በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት እየሸፈነ በሚገኝው ማከፋፈያ ግንባታ ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዎላይታ ሪጅን ፕሮጀክት ማስተባበሪያ አስታወቀ።
ኢትዮጵያ ከዎላይታ የሀገሪቱን ከፍተኛውን ኤለክትሪክ ኃይል ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር በየዓመቱ ከ86 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለውጭ ሀገራት ሀገራት በመሸጥ ታገኛለች።
በሌላ በኩል በዚሁ በሀገሪቱ ከፍተኛ ኤለክትሪክ ኃይል ማመንጫ ዎላይታ ላሾ ፓውር ስቴሽን “በቀጥታም በዘዋዋሪም አከባቢውን ማህበረሰብ ረጅም ጊዜ ከቆዩ የጤና ጉዳት ይደርስባቸዋል” በሚል በተጠናው ጥናት መነሻ በዙሪያው ለሚገኙ ነዋሪዎች የካሳ ክፊያ የተወሰነ ቢሆንም የዘርፉ ባለሙያዎች ከጉዳቱ አንፃር ለነዋሪዎቹ ከፍተኛ ትኩረትና ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ቢያሳስቡም እስካሁን ትኩረት ተነፍገዋል።
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኤለክትሪክ አገልግሎት የዎላይታ ሪጅን ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተዘራ ታደሠ የዎላይታ ሶዶ ቁጥር 2 ኃይል ቋት ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ ሲከናወን ከመኖሪያ ቀያቸው የተነሱ 1 ሺህ 650 ነዋሪዎቹን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ 61 ኪ.ሜ የዝቅተኛ እና 21 ነጥብ 23 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ መከናወኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም 27 ባለ 15 ኪ. ቮ. አ ትራንስፎርመሮች መተከላቸውን ጠቅሰው ቀሪ አራት ትራንስፎርመሮች ለመትከል እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው ነዋሪዎቹን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ 200 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ ጠቅሰው የወጪው 40 በመቶ በተቋሙ የተሸፈነ ሲሆን፤ ቀሪው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የተሸፈነ ነው ብለዋል፡፡
ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሆኑት የዋጃ ሾያ፣ የዋራዣ ላሾ ሱታ፣ የጉርታንጆ፣ የቁጦ፣ የሻምባ ቅሌና፣ የላሾ ከተማ፣ የጉርሞ ወይዴ፣ የዋጃ ቄሮ ቀጠና 1፣ 2 እና 3 እንዲሁም የዳሞት ዋጃ ቀጠና 1 እና 2 ቀበሌ ነዋሪዎች መሆናቸውን አስረድተው ዝርጋታውን በስድስት ወራት ለማጠናቀቅ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም በትራንስፎርመር ግብዓት እጥረት ምክንያት ዝርጋታው ከተያዘው ግዜ በላይ መውሰዱን ጠቅሰዋል፡፡
ቢሆንም በዚሁ የዘርፉ ባለሙያዎች “ከጉዳቱ አንፃር ለነዋሪዎቹ ከፍተኛ ትኩረትና ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት ቢያሳስቡም እስካሁን ትኩረት ተነፍገው ባሉበት በአከባቢው ሰዎች በጤንነታቸው ላይ ቀጥታ ለሚደርሰው ጉዳት በሚል ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ በካሣ የተሰጠው ትንሿ ድጋፍም ለተጎጂዎች ሳይደርስ አብዛኛው በአመራሮቹ እጅ ገብቷል” ስሉ የአከባቢው ነዋሪዎች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አቤቱታ ገልጿል።
ክፍያውን ቀጥታ ለግለሰቦች መስጠት ስገባ ለመንግሥት አካላት በአደራ መልክ በመሰጠቱ ለተወሰኑት ተስጥተው ገንዘቡን የተከለከሉ የአከባቢው ሰዎች እስከ ዞን ድረስ በተደጋጋሚ በአካልና በደብዳቤ ቢጠየቁም ምላሽ ማግኘት እንዳልተቻለ አክለው ተናግሯል።
በጉዳዩ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ በተለያዩ መንገዶች ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው ባይሳካም ምላሽ ካገኘን እናደርሳለን።
ይሄው በኢትዮጵያ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት እየሸፈነ የሚገኝው በዎላይታ ዞን በኡማ ወንዝ ላይ የተገነባው ( ጊቤ_3 1887 MW ) ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ለአዲስአበባ ዋና ማከፋፈያና ለኬኒያ እና ታንዛኒያ ቀጥታ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያስተላልፍ ዎላይታ ዞን ላሾ ቀበሌ የሚገኝ የኤሌክትሪክ የኃይል ቋት ማዕከል ለሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ገንዘብ የሚያስገኝ ኤለክትሪክ ሽያጭ ለታንዛኒያ መቅረቡ ይታወቃል።
የምስራቅ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ሀይዌይ ( East Africa Electric Highway ) ፕሮጀክት አካል የሆነውና በግቤ 3 ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ከዎላይታ ላሾ ኃይል ማከማቻ ቀጥታ ወደ በኬንያ ወደ ታንዛንያ የተዘረጋው ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመር የሙከራ የኃይል አቅርቦት መጀመሩን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቀው ነበር።
የምስራቅ አፍሪካ ኤሌክትሪክ ሀይዌይ ፕሮጀክት የመጀመሪያው የኃይል ትስስር በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል ተከናውኖ የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ክፍል በኬኒያና በታንዛንያ መካካል የተዘረጋው ባለ 400 ኪሎ ቮልት የኃይል አቅርቦት በመጀመሪያዎቹ የግብይት ዘመናት በዓመት ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ የሚያስገኝ ሲሆን ለኬንያም ከዚሁ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በአመት ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ እያገኘ እንደሆነ ይታወቃል።
ነገር ግን “ከመላው ኢትዮጵያ አልፎ እስከ ጎረቤት ሀገራት ድረስ ብራሃን እየሰጠ ለራሱ ተገቢ ካሳ ሳይሰጥ አርሶ ከሚበላበት መሬቱ ተፈናቅለው የሀገሪቱን የኃይል ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር ከ86 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ከውጭ ሀገራት ሺያጭ የሚያስገኝ ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክት ያስገነባው ህዝብ እስከመቼ በጨለማ ይቆያል? በዓመት ከ50 ኢንዱስትሪ ፓርክ በላይ መገንባት የሚያስችል ገቢ የሚያስገኝ ፕሮጀክት ባለቤትና ጠባቂ የሆኑት ልጆቻቸው በየከተማው ጎዳና ላይ እየተሰቃዩ አንድ ኢንዱስትሪ ፓርክ እንኳን ስጠየቅ በዝምታ እስከመቼ ? ግድቡ ስጠናቀቅ ለዎላይታ ሶዶ ከተማ እና አከባቢው ከ50 MW በላይ ለመስጠት የተገባው ቃል ለምን ታጠፈ?” የሚሉ ድምፆች ከፍ ብለው ይደመጣሉ።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia #Wolaita
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው