
በዛሬው ዕለት በዎላይታ ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር በመሐል ቀበሌ የሚገኘው በተለምዶ የአሮጌ አራዳ ቅዳሜ ገበያ ተብሎ የሚጠራው ለረዥም አመታት ለከተማችን ህብረተሰብ አገልግሎት ሲሰጥና ግብይት ስያካሂዱ የነበሩበትን ስፍራ የቦታ ለውጥ ተደረገ፡፡
ዛሬ የሚጀመረውን አዲሱን ገበያ መጀመሪያ ካለበት ቦታ አሁን ደግሞ ወደ ሶዶ በር ቀበሌ ሐዋርያት መንደር አምባ ሜዳ መምጣቱን የተከበሩ የቦዲቲ ከተማ ከንቲባ አቶ ክፍሌ ታውሌ መሪነት አጠቃላይ የከተማው አመራር በተገኙበት መጀመሩን አብስረዋል፡፡
ከዚህ በፊት ገበያው በነበረበት ቦታ የቦታ ጥበት በመኖሩ ምክንያት ለመገበያየት በተወሰነ መልኩ ችግር ሲያጋጥመን እንደነበረ የሚታወቅ መሆኑን በመግለፅ ያንን ችግር ደግሞ ይሄ ስፍራ ይቀርፈዋል ብለዋል የተባለውን ከከተማ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡