1000033543

አፍሪካ ዋና ዋና እንቅፋቶቿንና ዕድሎቿን በመለየት መፍትሔ ለማመንጨት በዓላማና በእውቀት የሚመሩ መሪዎችን ማፍራት ወሳኝ እንደሆነ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናግረዋል።

በመላው አፍሪካ ያሉ የአስተዳደር፣ የአመራር እና የፖሊሲ ጉድለቶችን መፍታትን አላማ ያደረገው የመጀመሪያው ተቋም በቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና በሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ አማካይነት ተቋቋመው ወደ ተግባር መግባቱ ተገልጿል።

የአፍሪካ የአስተዳደር ትምህርት ቤት (ASG)፣ በሕዝብ ፖሊሲ፣ በምርምር፣ በአስተዳደር፣ በአመራር እና በአስተዳደር ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት መርሃ ግብሮችን ለማቅረብና ለመንደፍ ጥር 14 ቀን 2025 በሩዋንዳ በይፋ እንቅስቃሴውን መጀመሩ ተገልጿል።

ይሄንን በመላው አፍሪካ ያሉ የአስተዳደር፣ የአመራር እና የፖሊሲ ጉድለቶችን መፍታትን አላማ ያደረገውንና በአፍሪካ የመጀመሪያው ተቋም የሆነውን የመሰረቱት የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ እና የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ሲሆኑ በሩዋንዳ በሚገኘው ካምፓስ የአፍሪካ የአስተዳደር ትምህርት ማዕከል (ASG) በአፍሪካ አህጉር የወደፊት መሪዎችን ለማፍራት በፖሊሲ፣ በምርምር፣ በአስተዳደር፣ በአመራር እና በአስተዳደር አለም አቀፍ ደረጃ የተመረጡ ፕሮግራሞችን ከሁሉም አፍሪካ ሀገራት ለተመረጡ ተማሪዎች ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የወቅቱ AGRA የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተቋቋመው ተቋም የአፍሪካ ልዩ እውቀቶችን ከአለም አቀፋዊ ምርጥ ተሞክሮዎች ጋር በማዋሃድ የአህጉሪቱን ዋና ዋና ተግዳሮቶችና ዕድሎች ለመቅረፍ በዓላማ የሚመሩ መሪዎችን ለማፍራት ማዕከል ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።

“አፍሪካ ታላቅነቷን ለማስመለስ የመጀመሪያው እርምጃ የታሪኳን፣ የፖለቲካ ኢኮኖሚዋን እና የአመራርነት አስተሳሰቦችን በመሪዎቿ ውስጥ ግንዛቤ እና እውቀት በመገንባት ነው፥ ከዚያ ጠንካራ መሰረት በመነሳት መሪዎች የአፍሪካን ጉዞ ሊቀርጹ ይችላሉ” ሲሉም አቶ ኃይለማርያም ተናግረዋል።

የሩዋንዳ የትምህርት ሚኒስትር የሆኑት ጆሴፍ ንሴንጊማና በበኩላቸው The African School of Governance (ASG) ለአፍሪካውያን ወደፊት የላቀ አመራር በማፍራት ወደ ዕድገት የመምራት አቅም እንዳለው እንዲሁም በአለምአቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ ጠቁመዋል።

በዝግጅቱ ላይ የኤኤስጂ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ኪንግስሊ ሞጓሉ እንዳሉት “ተቋሙ በአፍሪካ እውነታዎች ላይ የተመሰረተ ዘላቂ የአስተዳደር ሞዴል ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ በማብራራት ASG እውቅና ያለው የፓን አፍሪካ ድህረ ምረቃ-ደረጃ ተቋም በአፍሪካ ያለውን የአስተዳደር ለውጥ መፍትሄዎችን ለመምጣት ቁርጠኛ ነው” ብለዋል።

የአፍሪካ የአስተዳደር ትምህርት ማዕከል በ16 ኦክቶበር 2024 የጀመረ የድህረ ምረቃ ተቋም ሲሆን ካምፓሱ በኪጋሊ፣ ሩዋንዳ የሚገኝና በአፍሪካ አህጉር የወደፊት መሪዎችን ለማፍራት በማቀድ በፖሊሲ፣ በምርምር፣ በአስተዳደር፣ በአመራር እና በአስተዳደር አለም አቀፍ ደረጃ የተመረጡ ፕሮግራሞችን ለማቅረብ አልሞ የተቋቋመ ነው።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #Rwanda #Africa #ASG #AGRA