በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከብልጽግና አቅጣጫ ውጪ ሾልከው ያመለጡ አመራሮች
በቅርቡ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የገዥው ፓርቲ ም/ፕረዝዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አደም ፋራህ በተገኙበት በዎላይታ ሶዶ በተካሄደው መድረክ ላይ በአብዛኞቹ ተሰብሳቢዎች በዋናነት ስር በሰደደው ሙስና፣ ስነምግባር ጉድለት፣ አድሏዊነት፣ ብልሹ አሰራር፣ በመፍትሔ አቅጣጫ ዙሪያ እንዲሁም የመንግስት አሰራር ሆነ የገዥው ፓርቲ ተግባርና ስልጣን በግለሰቦች እጅ በመውደቁ ህብረተሰቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዳይጥል እንቅፋት ሆኗል” በሚል ተገምግሞ የተነሱ ተጨባጭ መረጃዎችን በመውሰድ አስቸኳይ እርምት እርምጃ የሚያስፈልገው በመሆኑ በቦታው ምንም ውሳኔ ሳይሰጡ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መመለሳቸውና የእርምት እርምጃ እየተጠበቀ ስለመሆኑ መዘገባችንም ይታወሳል።
በተለይም ክልሉን በተመለከተ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ እውነትንና ተጨባጭ መረጃዎችን መነሻ አድረጎ በተደጋጋሚ በሰራው ዘገባ መሠረት በክልሉ ሁለት ምክትል ርዕሰ መስተዳደሮች ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ከኃላፊነታቸው ተነስተው ሌሎች በቦታው የተተኩ ቢሆንም ተጨባጭ ህገወጥ ተግባር ውስጥ የተዘፈቁ አመራሮች ሾልኮ መቅረታቸውን ለመታዘብ ችለናል።

በዚሁ መነሻ በትናንትናው ዕለት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ “የመንግስት አሰራር ሆነ የገዥው ፓርቲ ተግባርና ህግ በመጣስ በየአካባቢው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ እንዳይሰጥና ህብረተሰቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዳይጥል እንቅፋት ፈጥሯል” በሚል የተገመገሙ አመራሮች ሹም ሽረት አካሂደዋል።
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የደቡብ ኢትዮጵያ የአመራር ብልሽት በተመለከተ በከበሩ ማዕድናት፤ በኮንትሮባንድ፤ በከተማና በገጠር በኢንቨስትሜንት መሬቶች እንደሆኑ በመረጃ አስደግፈን ለሕዝብ ይፋ ማድረጋችን የሚታወቅ ሲሆን የተወሰኑ በዚሁ ብልሹ አሰራር የተዘፈቁ አመራሮች ከኃላፊነታቸው የተነሱ ቢሆንም አብዛኞቹ ለጊዜው ምክንያቱ በማይታወቅ ሁኔታ በስልጣን እንዲቀጥሉ መደረጉን በርካቶችን እያነጋገረ ይገኛል።
ለምሳሌ ዎላይታ እና ጋሞ በጉርብትና ቢሆን እንጂ በክልል መዋቅር አንድ ላይ በፍጹም አይደራጅም፣ የህዝብም ፍላጎት ያ ነው፣ ሳይደራጅ ለሚፈርሰው የብልፅግና መንግስት ህዝብን ባያስገድድ ይመረጣል” በሚል ከመንግስት አካሄድ ውጪ በመንቀሳቀስ የሚታወቁት የቀድሞ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የወቅቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ይገኙበታል።

በጋሞ ዞን በ2010 እስከ 2014 ዓ.ም በዞኑ አስተዳዳሪ በነበሩት እንዲሁም የወቅቱ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ በአቶ ብርሃኑ ዘዉዴ ከክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት እውቅና ውጪ መሬት በምደባ ማስተላለፍ (የተላለፈላቸው የመሬት መጠን 104 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ የተመዘገበ ካፒታል 1,111,249297 ስራ ላይ የዋለ 24,764,800 ነበር።
የቢሮ ኃላፊው ከክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት እውቅና ውጪ በጥቅም ትስስር ህጋዊ አሰራርን በመጣስ በጋሞ ዞን በአርባምንጭ ከተማ በቁጥር 53 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በአቶ ብርሃኑ ዘዉዴ አማካይነት አሰራርን ባልተከተለ መልኩ የተላለፈ ስለመሆኑ በመረጃ አስደግፈን ዘግበን ነበር።
በተጨማሪም ከ500 ሄክታር በላይ የማዕድን ልማት መሬት ከክልሉ ሆነ ከእንቨስትመንት አሰራር ውጪ በጥቅም ትስስር ለግለሰቦች በአንድ ደብዳቤ ትዕዛዝ ሲሰጥ “በዞናችን በተለያዩ አካባቢዎች የድንጋይ ከሰል ማዕድን ከምችት መኖሩ በጥናት የተረጋገጠ ሲሆን በተለይ በቦረዳ ወረዳ ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ለማምረት ፈቃድ በማውጣት ሂደት ላይ የሚገኘው ማራ ማይንግ ኃላፊነት የተ/የግል ማህበር ለጥናት ይዞ ከነበረው 600 ሄክታር ላይ ለድርጅቱ 10 ሄክታር ብቻ በማስቀረት ሌላው ለጋሞ ልማት ማህበር እንዲሁም በዞኑ በግልም በማህበርም የድጋፍ ደብዳቤ ለወሰዱ ተሸንሽኖ እንድሰጣቸው የዞኑ አስተዳደር ምክር ቤት ባደረገው ሰብሰባ መወሰኑ ይተወሳል” ሲል ትዕዛዝ የሰጡት የቀድሞ የዞኑ ዋና አስተዳደሪ እንዲሁም የወቅቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዱ እንደሆነ ከሰነዱ ጋር ማጋለጣችን ይታወሳል።
ሌላኛው ደግሞ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ የሌሎች ብሄሮች ሰራተኛ አለአግባብ እንዲባረሩ በውድድርም እንዳይገቡ በማድረግ 88% በላይ ሰራተኞች የአንድ አከባቢ ብቻ እንዲሆኑ በማድረግ በተለያዩ ዞኖች የሚገኙ ግብር ከፋዮች ላይ ያልተገባ ጫና እየፈጠሩ ስለመሆኑ ዘግበን ነበር።

የክልሉ ገቢ ቢሮ 88% በላይ ሰራተኞች የአንድ አከባቢ ሰዎች ብቻ እንዲሰሩ በመደረጉ በተለያዩ ዞኖች ላይ ያልተገባ ጫና በመፍጠር ላይ ከመሆኑ በተጨማሪ በተለይም በዎላይታ ዞን፣ በጌዴኦ እና ጎፋ ዞን የሚገኙ ትላልቅ ድርጅቶች ግብር ከፋይ የሆኑ ባለሀብቶች ላይ ያለአግባብ ጫና በመፍጠር ፋብሪካዎች እንዲዘጉ፣ ባለሀብቶች እንዲታሰሩ እና እንዲሸማቀቁ መደረጉም ተገልጿል።
በክልሉ ከሁሉም መዋቅሮች ከግብር ከፋይ የተሰበሰበ ከፍተኛ ገንዘብ የተለያዩ ህገወጥ ዘዴዎችን በመጠቀም ወጪ ተደርጎ እንዲወጣ ተደርጎ በኢፍትሃዊነት ለራሳቸው ለሚሉት ጥቅምና ፍላጎት መጠቀሚያነት እያዋሉ ስለመሆኑም የደረሰን ተጨባጭ የስነድ መረጃ ጠቅሰን ዘግበናል።
ከ 45 በላይ ስራተኞች የቢሮው የሰው ሀብት አመራሮችና ሰራተኞች ሳያውቁ በህገወጥ መንገድ በራሷ ፊርማ ብቻ ቅጥር መፈፀሟ የተገለፀ ሲሆን ለማሳያነት ከክልሉ ገቢዮች ቢሮ አመራርን ጨምረው አጠቃላይ 77 ሰራተኞች 88% ጋሞ፣ 6 የዎላይታ ተወላጆች (2 ሾፈሮች እና 4 ተራ ስራተኞች) እንዲሁም የተቀሩ ሰራተኞች 3% የማይሞሉ ከሌሎች ብሄሮች እንደሆኑ ያገኘነው ተጨባጭ መረጃ ይጠቁማል።
በተጨማሪም የመንግስት ስራተኞች ደመወዛቸውን በአግባቡ መክፈል እየተቸገሩ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ዞኖች የሚከፍሉትን ግብር ከአሰራር ውጪ እየመሩ የሚገኙት የቢሮ ኃላፊዋ ወይዘሮ አለመነሽ፦ ፌደሬሽን ምክርቤት ባፀደቀው ህግ መሠረት በክልሉ በአንድ አከባቢ የሚገኝ የፌደራል ተቋም ለክልሉ በማሳወቅ ለፌደራል ገቢዎች ከከፈለ በኃላ በፐርሰንት ወደ ተቋሙ ያለበት ዞን የሚላክ “የጋራ ገቢ ህግ” መሠረት መላክ የነበረበትን ከግማሽ በታች እንዲሆን ማድረጓንና አለግባብ ገንዘቡ በህገወጥ አሰራር ወጪ እየተደረገ ስለመሆኑም ያገኘነው ተጨባጭ መረጃ ያመለክታል።
አንድ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው አመራር መረጃ ከሆነ በህጉ መሠረት፦ ከጋራ ገቢ ከፌደራል ለሚመለከታቸው ዞኖች ለክልሉ የተላከውን በቢሊዮን የሚቆጠር ከፍተኛ ገንዘብ አለአግባብ ውጪ እየሆነ እስካሁን ኦዲት ተደርጎ አለማወቁን አስረድተዋል።
ለግንዛቤ ያህል፦ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ገንዘብ በፋይናንስ ቢሮ አማካይነት ለሁሉም ዞኖቹ በህጋዊ ቀመሩ መሠረት ገቢ ማድረግ ሲገባው በተቃራኒው ያንን ህጋዊ ቀመር በመጣስ ገንዘብ በክልሉ እንዲቀር በማድረግ ከአመራሮቹ ጋር በመመሳጠር አለአግባብ ወጪ እንዲሆን ያደርጋል።
በመሆኑም ክልሉ የገዥው ፓርቲው በይፋ ባረጋገጠው መሠረት “የመንግስት አሰራር ሆነ የገዥው ፓርቲ ተግባርና ህግ በመጣስ በየአካባቢው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ እንዳይሰጥና ህብረተሰቡ በመንግሥት ላይ እምነት እንዳይጥል እንቅፋት ፈጥሯል” በሚል የተገመገሙ አመራሮች ሹም ሽረት አካሄድ ለህብረተሰቡ ዘላቂ ልማትና ሰላም ለማረጋገጥ ሲባል ዳግም ሊያጤናውና ሊፈትሸው የሚገባ እንደሆነ ያስረዳል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia
Read more on our official website
አመራሮቹ ከገዢው ፓርቲ አቅጣጫ ውጪ እንዴት ሾልከው አመለጡ?!