1000036065

“አብዛኛው የደቡብ አከባቢ ህዝብ የፋኖ ዕዝ መቋቋም ይቅርና ፋኖ መኖሩንም አያውቅም”፤ “ከብሄር ብሄረሰቦች ከተወጣጡ መካላከያ ሰራዊት ጋር ጦርነት ከገጠሙት ታጣቂዎች ምን ህብረት አለን?!” – መልስምት

ሰሞኑን በአንዳንድ ሚዲያዎች “በደቡብ የፋኖ ዕዝ ተመስርቶ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል” በሚለው ወሬ መነሻ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በአከባቢው የተለያዩ አካላት ሀሳብ በማሰባሰብ ተከታዩን ዘገባ ሰርቷል።

“ጦርነት ችግሮችን እያባባሰ ይሄዳል ነው። መፍትሔም አያመጣም፥ በተለይም ደግሞ የእርስ በርስ ጦርነት ሲደረግ በስሜት ብዙዎች የሚገቡበት ሲጠናቀቅ የሚጸጸቱበት ነው። ሌላዉ ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ አንስቶ ማስመለስ አይቻልም ለሚለዉ ያም ካልሆነ እኔ ሰላማዊ ትግል ይሻላል ባይ ነኝ።”

“የፋኖ አመራሮቹ ታዉቀዉ የሚያራምደው የትግል አላማ ታዉቆ ጥያቄዎቼ እነዚህ ናቸዉ ብሎ ዝርዝሩን ቢያስቀምጥ በጣም ጥሩ ነበር። አሁን ባለዉ ግን የተለያዩ የፋኖ አመራሮች የሚያወሩት የተለያዬ ነገር ነው። አንዱ ሕገመንግሥት የሚያከብር ነገር ይናገራል፣ አንዱ ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን ማፍረስ አለብን ይላል፣ አንዱ ብሔረሰቦችን ወዳጆቼ ናቸዉ ይላል፣ አንዱ ይዝታል፣ አንዱ ስለአማራ እና አማራ ብቻ ያወራል፣ አንዱ ስለኢትዮጵያ ያወራልና የራሱ ግልጽ አላማ የሌለው በደቡብ የፋኖ ዕዝ ተቋቁሟል ማለት ከቅዠት ያለፈ ፋይዳ የለውም” ብሏል።

“እኛ በተለይም ደቡብ አካባቢ ህዝብ ትምህርት ቤት ተዘግቶ፣ ጤና ተቋማት፣ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ንግድ ተቋማት ተዘግቶ እንዲሁም የህዝብ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ቆመው በጦ’ር መሳሪያ የመገ’ዳደል ፖለቲካ በፍጹም አማራጭ መፍትሔ አድርገው የሚቀበል አይደለም። እኛ ግን የምናበረታታዉ ጦርነትን ሳይሆን ሰላማዊ ድርድርን ነው። የአማራዉ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ጋር ወንድማማች ነው። የወንድማማች መገዳደል ሊቆም ይገባል እንላለን” በሚል ምክር ለግሷል።

“በአሁኑ ሰአት በአማራ ክልል እጅግ በተካረረ ሁኔታ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑ በእዉነቱ በጣም አሳዛኝ ነው። ከእርስ በርስ ጦርነት መዉጣት አለመቻላችን በጣም ያሳዝናል። ከዛ በተረፈ ይህ ጦርነት አሁኑኑ መቆም ስላለበት የተኩስ አቁም ስምምነት መደረግ አለበት ብዬ አምናለሁ። ከሁለቱም ወገን የሚያልቀዉ የኛዉ ዜጋ ነው፣ በከንቱ ተጨባጭ እመርታ ለሀገራችን የማያመጣ ጦርነት መቆም አለበት። ኢትዮጵያ ችግሯ መቼም በጦርነትና በጉልበት አይፈታም። ይባስ ብሎ ጦርነት የበለጠ ችግሩን የሚያባብስ እና ንጹሃንን የበለጠ ተጎጂ እያደረገ የሚሄድ ነው። ከሚያልቀዉ ወገናችን በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ኪሳራዉም ከባድ ነው።”

“የአማራ ሊህቃን በሐገር ዉስጥም በዉጪም ከስሜታዊነት ወጥተዉ መንገዳቸዉን መመርመር አለባቸው። ለአማራ ሕዝብ እንቆረቆራለን የሚሉ ኃይሎች፣ አላማ እና እስትራቴጂያቸዉ የተለያዬ ነው፣ አንዱ ከተለያዩ አካላት ጋር በጋራ ለመሥራት ይጥራል፤ ሌላዉ እነዛን አካላት እንደጠላት ፈርጆ ይንቀሳቀሳል።”

“በሐገሪቷ ስለሚገኙ ለተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችም ያላቸዉ አረዳድ የተለያዬ ነው። ይህ ኃይላቸዉ እንዲበታተንና በአነስተኛ ኪሳራ ምናልባትም በሰላማዊ መንገድ የሕዝቡን ጥያቄ እንዳያስመልሱ እንቅፋት ሆኗል ሰጥቶ የመቀበልን ፖለቲካ ለማካሄድ እንቅፋት ሆኗቿል። በተለይ የአማራ ሊህቃን የሕዝባችን ጥያቄ የሚሏቸዉ ነገሮች ከሌሎች ሕዝቦች ጋር የተሳሰሩ መሆናቸዉንና ፖለቲካ ደግሞ በባህሪዉ ሰጥቶ መቀበልን የሚፈልግ መሆኑን አምኖ መንቀሳቀሱ ይበጃል ባይ ነኝ፣ እነሱም ቢሆን በጉልበት የሚሳካላቸዉ ነገር እንደሌላቸዉ ቢያዉቁ ጥሩ ነው።”

“ከሌሎች ብሔር ሊህቃንም ጋር ደግሞ ከመፈራረጅ ባለፈ የጋራ አጀንዳ ለመፍጠር መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፥ ጦርነቱ በተራዘመ ቁጥር እየበዛ የሚሄደዉን የሕዝቡንም ስቃይ ከግምት ዉስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው። ሰላም ይሻላል፣ ሁሉን አቀፍ ዉይይትና ድርድር ይሻላል።”

“በአማራ ሊህቃንም በኩል ደግሞ ለሌሎች የፖለቲካ ኃይሎች እዉቅና ሰጥቶ በጋራ የመሥራትና የመታገል ክፍተት በዉስጥም በዉጭም ይታያል። የድሮ አገዛዞች ያደረሷቸዉን በደሎች መካድ አያስፈልግም፣ ስለነዛ አገዛዞች ጥብቅና መቆም አያስፈልግም፣ ይልቅ ያ ችግር ዛሬ የለምና የዛሬን ችግር በጋራ እንፈልግ የሚለዉ ላይ ማተኮር ያስፈልጋል።”

“ፋኖም አንድ አደረጃጀት ፈጥሮ ወደ ድርድር ይምጣ። ከዛ ባለፈ የማምታታት አካሄዱ የትም ስለማያደርስ የመፍትሔው አካል ቢሆን ይመረጣል፣ ከዚህ በላይ የዉድመት መንገድ ላይ መቀጠል የለበትም። ኢትዮጵያ ዉስጥ በድርድር የጋራ ነገር ከፈጠርን እንጂ፤ ማንም ማንንም ማንበርከክ አይችልም።”

“አንዳንድ የፋኖ ደጋፊዎች አሁን ያለዉን ጦር የብርሃኑ ጁላ ጦር፣ የኦሮሞ ጦር እያሉ ለማጠልሸት ይሞክራሉ፦ ይህ በፍጹም ትክክለኛ ካለመሆኑም በላይ አሰፈላጊም የሆነ አባባል አይደለም። መቼም ቢሆን መከላከያ ጠንካራ እንዲሆን ነው መፈለግ ያለብን፣ ጦሩን የሚከፋፍል መርዝ መርጨት ተገቢ አይደለም፤ መከላከያ ችግር ቢኖርበትም የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች ስብስብ የሆነና ለሀገሪቷ ህልዉና አስፈላጊ ነው።”

“መከላከያ የበለጠ አካታች እና የበለጠ ጠንካራ እንዲሆን እንፈልጋለን፣ ወንጀል የሠራ ይጠየቅ እንጂ ለመከላከያ መጥፎ በጅምላ አንመኝም። የእርስ በርስ ጦርነቶች የሀገር ጦሩን ያዳክማሉና መቆም አለባቸዉ፣ ችግራቸዉ ፖለቲካ ነዉና ፖለቲካዊ መፍትሔ ያስፈልጋል፥ ጦሩ ላይ ከማነጣጠር በበለጠ የፖለቲካ አመራሮች ላይ ማነጣጠሩ ይጠቅማል።”

“ሌላዉ ደግሞ በተለይም ከሕገመንግስቱ ማዕቀፍ የሚወጡ ጥያቄዎች በፌደራል መንግሥትም ሆነ በፋኖ ብቻ ሊመለሱ አይችሉም፤ ሁለቱ ቢስማሙ እንኳን የሚቻልበት አግባብ የለም በሐገሪቷ የሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች መሳተፍ አለባቸዉ ነው።”

“ጦርነት ደግሞ ወደ መፍትሄው እያቀረበን ሳይሆን እያራቀን ይሄዳል ነው። የፌደራል መንግስት የሐገሪቷን ሕገመንግሥት አክብሮ አይንቀሳቀስም ብለዉ ያኮረፉ ኃይሎች በብዛት ባሉበት ፋኖ ሕገመንግሥታዊ ሥርአቱን በሚያጠፋ መንገድ የሚንቀሳቀስ ከሆነ አስቸጋሪ ነው። ለሁሉም ደግሞ ከጦርነት በሰላማዊ ድርድር ችግሮችን ለመፍታት መንቀሳቀሱ ይበጃል ነው።”

“አንድ ግን አጽንኦት ሰጥቼ የምናገረዉ በኢትዮጵያዉያን መሐከል የሚደረግ ድርድር እንጂ ጦርነት አንደግፍም። በተለይ ፋኖ ከለዉጥ በኃላ የተደራጀ በትግራይ ጦርነት ወቅት ከመንግስት ጎን የተሳተፈ እንዲሁም በመጀመሪያ ከነበረዉ የክልሉ መንግስት ጋር አብሮ የሚሰራ ኢ_መደበኛ የታጠቀ ቡድን የነበረ ሆኖ ሳለ አሁን ላይ “በደቡብ የፋኖ ብርጌድ ተመስርቶ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምሯል” የሚለው ወሬ የአከባቢውን ህዝብ ስነልቦና ካለማወቅ የመነጨ ምኞት ነው፣ አብዛኛው የደቡብ አከባቢ ህዝብ የፋኖ እንቅስቃሴ ከደቡብ ህዝብ መሠረታዊ ፍላጎት ጋር የማይገናኝ በመሆኑ የፋኖ ዕዝ መቋቋሙ ይቅርና ፋኖ መኖሩንም አያውቅም” ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የተወጣጡ የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት ጋር ጦርነት ከገጠሙት ምን ህብረት አለንና!?” ብሏል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #Amara #Fano #southethiopia