የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒታል ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ገፈፋ እና የዓይን ህክምና ከአሜሪካ በመጡ ስፔሻሊስቶች ጋር በመተባበር ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ይሰጣል።

የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒታል ዓይን ህክምና ማዕከል ከ Himalia Cataract Project (HCP) ከተሰኘው ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከቀን 27/07/13 እስከ 01/08/13 ዓ.ም ለአራት ተከታታይ ቀናት ህክምናውን የሚሰጥ መሆኑን የዎ.ሶ.ዩ ማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒታል የዓይን ህክምና ክፍል አስተባባሪ አቶ መልካሙ ኮራቶ ገልጸዋል፡፡

ህክምናውን የሆስፒታሉ ዓይን ህክምና ስፔሻሊስት ሃኪሞች ከአሜርካን ሀገር ከመጡ ስፔሻልስት ሀኪሞች ጋር በመተባበር የሚሰጥ መሆኑን አክለዋል፡፡

የዓይን ሞራ ግርዶሽ ገፈፋ እና የዓይን ህክምና ከ700 በላይ ለሚሆኑ በበሽታው ለተጠቁ ለዎላይታና አካባቢው ማህበረሰብ በመሆኑ በተጠቀሱት ቀናት ከጧቱ 2፡00 ጀምሮ በኦቶና ማስተማሪያ ሪፌራል ሆስፒታል ዓይን ህክምና ማዕከል በመገኘት የነጻ ህክምና ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተቋሙ ያሳስባል ሲል የሆስፒታል ኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ቡድን ዘገባ አመላክቷል።