1000037941

ለ29 ዓመታት ምዕመናንን ለሰማይ ሲያዘጋጅ የነበሩ ቄስ በተቃራኒው የምድር መሰደድ ለምን መረጡ ?

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዎላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት መላከሰላም ቀሲስ ቦክቻ ኤንጋ የልጃቸው ሞባይል ቀፎ መሰረቁን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያ የለጠፉት መልዕክት በኦርቶዶክስ ምዕመናንን ጨምሮ በአከባቢው በርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ ሆነው ይገኛል።

መላከሰላም ቀሲስ ቦክቻ በዚሁ በግል ፌስቡክ ገፃቸው አማካይነት ባልተለመደ ሁኔታ ትናንት እኩለሌሊት ባሰፈሩት ፅሁፍ ያነሱት አንኳር ነጥቦች ምንድናቸው ?

👉 “ከነቤተሰቦቼ ለመሰደድ ዝግጁ ነኝ። በልጆቼ ላይ በተጠና ሁኔታ ተከታትለው የተፈጸመውን የግድያ ሙከራና የስልክ ዘረፋ መካሄዱ በእጅጉ አሳዝኖኛል።”

👉 “በዎላይታ ምድር ለ29 ዓመት ዎላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በመሆን፤ በተለያዩ ደረጃዎች ያገለገልኩበት ከንቱ ይሁን ልጆቼን ተደራጅታችሁ አትንኩብኝ፣ ሴቷን በጥዋቱ 4 ሰዓት ሰው እያዬ መንገድ ላይ ደፍታችሁ ስልኳን ዘረፋችሁ ወንዱን በሴንጢ አስፈራርታችሁ በቀን ብርሃን ሞባይሉን ዘረፋችሁ።”

👉 “በኢትዮጵያዊ ስሜት እንጂ በእናንተ አስተሳሰብ ለእኔም ሀገር አለኝ። ቤተሰቤን ይዤ ሄጄ ብኖሮ ምቀድስበት፣ ማስተማርበት፣ ማስተዳድርበት፣ የምኖርበት።”

👉 “በእንዲህ ያለ ግፍና በደል መቀጠል ለእኔም ለቤተሰቦቼም አይበጅምና የራሴን ውሳኔ በመስጠት ለመሰደድ ዝግጁ ነኝ በልጆቼ አትምጡብኝ። አበቃ። በራሴ ዝም ብዬ የኖርኩበት ዘመን ይበቃል በልጆቼ አትምጡብኝ።”

👉 “ለእኔም ሀገርም ምድርም አለኝ ብቻ በልጆቼ አትምጡብኝ እኔማ በሽተኛ ሆንኩ ወርቅ ላበደረ ጠጠር ሆኖ ነገሩ። ለዛሬው በዚህ ይብቃ ቤተሰቦቼን ይዤ ለመሰደድ ዝግጁ ነኝ።” በሚል የሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት የልጃቸው ሞባይል ቀፎ መሰረቁን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያ ለጥፏል።

በአከባቢው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆኑ ምዕመናንን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ለቄስስ መልዕክት ምን አስተያየት ሰጡ ?

👉 “አባታችን ህመምዎ ያመናል። እጅግም ያሳዝናል። ነገር ግን ይኸ ጽሁፍ ከእርስዎ አይጠበቅም። እኔ እንዲያውም አካውንት ተሰርቆ መሆን አለበት ብየ አስባለሁ። ህዝብ ከህዝብ ጋር ከሚያጋጩ እንደ እግዚአብሔር አገልጋይ በግልዎ መከራ ቢቀበሉ አይሻልም❓ከቻሉ ቶሎ ይኸ ልጥፍ ያንሱ።”

👉 “ይሄ ከባድና አሳዛኝ ነው። ግን ከህዝብ ጋር ባያገናኙት ጥሩ ነው። ነጣቂዎች በህዝብ ከተደበቁ በህግ አግባብ እንዲወጡ መደረግ አለበት። እኛም የምንወዶት የምናከብርዎት ልጆችዎ የዚህ ህዝብ ልጆች ነን 🙏”

👉 “ለእርስዎ ሆነ ለልጆችዎ ክፉ ለሚያስብ እግዚአብሔር አሳልፎ አይሰጥም። ፈጣሪ ልቦና ይስጠው። ነገር ግን የእርስዎ አገላለጽ በፍጹም ዎላይታ የዋለልዎትን ውለታና አክብሮት በዜሮ የሚያባዛ በብሔር ምክንያት የተገፉ የሚያስመስል፣ አደገኛ እጅግ አደገኛ አገላለጽ ስለሆነ ልጥፉን ቢያነሱ እላለሁ። በየትኛውም አከባቢ ለሰው በግል ቅራኔ ምክንያት ክፉ ሥራ የሚሠራ ይጠፋል ብዬ አላስብም። አንድ የሃይማኖት አባት ሀገሬ እያለ መናገር ያለበት ጉዳይ አይደለም ዎላይታ ደግሞ በዚህ ያምናል። እርስዎም ያውቃሉ ያሳደገ ለወግ ለማድረግ ያበቃ የተንከባከበ ሕዝብ በጅምላ እንደጎዳ አድርጎ ማቅረብ ስለማያስፈልግ ነው።”

👉 “የተከበሩ አባታችን እኛ ለእርሶ ያለን ፍቅር የሚታወቅ ነዉ። በእርሶ ልጅ ብቻ ሳይሆን በማንም ላይ ዝርፊያ መካሄድ የለበትም። ሊወገዝ ይገባል። ይሁን እንጂ የሚፈጥሩ ችግሮችን ከብሔር ጋር ማያያዝ የለብንም። በተለይ በአባቶች ደረጃ ጥንቃቄ የሚፈልግ ነዉ። አንድ ምሳሌ ለመጥቀስ ያህል በ2014 ዓ.ም በወርሃ ሚያዝያ እኔ የለበስኩትን ጃኬት፣ ገንዘብና ሞባይል ተዘርፊያለዉ። ይህንን ዝርፊያ ወደ ብሔር እና አከባቢ እንዴት አስጠጋለሁ? የዘረፉኝ ሌቦች ናቸዉ።
ዓለም ሁሉ ለአባቶች ሀገራቸው ነው። ፈተና መምጫው አይታወቅም አባታችን ለእኛም ለእርሶም ፀልዩ።”

👉 “ድርጊቱ ያሳዝናል ነገር ግን የተለጠፈው ነገር በጣም ያስጠላል እና እኔ ያየሁት ነገር ከአንድ ሀይማኖት አባት ነው ለማለት ይከብዳል እዉነት የዎላይታ ህዝብ ዘር ቆጥሮ ጥቃት ፈፅሟል? ዘር ብሔር ምን ማለት ነው??? በጣም ያሳዝነናል እንዲህ አልጠበኩም። እግዚአብሔር መቸስ እዉነቱን ያውቃል።”

👉 “ከተፈጠረው ነገር በላይ የእርስዎ ነገሩን የብሄር ጥቃት መልክ ሰተው መፃፎ እጅጉን ያስደነግጣል: ለዎላይታ ህዝብ ዋልኩ ከሚሉት እጅጉን ህዝቡ ውሎሎታል: እርስዎ የዚህ አካባቢ ሰው አይደለሁም ብለው እስከሚፅፉ እስከዚህች ፅሁፍ ድረስ የዚህ አካባቢ ሰው አለመሆኖን አላውቅም ነበር። የእርስዎ ልጆች ላይ በደረሰው ነገር እጅግ ባዝንም ሀገሬ ባሉት ቦታ ላይ ባሉ የዎላይታ ተወላጆች ላይ የአፀፋ ጥቃት ሊያስነሳ የሚችል አዋጆትን ግን የበለጠ እቃወማለሁ።”

👉 “በእርስዎ አገላለፅ መሰረት የአያት ቅድመ አያቱ እትብት እዚሁ ተቀብሮ ተወልዶ ባደገበት አባቱ ደጃፍ ላይ ለማይረባ የሞባይል ቀፎ የተገደለው ስንቱ እንደሆነ ከእርስዎ በላይ የሚያውቅ የለም። ወንጀለኛን በህግ አግባብ መጠየቅ እንጂ የወላይታ ህዝብ ወርቅ ላበደረ ጠጠር የሚተረትበት ሳይሆን ከውስጥ ሆነው እንደጠላት ሚገዘግዙትንም ጭምር አቅፎ የሚያኖር ደግ ህዝብ ነው። እንግዲህ ምን ይባላል መልካም ይግጠሞት”

👉 “አባታችን አይዙዋቸው ለምን ሀገር መለቀቅ ሀገራችን ዎላይታ የእሶም ጭምር ነች እኮ አንዳንደ ያጋጥማል ደግሞም እንደዚህ አይነት አጸያፍ ድርገት በሁሉም ሀገር በሁሉም ቦታ አለ እኮ ዎላይታ ሰዎች የተለየ ዓይን እርሶ ባዳ አድርጎ አለዩሁም የዎላይታ ሕዝብ የእርሶ ጎን ናቸው ድርገት አፈጻምና ዛቻ ያደረጉ ሰዎች በሕግ መከሰስ ተገቢ ነው የእርሶ ጎን የማይሆን ሕዝብ የለም።”

👉 “ግን የተዛባ አስተያየት በዎላይታ ህዝብ ለምን? ባከበርዎ ህዝብ ላይ እንድህ ማለት ጥሩ አይደለም። መንፈሳዊ አባት ነኝ ከሚሉ ሰው ጭራሽ አይጠበቅም። በግልዎ ተብደለው ልሆን ይችላል። 29 አመት ዎላይታን ሲያገለግሉ እንደህዝብ በዎላይታ ምን ተበደለዋል? ወልደው ከበደው …..ክብር አይተዋል። ዎላይታ የመብት ጥያቄ ባነሳ ወቅት እንኳን ለበርካታ ጊዜ ዎላይታን ወክለው ዎላይታ ሆነው እኛም በነበርነበት ቤተመንግስት ከተመው ስለ ዎላይታ መክረዋል። ዎላይታ በመኖርዎ ክብር አግኝተዋል። አልተዋረዱም። ዎላይታ እንኳን አለመሆኖን ከዛሬዋ ጽሁፍዎ ተገንዝብያለሁ።”

👉 ” ዎላይታ ብሄርን፣ ዘርን ቆጥሮ አያውቅም። ዎላይታ በምድሩ የሚኖረውን ማነህ? ምንድነህ? ከየት መጣህ? ለምን መጣህ ብሎ አያውቅም። አለ ስም ስም መስጠት ተገቢ አይደለም። ህዝባችን ጽንፈኛ ብሄርተኛ አይደለም። ታዲያ ከአስዳዳሪነት መነሳት 29 አመታት መጥመጠው የጠቧትን የዎላይታን ጡት በርግጫ መማታት ተገቢ ነው? በዚህ ልክ ዎላይታን አመድ አፋሽ ማድረግ ተገቢ ነው? የማናችንም ልጅ ሞባይል ተቀምተው ልሆን ይችላል። በህግ አግባብ መጠየቅ ይቻላል። ከብሄር ጋር የሚያገናኝ ነገር የለውም።”

👉 “ከርስዎ የማይጠበቅ ተግባር ነው። ምነው ግን ለ29 ዓመታት ሲኑሮ ያላስታውሱትን የማንነት ፍለጋ መዳከር ተገቢ ነው? ጋሞነትው ከ29 አመት በሗላ ማስታወሰው በራሱ ችግር የለውም። በፖለቲከኛ ሴራ ለሚናወዘው ለሁለቱ ብሄሮች ሀይማኖታዊ አጀንዳ መጨመሩ ለማንም አይበጅም። በሮግጥ ታርመው ህዝቡን ይቅርታ ይጠይቁ👉 ከዚያም ለ29 ወደማያዉቁትና ወደላስታወሱት” ሀገር” ከሚሄዱ እዚሁ ይቆዩ ግድየለዎትም👉ዎላይታ ፍቅር ናት!!!”

👉 “ሌባ ሞባይል ሰርቆ መላውን ህዝብ ተጠያቂ ለማድረግ መከጀል ስድብ ነው። እባክዎ በአቅራቢያው ባለው ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ያመልክቱ😏 ዎላይታ ሰላም ነው። ለመሄድም ለመምጣትም መንገዱ ክፍት ነው። ነገር ግን በአንድ ፖስት ማንነትዎን ግልጽ አድርጓል እናመሰግናለን 😏”

👉 “እርስዎ እንዲህ ብሔር ከብሔር ጋር የሚያጋጭ መልዕክት እንደ አንድ ሀይማኖት አስተማሪ አባት አልጠብቅም፣ ዝርፊያ የትም ያለ ነዉ፣ ልጆች የተዘረፉት በቀን በተጠና መልኩ ተዘረፉ የሚሉ ከሆነ በቂ ማስረጃ በማቅረብ በህግ ፍት ማቆም፣ ወንጀለኛን ማንም አይፈለግም ወንጀለኛ ብሔር አይመርጥም፣ በሁሉም ቦታ ያለ ስለሆነ የሚሄዱት ወዳገለገሉት ጌታ ከሆነ እዛው ሠላም አለ። ስለዚህ ይሄ እርስዎን አይመጥንም።”

👉 “ይሄ በጣም የሚያሳዝን ተግባር ነው ነገር ግን ክቡር አባታችን ብዙልጆች ብዙ ቤተሰብ ከርሶ መንፈሳዊ ህይወት ውስጥ እንዳሉ ያስቡ በብዙ ደሞ እግዚአብሔር እያከበሮት ይሄን ያህል ዘመን አገልግለዋል ስለዚህ በዚ ደረጃ አይጨነቁ 💔 ሀጢያተኛን ሀጢያቱ ታሳድደዋለች የትም አያመልጥም”

👉 “ሞባይልና ሞተር በቀንም በሌሊትም ይነጠቃል፤ ይህ ንጥቂያ በዎላይታም ከዎላይታ ውጪም ሞልቷል። እርስዎ ለሚወዱት ልጆች ደህና ሞባይል ገዝተው ሊሆን ይችላል፤ በቅርብ ልጆችዎን የሚያውቁም ሆነ ምቹ አጋጣሚ ያገኙ ነጣቂዎች ሞባይላቸውን ነጥቀው ሊሆን ይችላል። ነጣቂ ብሔር ጠይቆ አይደለም ተግባሩን የፈጸመው። አስጸያፊ ተግባሩን መላው የዎላይታ ህዝብ እንዳደረገ የብሔር መልክ ለማስያዝ ያደረጉት ጽሑፎት ትክክል አይደለም፤ መላከሰላም የእምነታችሁ ተከታይ ባልሆንም በጣም ነው የማከብርዎት። ነገር ግን ካለፉት ሶስት ወራት ጀምሮ በዚህ ገጽ የሚጻፉ ነገሮች አስተማሪ አይደሉም፤ ግጭት ቀስቃሽ ናቸው ብዬ መውሰድ እችላለሁ።”

👉 “እባክዎትን እኛ ከርስዎና ከመሰል የሃይማኖት አባቶች መልካም መልካሙን ብንማር ባይ ነኝ። ልጆችዎ ጥንቃቄ ካላደረጉ ነገም ሞባይላቸውን ሊነጠቁ ይችላሉ፤ ይህ ደግሞ ሊያስኮበልሎት አይገባም ባይ ነኝ፤ ነጣቂዎች አንድ ወይም ሁለት ናቸውና። የዎላይታ ህዝብ እንደሚያከብሮትና እንደሚወዶት ከኔ በላይ እርስዎ ያውቃሉ። ልጆችዎ በጥንቃቄ እንዲጓዙ ያድርጉ። በተለይም የምሽት ጉዞና የንጋት ጉዞ ጥንቃቄ ቢያደርጉ መልካም ነው። ሰላም ይብዛሎት ቄሲስ!!”

👉 ዘር ሃይማኖት ሳይለይ ከሚዘርፈው ዘራፊ ጋር ሰፊውን የዎላይታ ህዝብን በመኮነኖ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው። ማንም ሕሊና ያለው ሰው ወንጀልና ወንጀለኛን ደግፎ አያውቅም። የትም ሀገር ላይ ወንጀለኞች እንዳሉ ሁሉ ዎላይታ ውስጥ አሉ። ለእርሶስ ዎላይታ ስንት ውለታ ሰራች በትንሹ ከቀበለ ዉረዳ ከክልል ፌደራል ላይ ታዋቅ የሆኑት ዉደ ዎላይታ መተው አይደል ምንድነው አባታችን ሃገር ሃገር ስደት ስደት እያሉ ማሸቃበጥ?! አንድና ሁለት ዱሩየ ባጠፋው ህዝብን መውቀሰ እንደዚህ ዘረኛ መሆን ምንድነው ወይሰ የሌላ ሰው ስልክ ተቀምቶ አያቅም የእርሶ ልጅ ስልክ የመጀመሪያ ነው?” –

የሚሉ አስተያየቶች በአከባቢው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆኑ ምዕመናንን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዎላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ቀሲስ ቦክቻ ኦንጋ የልጃቸው ሞባይል ቀፎ መሰረቁን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያ ለለጠፉት መልዕክት እየተሰጠ ይገኛል።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከየትኛውም አከባቢ በበለጠ ለሀገር ባለውለታ የሆነችውን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ከጥንት ጀምሮ አቅፎ ታሪካዊ ቅርሶቿን ጠብቆ ያቆዬ ዎላይታ ላይ አንዲህ አይነት አፍ ሲከፍት በእውነት ያማል ይላሉ።

ዎላይታ እንደ ዛሬ በርካታ የአከባቢው ተወላጆች የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተከታይ ሳይሆኑ በፊት ዳሞታ ተራራ አናት ላይ፣ ያክማ ላይ፣ ዱጉና ፋንጎ እንዲሁም በሌሎች ቦታ ላይ የቤተክርስቲያኗን ጥንታዊ ቅርስ ከእነ ክብሯ ጠብቆ እስከዛሬ ድረስ በሀይማኖት መቻቻል የዘለቀውን አከባቢው ሰው ይቅርና ፈጣሪ እንኳን የሚመሰከርለት ሀቅ ነው።

ዎላይታኮ ለዚህች ቤተክርስቲያን በየትኛውም አከባቢ ባልተለመደ ሁኔታ በዋና ከተማዋ መሀል ላይ ትልቅ ገዳም ያበረከተ ከእነ ታሪካዊ ቅርሶቿ በክብር ጠብቆ ለዚህ ትውልድ ያስረከበ ስለመሆኑ እየታወቀ በጥቂት ክስተት በዚህ ህዝብ ላይ እንዴት አፍ ለመክፈት ድፍረቱን እንዴት አገኙ በሚል ይሞግታሉ።

ዎላይታ የጥንት ታሪክ ማውራት ይቅርና በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት አመታት የፓለቲካ ጥያቄዎች ወጥሰት ተከትሎ በየቦታው ቤተክርስቲያን እና መስጊዶች ሲቃጠሉ፣ ምዕመናን ሲገደሉና ሲሰደዱ በአከባቢው የሚገኙ የትኛውም ሀይማኖት ተቋማት ላይ ሆነ ምዕመናን ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስ ከጥንት ጀምሮ በሚታወቀው ሰላማዊ አከባቢ ላይ በዚሁ ልክ አካሄድ አጀንዳ ለማድረግ ለምን ተፈለገ ?

ዎላይታ ሀይማኖት ብቻ ሳይሆን ከየትኛውም አከባቢ የመጣ ብሄር ተወላጅ ከአከባቢው ተወላጆቹ በላይ ተከብረው፥ የትኛውንም ስራ ሰርቶ ያለምንም መገለልና ስጋት ተከብረው ተቻችለው በፍቅር የሚኖሩበት ስለመሆኑ በህዝቡ ውስጥ እየኖረ በአይኑ እያየ ለምን እንዲህ በቀላል ንግግር ከአባቶችና ከሚመለከተው የመንግስት አካል ተነጋግረው መፍታት በሚችለው በአንድ ጥቃቅን ክስተት ባለውለታ በሆነ ህዝብ ላይ ለምን ?! ይላሉ።

ዎላይታ የእነ ቅዱስ አቡነ ተ/ኃይማኖት፣ የእነ አባባ ዋንዳሮ ምድር፣ የእነ አቡኔ ጴጥሮስ ምድር፣ የእነ ቢሾፕ ዳዊት ጦሼ ምድር፣ የእነ ዶክተር ዮሐንስ ባሳና እንዲሁም የበርካታ ሀይማኖቶች ከጥንት ጀምሮ በመቻቻልና በሰላም የቆዬ ምድር ላይ በጥቃቅን ግለሰባዊ ክስተቶች ሰበብ ከታላቅ ክብር ከፍታ ማውረድ ከቶም አይቻልም❗️ሰላም ለሰው ዘር ሁሉ እንላለን❤

UpdateNews

ይቅርታ ጠየቁ !! February 18, 2025

የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዎላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት መላከሰላም ቀሲስ ቦክቻ ኤንጋ የልጃቸው ሞባይል ቀፎ መሰረቁን ተከትሎ በማህበራዊ ሚዲያ የለጠፉት መልዕክት በኦርቶዶክስ ምዕመናንን ጨምሮ በአከባቢው በርካቶች ዘንድ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ ከደቂቃዎች በፊት ይቅርታ ጠይቀዋል።

በዚሁ ይቅርታ መልዕክታቸው “በጥቂት ግለሰቦች ምክንያት ብዙኃኑን የነካ ስለሆነ ይቅርታ እንድጠይቅ በመከሩኝ ምክር መሠረት ቅር የተሰኛሁ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ይቅርታ እንድታደርጉልኝ እጠይቃለሁ” ብለዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia