1000038396

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባለስልጣናት የፋና ምርመራ ዘገባ እንዳይተላለፍ ከፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ ለማውጣት እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተገለፀ።

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደረገው የማዕድን ምዝበራ እና የአሰራር ጥሰት በተመለከተ የፋና ሚዲያ ዝርዝር የምርመራ ዘገባ ከሰራ በኋላ፣ የክልሉ ባለስልጣናት ጫና አድርገው ዘገባው ለህዝብ እንዳይቀርብ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለማሳገድ እየተንቀሳቀሱ እንደሆነ የተለያዩ ምንጮች ለዎላይታ ታይምስ ገልጸዋል።

ይህ በክልሉ አመራሮች በፍትህ ተቋማት አሰራር ጭምር ጠልቃ ገብነት እርምጃ በሕገ-ወጥ መንገድ ዜጎችን የመረጃ መብት እንዲሁም የፕሬስ ነፃነትን በመገደብ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደሆነ በሚዲያ ባለሙያዎች ዘንድ ጥያቄ ፈጥሯል። 

ፋና ሚዲያ በክልሉ የተከሰቱትን የማዕድን ምዝበራ ጋር በተያያዘ ዝርዝር ምርመራ አዘጋጅቷል። ይሁን እንጂ፣ ዘገባውን ሙሉ በሙሉ ለህዝብ ከማቅረብ በፊት የክልሉ አስተዳደር በከፍተኛ ደረጃ ጫና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ አማካኝነት የሚዲያውን ምርመራ ዘገባ ለማሳገድ እየሞከረ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። 

“ይህ የሚዲያ ነፃነት ጥሰት ነው፤ የህዝብ መብትም ጉዳይ ነው። እውነት ሊደበቅ አይችልም” በተጨማሪም፣ ፋና ሚዲያ በተለይ እንደ ሚዲያ ገለልተኛ ዘገባ ማቅረብ የሚገባው መሆኑን በተጨባጭ ማረጋገጥ አለበት” በማለት አንድ የሚዲያ ባለሙያ በስም ሳይገለጽ ለዎላይታ ታይምስ ተናግሯል።

የክልሉ አመራሮች በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ የሚያሳድረውን ጫና በፍጥነት መቆምና መፍትሄ ማግኘት እንዳለበት ነው። “የፍርድ ቤት ትዕዛዝ የሚሰጠው ሕግን ለመጠበቅ እንጂ፣ የህዝብን ጥቅም የሚያጠላ መሳሪያ ሊሆን አይገባም” በማለትም አስረግጠዋል። 

አክለውም “ህዝብ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ስለሚከናወኑ ተግባራት የማወቅ መብት አለው። የማዕድን ምዝበራ እና የአሰራር ጉድለት ጉዳይ የህዝብን ጥቅም የሚነካ በመሆኑ፣ ግልጽነት ሊሰፍንበት ይገባል። በምዝበራው እና በአሰራር ጉድለቱ ውስጥ የተሳተፉ ባለስልጣናት ተጠያቂ መሆን አለባቸው” ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስተዳደር በሚዲያ ነፃነት ላይ የሚያደርሰው ጫና የሕግ በላይነትን እና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን የሚያጠላ በመሆኑ ፋና ሚዲያ በመንግስት ውስጥ ቢሆንም፣ ገለልተኛነትን በማስከበር የህዝብን መብት እንዲያከብር ጥሪው ቀርቧል።

እንደ መረጃው ከሆነ የዚህ ጉዳይ አስፈፃሚ ተብሎ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለው ግለሰብ ፍፁም ታዬ የሚባል ከአመራሮቹ ጋር በጥቅም የተሳሰረ እንደሆነ አረጋግጠናል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

#Ethiopia #southethiopia