1000039166

የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ ሦስት የቀድሞ የአፍሪካ መሪዎች የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጦርነት መፍትሔ ለማምጣት እንዲያስችል የሰላም ሂደትን እንዲያመቻቹ ተመረጡ።

የምሥራቅ አፍሪካ ማኅበረሰብ እና የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማኅበረሰብ የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሰላም ሂደትን እንዲያመቻቹ የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ ሦስት የቀድሞ የአፍሪካ መሪዎችን መርጠዋል።

የሰላም ሂደቱን እንዲያመቻቹ የተሰየሙት የቀድሞ የአፍሪካ መሪዎች ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ በተጨማሪ የቀድሞው የኬኒያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ እና የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ናቸው።

በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰላም ለማምጣት በተናጠል ሲካሄዱ የቆዩ የናይሮቢ እና የሉዋንዳ የሰላም ሂደቶች ተዋህደው ሂደቱ በቀድሞዎቹ መሪዎች የጋራ አመቻቺነት እንዲቀጥል መወሰኑን የሲጂቲኤን ዘገባ አመላክቷል።

ይህ ውሳኔ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ) እና የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳዲክ) መሪዎች በጋራ ባደረጉት ስብሰባ የተገኘ ሲሆን ይህም ከዚህ ቀደም የነበሩትን የተለያዩ የሰላም ጥረቶች ወደ አንድ ወጥ አካሄድ ያዋህዳል።

አዲሱ የተዋሃደው ሂደት ከዚህ ቀደም ኬንያታ ይመሩት የነበረውን የኢኤሲ “የናይሮቢ ሂደት” ከአንጎላ ባስተባበረችው የአፍሪካ ህብረት ተነሳሽነት “የሉዋንዳ ሂደት” ጋር ያጣምራል።

በምስራቅ ዲ.አር.ሲ ያሉ ታጣቂ ቡድኖች መሳሪያቸውን እንዲያስቀምጡ ማበረታታት፣ እርስ በርስ አማፂ ቡድኖችን ይደግፋሉ በሚል ክስ በዲ.አር.ሲ እና ሩዋንዳ መካከል ያለውን እየጨመረ የመጣውን ውጥረት መፍታትን ያለመ ነው ተብሏል።

የእነዚህ ታዋቂ የአፍሪካ መሪዎች መሾም ቀጣይነት ላለው ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት የክልሉን ቁርጠኝነት የሚሳየው ሲሆን ልምዳቸው እና ዲፕሎማሲያዊ እውቀታቸው በችግር በተሞላው ክልል ውስጥ ውይይትን ለማበረታታት እና ሰላምን ለማስፈን ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #Africa #DRC