1000042775

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ የተጠናቀረ

ሙሹራና ሙሽሪትን በመጠባበቅ ላይ የነበሩ ግለሰቦች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ያደረሰው መንግስት አመራር ከማረሚያ የፍርድ ሂደት እየተከታተለ መሆኑ ተገለፀ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ይርጋጨፈ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ሚጁ ያለመንጃ ፈቃድ የመንግስት መኪና እያሽከረከረ ለሶስት ሰው ሞት፣ ለ8 ሰዎች ከባድ ጉዳት እንዲሁም ከ20 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ከወረዳው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

እንደ መረጃው ከሆነ “ዛሬ ሀገርምድር ሠላም ብለው ቤተ ዘመድ ተጠራርተው ሠርግ ላይ ሙሹራና ሙሽሪት በመጠባበቅ ላይ እያሉ ዝናብ በመዝነቡ ዱንኳን ውስጥ ተጠልሎ በነበሩ ሰዎች ላይ ልምምድ ብሎ ዋና ሾፌሩን በአጠገቡ አስቀምጦ እየተለማመደ የነበረው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ድንኳን ጥሶ በመግባት በሰው፣ በንብረት ከፍተኛና ከባድ አደጋ በማድረስ ሠርጉን ወደ ለቅሶ፣ ደስታን ወደ ሀዘንና በመቀየር ትልቅ አደጋ አድርሰዋል” ሲል አንድ የሟች ቤተሰብ አስረድተዋል።

የወረዳው አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ሚጁ በትናንትናው ዕለት ፍርድቤት ቀርበው የጥፋተኝነት ወሳኔ መተላለፉንና ውሳኔ ለመስጠት ቀጠሮ መያዙንም ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አክለው ገልጸዋል።

ዋና አስተዳዳሪው እና ሾፌሩ በአሁኑ ወቅት በማረሚያ የሚገኙ ቢሆንም የስልጣን ትውውቅና ጥቅም ትስስር ተጠቅሞ የሟቾች ቤተሰብ ፍትህ እንዳያገኙ፣ የተጎዱት ተገቢ ካሳ እንዳያገኙ በፍርድቤት ላይ ጫና እያሳደሩ እንደሆነ ተናግሯል።

በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት፦ ዋና አስተዳዳሪው የመንግሥትን ስልጣን ተገን በማድረግ ያለመንጃ ፈቃድ የመንግስት መኪና እያሽከረከረ ለ3 ሰዎች ሞት፣ ለ8 ሰዎች ከባድ ጉዳት እንዲሁም ከ20 በላይ ሰዎች ላይ ጉዳት እንዲደርስ ያደረገው ተገቢ ውሳኔ እንዲያገኝ ክትትል እንዲያደርጉ ቤተሰቦቹ ተማፅነዋል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Gedio