1000045287

በጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከ3 ወራት በላይ ተሰርቆ ተደብቀው የነበረው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ይፋ ሆነ።

የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቅርንጫፍ ማዕከሉ በዎላይታ ሶዶ እንዲከፈት የዎላይታ ዞን አስተዳደርን በትናንትናው ዕለት የጠየቀው ደብዳቤ ይፋ ከሆነ በኃላ ማምሻውን በክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በኩል ሌላ ለወራት ተደብቆ የነበረው ደብዳቤ ይፋ መህኑን አረጋግጠናል።

የዎላይታ ታይምስ ሚዲያ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በፌስቡክ በዛሬው ዕለት ይፋ ካደረገው ደብዳቤ እንዳረጋገጠው በክልሉ የኢምግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ቅርንጫፍ ለመክፈት ታህሳስ 8/2017 ዓ.ም በአርባምንጭ ከተማ እንዲከፈት የሚል ሲሆን የዎላይታ ሶዶ ደግሞ በትናንትናው ዕለት መጋቢት 3/2017 ዓ.ም የተፃፈ እንደሆነ ለማየት ችሏል።

ይሄንን ተከትሎ በርካቶች በክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተለቀቀው ከሶስት ወራት በፊት በስርቆት ተፅፎ የተደበቀው ደብዳቤ “ዛሬ ከየትና እንዴት ሊወጣ ቻለ?” በሚል እየጠየቁ ይገኛሉ።

የትኛውም ተቋም ለህብረተሰቡ በቅርበት አገልግሎት እንዲሰጥ የሚደረግ ጥረት የሚበረታታ ቢሆንም በመንግሥት አመራሮች ግልፀኝነት በጎደለው አኳኋን መረጃ ለወራት በመደበቅ ይፋ አለማድረግ ለሚመሩት ህዝብ ካለመታመን ባሻገር መሠል በርካታ ጉዳዮች በድብቅ እየተሰራ እንደሆነ ግልጽ ማሳያ እንደሆነ ያረጋግጣል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita