ከፍተኛ አመራሩ በአባታቸው ስም ከ120 ሄክታር መሬት በላይ ቢወስዱም ተጨማሪ ለማግኘት በአከባቢው የተደራጀ ህገወጥ ወረራ እየፈጸመ ስለመሆኑ ተነገረ።
“የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አብርሃም ማርሻሎ ከሎካ አባያ ወረዳ በ2012 በአባታቸው አቶ ማርሻሎ ኢቲሶ ስም 120 ሄክታር መሬት ለኢንቨስትመንት የወሰዱ ሲሆን በጊዜው በህገውጥ መንገድ ነበር ያንን መሬት ለኢንቨስትመንት የወሰዱት አቶ አብርሃም ማርሻሎ የራሳቸውን ቤተሰብ በማደራጀት በመላው ሲዳማ ውስጥ የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች ላይ ብቻ በአከባቢው ተወላጆቹ ላይም ያለ ርህራሄ የጭካኔ የሌብነት በትሩን እያሳረፈ ይገኛል” በሚል ለደህንነታቸው ስም እንዳይጠቀስ የፈለጉ የክልሉ ከፍተኛ አመራር ገልጸዋል።

በተጨማሪም በክልሉ በዚሁ አመራር አማካይነት “በክስ ሂደት ላይ ያሉ የመሬት ጉዳዬችን ሰነዶችን ጭምር በማጥፋት ባደራጁት ቡድን በሐዋሳ እና አከባቢው ከተሞች ውስጥ ያሉ መሬቶች በህገወጥ በንግድ ለህግ ጥቅም እያዋሉ ታሪክ የማይረሳው በደል በህዝባችንን ላይ እየፈፀመ ነው፣ በአከባቢው የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦችን በማሸማቀቅ ጭምር እየተንቀሳቀሱ ስለሆነ ጉዳዩን የሚመለከተው አካል በትኩረት ማየት አለበት” ብለዋል።


ባለፈው ሰምንት በተካሄደው የሲዳማ ክልል አመራሮች መድረክ በሎካ አባያ ከዎላይታ ድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ጉዳይ ክልሉ ለምን መግለጫ አልሰጠም? የተፈጠረዉ ነገር ምንድነው ብሎ የሚጠይቅ ሰዉ መኖሩ ተገቢ ቢሆንም ከአቶ አብርሃም ጋር አያይዞ የዉስጥ ባንዳ ከዎላይታ ጠላቶች ጋር በማበር ጓዱን ከስልጣን መነቅነቅ ስለ ጀመሩ አመራሮች በአንድ አቋም መታገል አለባችሁ” በሚል አንድ አመራር አስተያየት መስጠቱን የመድረኩ ተሳታፊ ከፍተኛ ባለስልጣን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መረጃውን አጋርተው ነበር።
አክለውም “ይህ ነገር ሰፍቶ እስከ ፓርቲው ዋና ቢሮ ከደረሰ ጓዳችንን ልናጣው እንችላለን የሚል ሀሳብ በአስተባባሪ ኮሚቴ ቀርቦ አንዳንድ አመራሮች “የዎላይታ አክቲቪስቶች በማስረጃ ነዉ እየታገሉ ያሉት፣ ለኢንቬስትመንት የተሰጡ መሬቶችን በዞኑ በኩል እንደተሰጠ ጭምር በቂ መረጃ እያቀረቡ ነዉና በእኛ በኩል ምን አለ” የሚሉና ከአብርሃም፣ ከአባቱና ዘመድ አዝማዱ ጋር ተያይዞ በሎካ ወረዳ በሺዎች የሚቆጠሩ ሄክታሮችን በጸጥታ ሀይል ጭምር በመታገዝ እየተወረረ ነዉ የሚል ወሬ በህዝቡ ዉስጥ እየሰፋ ነዉና ሀሳቡን የመመከት ስራ መስራት አለብን” በሚል አመራሩ የድጋፍ አስተያየት መስጠቱንም የመረጃ ምንጫችን አረጋግጠዋል።
እኚህ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ሰጪ አመራር አክለውም፦ “አቶ አብርሃም ማርሻሎ ይህንን የሚፈጽሙት በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን (ይርጋለም ዞን) የሰላም፣ ጸጥታና መልካም አስተዳደር መምሪያ ሀላፊ አድርጎ ባስቀመጠው በወንድሙ አማካኝነት በወታደር ጭምር ታግዞ ነዉ የሚል ወቀሳ በተጨባጭ የቀረበ ስሆን፣ ይህንን ችግር ሌላ ጊዜ በራሳችን መድረክ እናየዋለን አሁን ግን ለጠላታችን መጠቀሚያ ሳንሆን ከጓዱ ጋር መቆም አለብን፣ ሁሉም አመራር በአጠቃላይ ከአብርሃም ጎን እንደሆነ በማሳወቅ በዎላይታ በኩል የሚመጣዉን ጫና በተደራጀ መልኩ በፌስቡክ ዘመቻ፣ በሚዲያ ሰራዊት እንምራ በሚል ማሳሰቢያ ተዘግቶ ወደ ሰነዱ ንባብ እንደተገባ አንድ የስብሰባው ተሳታፊ አመራር ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የገለፁት።
የመድረኩን መረጃ ያደረሱት እኚሁ የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን ስለ አቶ አብራሃም ሲገልፁ፦ “የማዕከላዊ ዞን የሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ኢሳያስ ማርሻሎ (የአብርሃም ወንድም) ሎካ አባያ የሚገኘው በዚሁ ዞን ነዉ፥ በተደራጀ መልኩ ነዉ ሲዳማንም ዎላይታንም እየበደሉ ያሉት። ወንድሙን በመሾሙ ምክንያት ህዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ ቁጣ አስነስቶ ነበር” ብለዋል።
ባለስልጣኑ አክለውም፦ “በወንድሙ ትዕዛዝ መሰረት በሎካ ድንበር ንጹሀን ዎላይታዎችን ያስገ’ደለ የዎላይታ ብቻ ሳይሆን የሲዳማ ጠላት ነው፣ ለሲዳማ የህዝብ ጠላት የለውም ጠላቱ አቶ አብርሃም ነዉ። ለዎላይታ የህዝብ ጠላት የለውም ጠላቱ አብርሃምና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከእርሱ ጋር የተባበሩ አመራሮች ናቸው። አቶ አብርሃም የህዝብ ንቀቱ ጫፍ ወንድሙን ከወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኝነት ቀጥታ የዞን ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አድርጎ በወታደር ሀይል የህዝብን መሬት እየወረረ ይገኛል” በሚል ገልፀው ነበር።
በመጨረሻም እኚሁ የመረጃ ምንጭ ባለስልጣን፦ “የሚገርመው አንድ የአቶ አብራሃም ደጋፊ ዘመድ የሆነ አመራር በዕለቱ ስብሰባ የዎላይታ አክቲቪስቶች አብርሃም ላይ ሲዘምቱ በሲዳማ ዉስጥ የሚገኙ የዎላይታ ተወላጆችን ቀብድ አስይዘው ነዉ የሚል አይነት እንድምታ ያለው ንግግር እየተናገሩ እንደ ነዉር እንኳን አይቆጠርም። ለአንድ ሌባ ሙሰኛ ስልጣን ማስጠበቂያ ሲባል ያን ያህል መላላጥና መጋጋጥ አሳፋሪ ነው ገዢው ፓርቲ በእነዚህ በወንድማማች ህዝቦች መካከል እሳት በሚጨምሩት ላይ ተገቢ እርምጃ እንዲወስድ ተደራጅተን እየተንቀሳቀስን ነው” ብለዋል።
እንደሚታወቀው አቶ በላይነህ ክንዴ እና ዳኜ ዳባ የተባሉ ባለሀብት ግለሰቦች ከፍተኛ የመንግስት አመራር ጋር በመመሳጠር በዎላይታና ሲዳማ አዋሳኝ አከባቢ የሰው ህይወት የጠፋበት ግጭት እንዲከሰት ቀጥታ ድጋፍ ማድረጋቸውን ባለው ሳምንት የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ተጨባጭ መረጃዎችን አስደግፎ መዘገቡ ይታወሳል።
በአከባቢው ለሚፈጠረው የፀጥታ ችግርና የመሬት ወረራ ዋናው መንግስታዊ ድጋፍ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ አባል እና የሲዳማ ክልል ብልጽግና ፓ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እንዲሁም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕረዚዳንት አቶ ጥላሁን ከበደ እጅአዙር ድጋፍ እንደሆነም ምንጮቻችን ጠቅሰን ዘግበን ነበር።
በተጨማሪም “የብልጽግና ከፍተኛ አመራር አቶ አብራሃም ማርሻሎ የራሳቸውንና የቡድኑን ጥቅም ለማስጠበቅ ከዚህ በፊት የሎካ አባያ ወረዳ አስተዳደሪ በነበረበት ወቅት ታጣቂዎችን ወደ አባያ ብላቴ እያስገባ ቀጠናውን ውጥረት እንዲነግስ እና ለዘመናት ተዋልዶ ተጋምዶ የኖሩ የሲዳማ እና ዎላይታ ሕዝብ ደም እንዲቃቡ ያደረገ እና እያደረገ የሚገኝ ግለሰብ” መሆኑም እንዲሁ።
ሰሞኑን በተፈጠረው የተደራጀ የግጭት ጠመቃ ዎላይታ በኩል ሶስት የአከባቢው ወጣቶች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ላይ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሆስፒታል የሚገኙ ቢሆንም እስካሁን የክልሉን ህዝብ ከጥቃት የመከላከል ግዴታ ያለበት በተቃራኒው በእጅአዙር ድጋፍ በመስጠት የተባበረው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጉዳዩ ዙሪያ ጥፋተኞች ወደ ፍትህ እንዲቀርቡ ከመናገር ዝምታ መምረጡ ተጨማሪ ስጋት እንደፈጠረባቸው የአከባቢው ነዋሪዎች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ቅሬታ ገልጿል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏