1742153393490

የአለምአቀፉ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ታላቅ ዓመታዊ ኮንፈረንስ ( ዋራ ቤቴል ) በሰላም ተጠናቀቀ።

የሰላምና መቻቻል ተምሳሌት በሆነችው ሲዳማ ክልል ላለፉት አራት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 34ኛው የአለምአቀፉ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ታላቅ አመታዊ ኮንፈረንስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ምዕመናንና ታላላቅ የሀይማኖት መሪዎችና አባቶች፣ ከተለያዩ ሀገራት፣ ከአጎራባች ዞኖችና ክልሎች አንዲሁም አከባቢዎች የተሳተፉበት በዛሬው ዕለት በሰላም መጠናቀቁ ተገልጿል።

ቤተክርስቲያኗ የሰው ልጅ በሰብአዊነት በፈሪሃ እግዚአብሔር እንዲያድጉ ኮትኩተው ከማሳደግ ጀምሮ ወደ ዘላለማዊ መንገድ እንዲጓዙ ከማደረጉ ባሻገር በሰብአዊ ድጋፍ አቅም ሌላቸው ወገኖች የምትደግፍ ሲሆን በዚሁ በዘንድሮ ኮንፈረንስም በሲዳማ ክልል ዳሌ ወረዳ ዋራ ሜዳ አከባቢው ማህበረሰብ የጤና አገልግሎት የሚውል ጤና ጣቢያ በቤተክርስቲያኗ ተሰርቶ ተመርቋል።

የአለምአቀፉ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ያካሄደው 34ኛው ዋራ ቤቴል ጉባኤ ከመጋቢት 4 እስከ 7/2017 ዓ.ም በነበረው ኮንፈረንስ ምዕመናኑ ለሀገራችን ሰላምና መረጋጋት ለፈጣሪያቸው ፀሎትና ምልጃ ያደረሱ ስሆን በፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ ቢሾፕ ደጉ ከበደ፣ ቢሾፖች፣ ቄሶች፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቄስ ኃይሌማርያም ጨምረው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ምዕመናን ተካፍለዋል።

በተካሄደው በዚሁ አመታዊ ኮንፈረንስ ከዓለም ዙሪያ ሁሉ ለእርሱ የተመረጡት መጥተው በዋራ ሜዳ ላይ የሰማዩን ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስን በሃሌሉያና በእልልታ ደምፅ ከፍ ያደረጉ ሲሆን 5306 አዲስ ነፍሳት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ለኃጥአታቸው ስርየት ተጠምቀው ወደ ቤተክርስቲያኗ መቀላቀላቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዋራ ቤቴል “ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምስራቅና ከምዕራብ የሃገሪቱ ክፍሎችና ከተለያዩ አለም ሀገራት ያለዘር፣ ቋንቋና ነገድ ልዩነት በአንድ ልብና ፍቅር የተሰበሰቡ በደሙ የተዋጁ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ልጆች በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራበት ስም ሁሉ በላይ የሆነውን የታላቁን አምላክ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እየጠሩ በፊቱ ሲሰግዱና ሲዘምሩ፣ በደዌና በአጋንንት የታሰሩ ሲፈቱ፣ ያየንበት፣ ከዚህ ጨለማ ዓለም አንዱን አምላክ ከምያስክድ ክፉ ትምህርት ሰዎች በንስሐ ሲመለሱ የታየበት ሚሊዮኖች በጉጉት የሚጠብቁት ጉባኤ” እንደሆነ ይነገራል።

የአለምአቀፉ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን🙏

WaraBetel2025 #WaraCrusade2025

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲
🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia