ኢትዮጵያ እና ኬንያ ድንበር በተፈጠረው ግጭት የ13 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ህይወት መጥፋትና የንብረት ዘረፋ መፈፀሙ ተገለፀ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዳሰነች እና በሰሜን ኬንያ ቱርካና የድንበር አከባቢ የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው የገቡ የቱርካና ታጣቂ የሚልሻ አባላት አርብቶ አደሮች ባደረሱት ጥቃት የ13 ንፁሀን ዜጎች ህይወት ሲያልፍ 3 ሰዎች በከፍተኛ የህክምና ክትትል ላይ እንደሚገኙ አቶ ታደለ ሀቴ የዳሰነች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተናግረዋል።

“ከየካቲት 12 ቀን 2017 ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው የገቡ የተደራጁ የመንግሥት ታጣቂ የሚልሻ አባላት ተከታታይነት ባለው ሁኔታ በተለያዩ አከባቢዎች ባደረሱት ጥቃት በአከባቢው ከፍተኛ ውድመት ደርሷል” ብለዋል።
የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው የገቡ የኬንያ ቱርካና የመንግሥት ታጣቂ የሚልሻ አባላት የሆኑ አርብቶ አደሮች ባደረሱት ጥቃት 12 ሰዎች ጥቃቶቹ በተፈፀሙት በስየስ እና በቀቸም አከባቢ ህይወታቸው ሲያልፍ 2 ተጎጂዎች ለከፍተኛ ህክምና ወደ ጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ቢጓዙም 1 ተጎጂ በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል ህክምናውን እየተከታተለ ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉን ዋና አስተዳዳሪው አስረድተዋል።
በደረሰው ጥቃት በአጠቃላይ የ13 ንፁሀን ዜጎች ህይወት ሲያልፍ በ3 ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሶ በአሁኑ ወቅት 1 ተጎጂ በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል እንዲሁም 2 ተጎጂዎች በኦሞራቴ ጤና ጣቢያ የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።
በጥቃቱ 6 የአሳ ማስገሪያ ጀልባ፤ ከ120 በላይ የአሳ ማጥመጃ መረብ፤ ለምግብነት የሚውል የደረቀ አሳ (ቆሮሶ) በአከባቢው ከነበሩ የንግድ ማህበረሰብ የኢትዮጵያ 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ተዘርፏል።
በደረሰው ጥቃት ህይወታቸው ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች መፅናናትን እየተመኘን በህክምና የሚረዱ ዜጎች በፍጥነት እንዲያገግሙ ተመኝተዋል።
በሌላ በዚሁ ጥቃት ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያና ኬንያ አዋሳኝ በቱርካና ሀይቅ ዳርቻ በቶዶንያንግ የድንበር መሻገሪያ ቦታ ላይ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ ታጣቂዎች ከትናንት በስቲያ በኬንያ ዓሣ አጥማጆች ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈጸም ከ20 በላይ ዓሣ አጥማጆች መገደላቸውን የኬኒያ ሚዲያዎች እየዘገቡ ስለመሆኑ የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ መዘገቡ ይታወሳል።
የዚህ ክስተት በተመለከተ እስካሁን ከኢትዮጵያ መንግስት ሆነ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኩል በይፋ የተባለ ነገር የሌለ ሲሆን ዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ለማጣራት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏