
የመጪው ምርጫ ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን በሚያስችሉ ጉዳዮች የጋራ ውይይት መካሄዱን የዎላይታ ዞን አረካ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ
በዛሬው ዕለት በተካሄደው ውይይት የከተማውን ሠላምና ፀጥታ በተመለከተ፤ በከተማው ስላለው ነባራዊ ሁኔታ እና በከተማው ዉስጥ እየተሰሩ ባሉ መሠረተ ልማቶች ዙርያ ጥልቅ ዉይይት ተደርጎል።
ዉይይቱን የመሩት የአረካ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መስፍን ዳዊት እንደተናገሩት የከተማው ሠላምና ፀጥታ ማስጠበቅ የሁሉም ህበረተሰብ ክፋል ተግባር ልሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።
ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር የሚደረገዉ ምርጫ ፍፁም ሠላማዊ፤ ተአማኒ፤ ነፃ እና ፍታዊ ምርጫ እንድካሄድ የከተማው መንግስት በትኩረት እንደሚሰራም አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የከተማው ማህበረሰብ የከተማውን ሠላምና ፀጥታ ከማስከበር አንጻር ከከተማ አመራሮችና ከፀጥታ መዋቅሮች ጋር በመተባበር እያበረከቱ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዉይይቱ የሀገር ሽማግለዎች፤ የሀይማኖት መሪዎች፤ የመንደር ተጠሪዎች፤ ደንብ አስከባሪዎች እና የሦስቱም ክፋለ ከተማ አመራሮች በአጠቃላይ ከ400 በላይ ሰዉ ተሳትፈዉበታል።
በመጨረሻም ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች ክቡር ከንቲባዉ እና የአረካ ከተማ ምክትል ከንቲባና የሠራተኛና ማህበራዊ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ኢያሱ ጩቢሶ ምልሽ በመስጠት ዉይይቱ ተጠናቅቋል ሲል የከተማ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ዘግቧል።