ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሚዋሰኑበት ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን ከፍተኛ የመንግሥት እና የፀጥታ መዋቅር አመራሮች በተገኙበት የውይይትና የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ በአቶ ወገኔ ብዙነህ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ኢትዮጵያ እና ኬንያ በሚዋሰኑበት የድንበር አከባቢ ከየካቲት 12 ቀን 2017 ጀምሮ የተፈጠሩ ግጭቶቸን ለመፍታትና በድንበር አከባቢው ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን በኬንያ ቱርካና ካውንቲ የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጁሊያስ ካቪላ ከተመራ የካውንቲው ከፍተኛ የመንግሥት እና የፀጥታ መዋቅር አመራሮች ጋር የውይይትና የምክክር መድረክ በቀን 18/06/2017 ዓ/ም ተካሂዷል።
ኢትዮጵያ እና ኬንያ ጠንካራ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን የኬንያ ቱርካና ካውንቲ የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጁሊያስ ካቪላ አስታውሰው አልፎ አልፎ በድንበር አከባቢ በሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተፈጥሮ ሀብት አጠቀቀምን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች እንደሚስተዋል ገልፀው ችግሮች በጋራ ትብብር በመፍታት በድንበር አከባቢው ዘላቂ ሠላምን በማስፈን የየሀገራቱ ዜጎች ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዲፈጥሩ መስራት ይገባናል ሲሉ ኮሚሽነር ጁሊያስ ካቪላ ተናግረዋል።
በድንበር አከባቢ ጠንካራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ሥራዎችን በመስራት የሚከሰቱ መሰል ግጭቶችን መከላከል እንደሚቻል በውይይት መድረኩ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ ገልፀው በአከባቢው ዘላቂ ሠላምን ለማስፈን በክልሉ መንግሥት ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
አቶ ወገኔ በንግግራቸው እንደገለፁት የተፈጥሮ ሀብትን መሠረት ያደረጉ ግጭቶችን ለመፍታት በጋራ ትብብር ልንሰራ ይገባል ሲሉ አሳስበው ጠንካራ የመረጃ ቅብብሎሽ ሥርዓትን በመዘርጋት የሚፈጠሩ ግጭቶች የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ መከላከል እንደሚቻል ኃላፊው ተናግረዋል።
በሁለቱ ሀገራት የድንበር አከባቢ የተፈጠሩ ግጭቶችን በፍጥነት በመፍታት አከባቢው ወደነበረበት ሠላም ለመመለስ በጋራ ለመስራት የሁለቱ ሀገራት የየክልል ከፍተኛ የመንግት አመራሮች ከመግባባት ደርሰዋል።
ከወረዳው ኮሙዩኒኬሽን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በውይይት መድረኩ ከኢትዮጵያ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ወገኔ ብዙነህ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏