” ህዳሴ ግድ ዘንድሮ በአመቱ መጨረሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት ስራ እንዲጀመር እየተሰራ ነው” – ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ
የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ምስረታ 10ኛ ዓመት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የግድቡ ሁለት ተርባይኖች በዓመቱ መጨረሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት እንዲጀምሩ እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ፥ ግድቡ 79 በመቶ ያህል መድረሱን ገልፀው ፥ በዚህ ዓመት የውሃ ማስተላለፊያ ፥ ወደ ታችኛው ተፋሰሶች የሚያስተላፍ የውሃ ማስወጫ ስራዎች በስፋት የሚሰራበት ነው ብለዋል።
በተጨማሪ ይህ ዓመት 11ዱን ተርባይኖች ማንሳት የሚችሉ የብረት ስራዎች እየተሰሩ ያሉበት መሆኑንና የግድቡን ቁመት ለማሳደግ የኮንክሪት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።