
ነፃ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ገፈፋ ሕክምና በዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲት ማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒታል እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የዎላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒታል ለበርካታ ዓመታት ለወላይታና አጎራባች ዞን ማህበረሰብ በዘመናዊና በተጀራጀ የሕክምና ማሽኖች እና በተለያዩ የጤና ዘርፎች ስፔሻላዝ ባደረጉ፣ በስነ-ምግባራቸው አንቱታን ባተረፉ የጤና ባለሙያዎች ዘረፌ ብዙ የህክምና አገልግሎት እየሠጠ መሆኑ ተገልጿል፡፡
እነዚህን ጤና አገልግሎቶችን ከተለያዩ ሀገራት፣ ድርጅቶችና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የህብረተሰቡን የጤና ችግሮችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመለየት ለማህበረሰቡ ሁለንተናዊ ጤና ከመቸውም ጊዜ በላይ በትኩረት ይሰራል፡፡
የዚሁ ማሳያ የሆነው የተደራጄ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ገፈፋ ሕክምና ዘመቻ በኦቶና ማስተማሪያ ሪፌራል ሆስፒል ከ27/07/2013 ዓ.ም – 01/08/2013 ዓ.ም ድረስ ከHimeliyan Cataract Project (HCP) ከአሜርካን ሀገር ከመጡ እና በተቋሙ ውስጥ እየሠሩ ከሚገኙ የዓይን ስፔሻሊስት ሀኪሞች ጋር በመተባበር ከ700 በላይ ለሚሆኑ ታማሚዎች የሚሠጥ መሆኑን የዓይን ሕክምና ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መልካሙ ኮራቶ ገልጸዋል፡፡
ሕክምናው በዋናነት ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ ለዓይነ ስውርነት ሊዳርግ የምችለውን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ገፈፋ መሆኑን የዓይን ሕክምና ባለሙያ አቶ ሣሙኤል ዳልጋ ተናግረዋል፡፡ አቶ ሳሙኤል አክለው የዓይን ሞራ ገፈፋ ዘመቻው ቀድም ብሎ በሁሉም አካባቢዎች እስከ ወረዳና ቀበለ ድረስ በመዝለቅ የዓይን ዕይታ ችግር ያለባቸው ወደ ኦቶና በተባለው ቀን መጥተው የነጻ ሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሠፊ ቅስቀሳና ዘመቻ የተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የዳሞት ፉላሳ ወረዳ ነዋሪና የሞራ ግርዶሽ ገፈፋ ሕክምና ተጠቃሚ አቶ ነጋ ሄባና በሽታው ዕድሜ እየገፋ መምጣቱን ተከትሎ ከዓመት በፊት ምንም ህመም ሳይሰማው እየፈዘዘ ለማየት እንደተቸገረና በኃላም ዕይታውን እንዳጣ ተናግሮ በሆስፒታሉ በኩል በተደረገው ቅስቀሳ በቀበሌ ደረጃ ሰምተው ወደ ተቋሙ በመምጣት ህክምናውን ካገኘ በኃላ እፎይታን ማግኘቱን በመግለጽ ለተደረገለት አገልግሎት ለተቋሙ ምስጋና አቅርቧል፡፡
ከሞሊ ሙንኢሣ የመጣችው ታካሚ ወ/ሮ ታልጎሬ ዳና እርጅናን ተከትሎ ከታህሣሥ ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ የግራ ዓይን ዕይታ እየቀነሰና በከፍተኛ የሕመም ስሜት ስትሰቃይ እንደነበረች ተናግራ በተደረገለት የሞራ ግርዶሽ ገፈፋ ሕክምና ከህመም ስቃይ የዳነች መሆኑዋን ገልጻለች፡፡
የዎለይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒል ከመማር-ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ባሻገር በዘመናዊ መልክ በተደራጁ የሕክምና መሣሪያዎች ፣ በሙያቸው አንቱታን ባተረፉና በመልካም ሥነ-ምግባር በታወቁ ስፔሻሊስቶች ዘርፌ ብዙ የጤና አገልግሎቶችን እየሠጠ ይገኛል በመሆኑ ሕክምናው እስከ 01/08/2013 ዓ.ም ስለሆነ ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያሳስባል ሲል ሆስፒታሉ ኮሙኒኬሽን ዩኒቲ ዘግቧል።