ቦና የትራፊክ አደጋ በተመለከተ በመፍትሔውና ጉዳት የደረሰባቸው ቤተሰብን በዘላቂነት ማጋዝ በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ በስፋት እንደተናገሩም የመረጃ ምንጫችን ጠቁመዋል።
የመድረኩን መረጃ ያደረሱት እኚሁ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን ስለ አቶ አብራሃም ሲገልፁ፦ “የማዕከላዊ ዞን የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ኢሳያስ ማርሻሎ (የአብርሃም ወንድም) ሎካ አባያ የሚገኘው በዚሁ ዞን ነዉ፥ በተደራጀ መልኩ ነዉ ሲዳማንም ዎላይታንም እየበደሉ ያሉት። ወንድሙን በመሾሙ ምክንያት ህዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ ቁጣ አስነስቶ ነበር” ብለዋል።

ባለስልጣኑ አክለውም፦ “በወንድሙ ትዕዛዝ መሰረት በሎካ ድንበር ንጹሀን ዎላይታዎችን ያስገ’ደለ የዎላይታ ብቻ ሳይሆን የሲዳማ ጠላት ነው፣ ለሲዳማ የህዝብ ጠላት የለውም ጠላቱ አቶ አብርሃም ነዉ። ለዎላይታ የህዝብ ጠላት የለውም ጠላቱ አብርሃምና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከእርሱ ጋር የተባበሩ አመራሮች ናቸው። አቶ አብርሃም የህዝብ ንቀቱ ጫፍ (ወንድሙን ከወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኝነት ቀጥታ የዞን ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አድርጎ በወታደር ሀይል የህዝብን መሬት እየወረረ ይገኛል” በሚል ገልጸዋል።
በመጨረሻም እኚሁ የመረጃ ምንጭ ባለስልጣን፦ “የሚገርመው አንድ የአቶ አብራሃም ደጋፊ ዘመድ የሆነ አመራር በዛሬው ስብሰባ የዎላይታ አክቲቪስቶች አብርሃም ላይ ሲዘምቱ በሲዳማ ዉስጥ የሚገኙ የወላይታ ተወላጆችን ቀብድ አስይዘው ነዉ የሚል አይነት እንድምታ ያለው ንግግር እየተናገሩ እንደ ነዉር እንኳን አይቆጠርም። ለአንድ ሌባ ሙሰኛ ስልጣን ማስጠበቂያ ሲባል ያን ያህል መላላጥና መጋጋጥ አሳፋሪ ነው ገዢው ፓርቲ በእነዚህ በወንድማማች ህዝቦች መካከል እሳት በሚጨምሩት ላይ ተገቢ እርምጃ እንዲወስድ ተደራጅተን እየተንቀሳቀስን ነው” ብለዋል።
እንደሚታወቀው አቶ በላይነህ ክንዴ እና ዳኜ ዳባ የተባሉ ባለሀብት ግለሰቦች ከፍተኛ የመንግስት አመራር ጋር በመመሳጠር በዎላይታና ሲዳማ አዋሳኝ አከባቢ የሰው ህይወት የጠፋበት ግጭት እንዲከሰት ቀጥታ ድጋፍ ማድረጋቸውን ባለው ሳምንት የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተጨባጭ መረጃዎችን አስደግፎ መዘገቡ ይታወሳል።
በአከባቢው ለሚፈጠረው የፀጥታ ችግርና የመሬት ወረራ ዋናው መንግስታዊ ድጋፍ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ እጅአዙር ድጋፍ እንደሆነም ምንጮቻችን ጠቅሰን ዘግበን ነበር።
በተጨማሪም የብልጽግና ከፍተኛ አመራሩ የራሱንና የቡድኑን ጥቅም ለማስጠበቅ ከዚህ በፊት የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳደሪ በነበረበት ወቅት ታጣቂዎችን ወደ አባያ ብላቴ እያስገባ ቀጠናውን ውጥረት እንዲነግስ እና ለዘመናት ተዋልዶ ተጋምዶ የኖሩ የሲዳማ እና ዎላይታ ሕዝብ ደም እንዲቃቡ ያደረገ እና እያደረገ የሚገኝ ግለሰብ መሆኑም እንዲሁም።
በተፈጠረው የተደራጀ የግጭት ጠመቃ ዎላይታ በኩል ሶስት የአከባቢው ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል የሚገኙ ቢሆንም እስካሁን የክልሉን ህዝብ ከጥቃት የመከላከል ግዴታ ያለበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታ መምረጡ ተጨማሪ ስጋት እንደፈጠረባቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ቅሬታ ገልጿል።
እስካሁን የክልሉን ህዝብ ከጥቃት የመከላከል ኃላፊነት ከመወጣት በተቃራኒው በእጅአዙር ድጋፍ በመስጠት የተባበረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታ የመረጠ ሲሆን በተፈጠረው በተደራጀ የግጭት ጠመቃ ዎላይታ በኩል ሶስት የአከባቢው ወጣቶች ተገድለዋል፣ በርካቶች ቆስለው ጤና ተቋማት ላይ ህክምና እየተከታተሉ ሲሆን ተጨማሪ የሰው ህይወት ሳይጠፋ የሚመለከተው አካል ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #Wolaita #Sidama
በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው