ለስራ ዕድል ፈጠራ የተመደበውን የወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ገንዘብ ከብክነትና ከምዝበራ በመታደግ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሊሠራ እንደሚገባ ተጠቆመ!
ከፌዴራል ጀምሮ በየደረጃው ለስራ ዕድል ፈጠራ የተመደበው የወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ገንዘብ በቀድሞ ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ በአሁኑ ኦሞ ባንክ ገቢ ተደርጎ የተሰራጨው ሀብት ኦሞ ባንክ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ገንዘቡ ያለበት ሁኔታ ግልጽ አይደለም፡፡

ሀብቱ በአሰራሩ መሰረት ለስራ ዕድል ፈጠራ በግልጸኝነት እየዋለ እንዳይደለ ለሚድያው የቀረበው መረጃ ያሳያል፡፡
ሀብቱ በዋናነት በባለቤትነት የሚያስተዳድረው የስራ ዕድል ፈጠራ ተቋም እንኳን ግልጽ መረጃ ኖሮት በክልሉ በሁሉም አከባቢ በከፍተኛ ሁኔታ ቁጥሩ እየጨመረ ላለው ስራ አጥ ወጣቶች በግልጸኝነት ማሰራጨት እንዳልቻለ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በተለያዩት ጊዜያት ለተዘዋዋሪ ብድር ፈንድ የተመደቡ ሀብቶች በጣም ከፍተኛ ብሆኑም ለወጣቶች የሥራ ዕድል ከመፍጠር አንጻር ያሏቸዉ አስተዋጽኦ ስመዘን በጣም አነስተኛ ከመሆኑም በላይ ከዓላማዉ ዉጭ የግለሰቦች ሀብት ምንጭ እንደሆኑ የዉስጥ አዋቂ ምንጭ መረጃ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጧል፡፡
ለአብነት በተለያዩ ጊዜያት ከመንግስት የተመደቡ የሀብት መጠኖች፡-
• ከቀድሞ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል ለቀድሞ የገጠር ወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ከ500ሚሊዮን ብር በላይ በ2005 ዓ.ም የተመደበ፤
• ከፌደራል መንግስት ለቀድሞ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል 1.88 ቢሊዮን ብር ከ2009 ጀምሮ እስከ 2011 የተመደበ ለኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ የተላለፈ፤
• የቀድሞ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል በመደበኛነት በየዓመቱ ከ100 ሚሊዮን እስከ 200 ሚሊዮን ብር ሲመደብ የነበረው፤
• በየዓመቱ ከዞኖች፣ ከልዩ ወረዳዎች፣ ከወረዳዎችና ከከተማ አስተዳደሮች ለኦሞ ባንክ ለስራ ዕድል ፈጠራ ተብሎ በቀጥታ የተላለፈ ለጊዜው ግምቱ የማይታወቅ ሀብት ይጠቀሳል፡፡
ከላይ ከተዘረዘሩት ሀብቶች መካከል የቀድሞ ደ/ብ/ብ/ሕ/ክልል መንግስት የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ወደ ባንክ ደረጃ እንዲያድግ ስወስን መነሻ ካፒታል እንዲሆንለት 700 ሚሊዮን መወሰኑን ጭምር መሆኑን የደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡
ከዚህ ውጪ በየደረጃው የተመደበውና ለኦሞ ተቋም የተላለፈው ሀብት ያለበት ደረጃ እንዲታወቅ እንደማይፈለግ የመረጃ ምንጫችን ያስረዳል፡፡
በመሆኑም ሀብቱን በአሁን ሰዓት እጅግ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ላለው ስራ አጥ ወጣቶች ለማሰራጨት ካለመቻሉም በላይ ገንዘቡ ለምዝበራና ለብክነት የተጋለጠበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አስረድቷል፡፡
ስለሆነም በቀድሞ የደ/ብ/ብ/ህ/ክልል ስር የነበሩ በአራቱም ክልሎች ውስጥ የሚገኙ የሚመለከታቸዉ አካላት በየአከባቢያቸው የተመደበውን የተዘዋዋሪ ብድር ገንዘብ ያለበትን ሁኔታ በመከታተልና በማረጋገጥ በዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ (በ10%) የብድር ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸዉ ተጠቁሟል፡፡
በጣም የሚያሳስዝነው ይህ ሀብት ኮሚሽን እየተወሰደ ለባለሀብቱ እና በአመራር ኔትወርክ ከአሰራር እና ከአግባብ ውጪ በብድር እየቀረበ እንደሚገኝ በቀረበዉ ጥቆማ ለማወቅ መቻሉ ነው፡፡
በተቋሙ ችግሩ ከተስተዋለ የቆየ ብሆንም በባለፉት አራት ዓመታት የግልጸኝነት ችግር እንዳይቀረፍ የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጥላሁን ከበደ ሚና የጎላ እንደሆነ የመረጃ ምንጫችን ያስረዳል።
የኦሞ ባንክ ቦርድ አባላትም ቢሆን ድርግቱን አርሞ የወጣቱን ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ይልቅ ወቅቷ መሻጋገሪያ ወቅት መሆኑዋን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመዉሰድ አይቶ እንዳለዬ፤ እያወቀም እንደማያዉቅ ሆኖ በመንቀሳቀስ ሀብቱ ከፍ ያለ በመሆኑ እስከ ቦርድ ሰብሳቢዉ ጭምር የግሉን ጥቅም ሊያስጠብቅ የምችል መንገድ ብቻ በመምረጥ ለማሳበብ ወቅቱን ለመጠቀም ወስኖ ቴክኒካል አመቻቾች ቡድኑ ጋር በመስማማት ከመስራት ዉጪ ከተሰጠዉ ኃላፊነት ከፍተኘነት አንፃር የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዳልተወጣ የመረጃው ምንጫችን ያስረዳል።
በመሆኑም የፌደራል መንግስትና የሚመለከተዉ አካላት በተለያዩ ጊዜያት ለስራ ዕድል ፈጠራ የተመደበውን የወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ገንዘብ ያለበትን ደረጃ በማጣራት እዉነቱን በመለየት ተገብዉን የማስተካከያ እርምጃ በመዉሰድ ለህዝብ ይፋ እንድያደርግ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
የብድሩ ተጠቃሚ መሆን የነበረበት ከነባሩ ደቡብ ክልል የወጡ የአሁኑ የአራቱ ክልሎች ወጣቶች ለወጣቱ ካለው ፋይዳ አንጻር ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በየአካባቢው ከሚመለከተው ከመንግሥት አካላት ጋር በመሆን ፍትሀዊ ተጠቃሚነታችሁን እንድታረጋግጡ ጥሪ እናቀርብላችኋለን።
ለስራ ዕድል ፈጠራ የተመደበውን የወጣቶች ተዘዋዋሪ የብድር ፈንድ ገንዘብ ከብክነትና ከምዝበራ በመታደግ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ሊሠራ ይገባል!!!
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏