1000041752

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ ||

በደቡብ ኢትዮጵያ ጌዴኦ ዞን የይርጋጨፌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በርካታ የጤና ባለሙያዎች መታሰራቸው ተገልጿል።

በአሁኑ ስዓት በሆስፒታሉ በርካታ ታካሚዎች በባለሙያዎች እጥረት ችግር ውስጥ መግባታቸውም ስማቸውን መንገር ያልፈለጉ ከፍተኛ የሆስፒታሉ ባለሙያ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አረጋግጠዋል።

የጤና ባለሙያዎቹ የታሰሩት ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ የደመወዝ ጭማሪ የይርጋጨፌ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለመክፈሉ የመብት ጥያቄ በመጠየቃቸው አሁን ላይ እስር ቤት መሆናቸው ተሰምተዋል።

በጌዴኦ ዞን በተለያዩ ጊዜያት በጤና ባለሙያዎች በተከታታይ መብታቸውን ጠይቀው ወዳልተፈለገ ነገሮች በመውሰድ በእስር እየተዳረጉ መሆናቸው አንድአንድ የጤና ባለሙያዎች ጠቁሟል።

ስራ እንኳን እንዳይበደል በወክሎቻቸው ባቀረቡት ጥያቄአቸውን በፍጥነት እና በቅንነት ተቀብሎ ቶሎ ማስተናገድና መመለስ እንዲሁም ማረጋጋት ሲጠበቅበት የጌዴኦ ዞን አስተዳደር ጉዳዩን ከምንም እንደማይቆጥሩ ተገንዝበዋል።

በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ላይ በከተማዋ ከንቲባ እና በሆስፒታሉ ቦርድ ስብሳቢ እየተፈጸመ ያለው የባለሙያዎች ጅምላ እስር መቆም አለበት ብለዋል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከስፍራው እንዳረጋገጠው ከ10 ቀናት በፊት የታሰሩት አብዛኞቹ የጤና ባለሙያዎች ፍርድ ቤት ያልቀረቡ ሲሆን በዚሁ ምክንያት 4 የሚሆኑ ዶክተሮች ደግሞ ትላንት የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብቶ መውጣታቸው መነጋገሪያ ሆኗል።

በጉዳዩ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እንዲሰጡ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia