1000032441

አደጋ ለደረሰባቸው ወገኖች የተሰበሰበው ሀብት ለተጎጂዎች ሳይደርስ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አመራሮች መሰወሩ ተነገረ

በአሳዛኝ ክስተት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡትን፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ለማገዝና ለማማቋቋም ተብሎ ከሀገር ውስጥ እስክ የውጭ ሀገራት እንዲሁም ግለሰቦች ከተለያዩ ቦታዎች ከ600 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ የተሰበሰበ ቢሆንም ገንዘቡ ለተጎጂዎች ሳይደርስ በክልሉና በአከባቢው ባለስልጣናት መሰወሩን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደረሰው ተጨባጭ መረጃ ያመለክታል።

እንደመረጃው ከሆነ “በክልሉ የማዕድን ሀብት ከመስረቅ ጋር ስማቸው በተደጋጋሚ በመነሳት የሚታወቁት የክልሉ ምክትል ርዕሠ መሰተዳድር ማዕረግ የክልሉ ውሃ ቢሮ ኃላፊ አቶ አክሊሉ አዳኝ የክልሉ አደጋ ስራ አመራር ኮሚኒዩኬሽን አቶ ጋንታ ጋምኣ በጋራ በመሆን በአርባምንጭ ፓራዳይዝ ሆቴል ሆኖ ከርዕሰ መስተዳድሩ ጋር በመሆን የተጎጂዎችን ሀብት የማሸሽ ስራ ሰርቶዋል” ብለዋል።

እነኚህ በመሬት ናዳ የተፈናቀሉ ወገኖች አሁን በዚህ ሰዓት ከ500 በላይ ህዝብ በላስትክ በቶች በተጠለሉበት ምግብ ውሀ በለለት በራሀብና በችግር ይሰቃያሉ። ከተጎዎቹ የጉልበት ስራ መስራት የሚችሉት ወደ ሳውላ ከተማና ወደ አጎራባች ወረዳዎች በመሰደድ ላይ መሆናቸውንም የመረጃ ምንጭ ጠቁመዋል።

“በአከባቢው እስካሁን የአክሊሉ አዳኝ እና የጥላሁን ከበደ ቅጥረኛ ሙሰኞች የትኛው ሚዲያ እንዳይደርስ እና እንዳያገኛቸው ቀን ቀን ካሉበት ላስትክ ቤት በማውጣት ህዝቡን ጫካ ውስጥ እየደበቁ ናቸው” በማለትም ገልጸዋል።

“በአደጋው ሰዓት ዓለም ሁሉ ከጎናችን ነበር፥ ተጎጅዎችን መልሶ ለማቋቋምም በጥሬ ገንዘብ ብዙ ሚሊዮን ብሮች እና በቁሳቁስና በዓይነትም ለመገመት የሚያዳግት መጠን ያለው ሀብት ተሰብስቧል፤ በስተመጨረሻም ለተጎጅዎች የሚሰሩ 200 መጠለያዎች በዞኑ ለሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ተከፋፍለው እንደተሰጡና በዋናነት በመዋቅሮቹ እየተገነቡ ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም “ቤቶች ተገንብተው እንዳለቁ ተደርጎ በዞኑ አስተዳደርና በገነቡ መዋቅሮች መካከል የእርክብክ ስነ-ሥርዓት የተከናወነ ቢሆንም አሁን ላይ በስፍራው የተገነቡ ቤቶች የእንጨት ቤቶች ሆነው በብዛት ጭቃ ያልተመረጉ ናቸው፤ ለተማሪዎች መማሪያ ክፍል ተብለው የተሰሩ ክፍሎችም የእንጨት ቤትና በአግባቡ ጭቃ ያልተመረጉ ናቸው፡፡ በአደጋው የተፈናቀሉ ወገኖችም ቁጥር በአባወራ መጠን ከ1000 ላይበልጥ ይችላል፡፡ ይህ ማለት ወደ ግማሽ የሚሆን ሰው በሸራ በተወጠረ ዳስ ውስጥ ሆኖ የመከራ ኑሮ እየገፋ ነው ማለት ነው” ብለዋል።

“በአጠቃላይ ይህንን ያህል ሰው ሜዳ ላይ ከተጣለ፤ የተሰሩ ቤቶችም የእንጨት ቤትና በአግባቡ ጭቃ እንኳን ያልተመረጉ ከሆነ፤ አከባቢው ንፁህ የመጠጥ ወሃና መብራት እንኳን ያላገኘ ከሆነ፤ ትምርት ቤት ተብሎ የተሰራው ዳስ እንጨቶች ብቻ የቆሙበትና በቂ የተማሪ ወንበር እንኳን የለላቸው ከሆኑ፤ የተሰበሰበው ገንዘብና ንብረት የት እንደገባ በአፋጣኝ ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ መደረግ አለበት” በሚልም ጉዳዩን በቅርበት የተከታተለና ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ገልጸዋል።

አመራሩ አክለውም “ገንዘቡ ሲሰበሰብ በአንድ ቋት መሆን ሲገባው ክልሉ ለላ አካውንት፣ ዞኑ ሌላ አካውንት፣ ወረዳውም ለተወሰኑ ቀናቶች የራሱን አካውንት ከፍቶ በተለያዬ አድራሻ የተሰበሰበው ገንዘብ የት እንደገባ መጣራት አለበት፤ ሌብነትና ዘረፋ ውስጥ የገቡ አመራሮች ካሉም በአፋጣኝ ተጣርቶ በህግ ሊጠየቁና ውጤቱ ለህዝብም ይፋ መደረግ አለበት፥ ከህዝብ ለቅሶ ሳቅ አይዘረፍም!!! ይህ የዘመናችን ነውረኛ ተግባር ነው!! በጎፋዎችም ማሾ!! ማሾ!!! ይባላል” ብለዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Gofa