በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ዘገባ ነው
በአትክልተኝነትና በፅዳት ስራ በወር 9 መቶ ብር ደመወዝ የሚያገኙ ሰራተኞች “የመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ውድነት ማካካሻ ተከልክለናል” ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል “መንግስት የኑሮ ውድነትን በተወሰነ ለመቅረፍ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች ላይ ትኩረት አድርጎ ያደረገውን የደመወዝ ማሻሻያ ደንቡን በመጣስ ለኮንትራት አልተፈቀደም በማለት የተፈቀደውን መነሻ ደመወዝና ውዝፍ ክፍያ ተከልክለው ያሉበት ቢሮ የመጨረሻው የርዕሰ መስተዳድሩ በመሆኑ መሄጃ አጥተናል” ሲሉ የሰራተኞቹ ተወካዮች ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አቤቱታ ገልጸዋል።

ቅሬታ ለየትኛው ቢሮ አቅርባችሁ ነበር? የቅሬታ ደብዳቤ የተፃፈ ካለ? የተሰጣቸው ምላሽ አለ? አሁን ሰራተኞች ስራቸውን እየሰሩ ነው ወይ? በኮንትራት ሲቀጠሩ በምን ውል ነበር የገቡት ? በየትኛው መስሪያ ቤት አማካይነት ነው ማስታወቂያ ወጥቶ በኮንትራት የገቡት ? በሚል ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ጠይቆ ምላሽ ሰጥቷል።
እንደ ሰራተኞቹ ገለፃ ከሆነ “የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተመሠረተበት ቀን ጀምሮ በአትክልተኝነትና በቢሮ ፅዳት በኮንትራት ቅጥር ከ1 ዓመት በላይ ደከመን ሰለቸን ሳይሉ በ1,100/አንድ ሺ አንድ መቶ /የሥራ ግብር ተቀናንሶ 900/ዘጠኝ መቶ ብር እየተከፈለ እያገለገሉ የቆዩ ሠራተኞች ከርዕሰ መስተዳድር ቤተመንግስት እስከ የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛሉ” ብለዋል።
“በደሉ የተፈፀመው የክልሉ ቁንጮ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ስለሆነ ወደማን እንሄዳለን ? በፅሑፍ የመጠየቅ አቅም ያለን አይደለም ደግሞም እንፈራለን። የኮንትራት ውል በተመለከተ በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤትና በእያንዳንዳቸው ሠራተኞች መካከል በየ 6ወር የሚታደስ ሆኖ የተፈረመ እንደሆነም” አስተባባሪዎቹ አስረድተዋል።
በተጨማሪም “ቅሬታችንን ለጽ/ቤቱ አመልክተው አስተዳደርና ፋይናንስን አነጋግሩ ብሎ ወደ አስተዳደር ፋይናንሰ ሄደው ጠብቁ በማለት ከቢሮው እንዲወጡ ብቻ ተናግሮ ፀጥ ማለታቸውን ገልፀው ሠራተኞቹ በተመሳሳይ አዲስ የተደራጀው ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለኮንትራት ሠራተኞች ያለምንም ልዩነት የከፈለ መሆኑን ለማረጋገጥ ችለናል፤ ይህ ድርጊት ሆን ተብሎ መኖር ስያቅታቸው ሥራ እንድለቁና በሌሎች በሚፈልጓቸው ሰዎች ለመተካት ታስቦ እንደሆነ መታወቅ አለበት” በሚል ተማፅኖአቸውን አሰምተዋል።
ከሰራተኞቹ ቅሬታ መነሻ ከሚመለከታቸው አካላት ምላሽና ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ቢሆንም ምላሽ ሲገኝ መረጃውን እንደምናደርስ ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን።
ሆኖም ግን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ውድነት ማካካሻ የደመወዝ ማስተካከያ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 77/2017 ተራ ቁጥር 9 ላይ የሰራተኞቹ ቅሬታ ትክክለኛ ስለመሆኑ አረጋግጠናል።


ይሄው መመሪያ በማያሻማ ሁኔታ፦ “በቢሮው ተመዝኖ ደረጃ በወጣለት ወይም በቋሚ የሥራ መደብ ላይ መመሪያውን ተከትሎ የተቀጠረ ጊዜያዊ ወይም የኮንትራት ሠራተኛ ወይም በሚመለከተው አካል በተፈቀደ የፕሮጀክት ደመወዝ ወይም ልዩ የደመወዝ ስኬል የተቀጠረ ጊዜያዊ ወይም የኮንትራት ሰራተኛ ደመወዝ ማስተካከያ ተጠቃሚ ይሆናል” ይላል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏
#Ethiopia #southethiopia
የ