1000038725

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ

በኢትዮጵያና ኬንያ አዋሳኝ በቱርካና ሀይቅ ዳርቻ በቶዶንያንግ የድንበር መሻገሪያ ቦታ ላይ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ ታጣቂዎች በትናንትናው ዕለት በኬንያ ዓሣ አጥማጆች ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈጸም ከ20 በላይ ዓሣ አጥማጆች መገደላቸውን የኬኒያ ሚዲያዎች እየዘገቡ ይገኛሉ።

ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት “ከባድ መሳሪያ የታጠቁ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳሳነች ሚሊሻዎች ዓሣ አጥማጆቹ በቱርካና ሀይቅ ላይ በሚሰሩበት ወቅት አካባቢውን በመውረር በዘፈቀደ ተኩስ ከፍተዋል” ይላል።

በጥቃቱ በርካታ ሰዎች ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት አለ። ከአካባቢው ፖሊስ የወጡ ተጨማሪ ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ጥቃቱ ቅዳሜ ማለዳ በቱርካና ውስጥ አንድ የታወቀ ሽፍታ ሶስት የዳሳነች ዓሣ አጥማጆችን በመግደሉ ምክንያት የተፈጸመ የበቀል እርምጃ ሊሆን ይችላል።

ከጥቃቱ በኋላ የተናገሩት የቱርካና ሰሜን የፓርላማ አባል ኤክዎን ናቡይን የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ለዚህ ክስተት ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀው ክስተቱን “እልቂት” ሲሉ አውግዘዋል። እንደ ፓርላማ አባሉ ገለጻ ሁኔታው “በጣም የከፋ” ሲሆን አዳኞች የቶዶንያንግን ህዝብ ለመጠበቅ በፍጥነት እንዲንቀሳቀሱ አሳስበዋል።

“የውስጥ ጉዳይ እና ብሔራዊ አስተዳደር ሚኒስቴር በዳሳነች ሚሊሻዎች በቱርካና ሀይቅ ቶዶንያንግ አካባቢ ከ20 በላይ ዓሣ አጥማጆች መገደላቸውን የሚያሳዝኑ ሪፖርቶችን እየደረሰን ነው። ቁጥሩ ከዚህም ሊበልጥ ይችላል” ሲሉ ናቡይን ተናግረዋል።

“ሁኔታው በጣም የከፋ ነው፣ አዳኞች ህዝባችንን ለመጠበቅ በፍጥነት መንቀሳቀስ አለባቸው። እልቂቱ በኬንያ ምድር ላይ እየተፈጸመ ነው፣ በደንብ በታጠቁ ሚሊሻዎች (ዳሳነች) የተያዘው።” ሲሉም አክለዋል። ክስተቱ ትናንት ቅዳሜ ምሽት በሎፔይሙካት እና ናቲራ በኬንያ-ኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በኦሞ ወንዝ አቅራቢያ ተከስቷል።

በጥቃቱ አምስት ጀልባዎች ተደብድበው በጀልባዎቹ ላይ የነበሩት በሙሉ ተገድለዋል። አጥቂዎቹ ከዓሣ አጥማጆቹ ሦስት የጦር መሣሪያዎችን ወስደዋል። ይሁን እንጂ አንዳንድ የተረፉ ሰዎች ተርፈው ወዲያውኑ በሎፔይማካቴ አለቃ ጥበቃ ስር ተደርገዋል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከስታንዳርድ ሚዲያ ያገኘውን መረጃ እንደሚያመለክተው “በቱርካና ካውንቲ ኮሚሽነር አቶ ጁሊየስ ካቪታ የሚመራው የቱርካና ካውንቲ የጸጥታ ቡድን በአሁኑ ሰዓት በኬንያ እና በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ቶዶንያንግ ላይ ይገኛል።

የዚህ ክስተት በተመለከተ እስካሁን ከኢትዮጵያ መንግስት ሆነ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኩል በይፋ የተባለ ነገር የሌለ ሲሆን ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለማጣራት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Kenya