
በዎላይታ ልማት ባለቤትነት የሚመራው የዎላይታ ሊቃ ትምህርት ቤት ፍሬ የነበሩ 21 እጩ የህክምና ዶክተሮች በመጪው ቅዳሜ ዕለት ከሐዋሳ ዩንቨርስቲ መመረቃቸውን ተከትሎ በሐዋሳ ሴንተራል ሆቴል የማህበሩ አመራሮችና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት የእንኳን ደስ አላችሁ ፕሮግራም ተካሂዷል።
በዘንድሮው ብቻ በዎላይታ ሊቃ ተማሪ የነበሩ ከሀገር ውስጥና ከውጭ በከፍተኛ ውጤት እየተመረቁ መሆናቸው ይታወቃል።
በሌላ በኩል የዎላይታ ሊቃ ት/ቤት ዘንድሮ (2013 ዓ.ም) ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና ከተፈተኑ 61 ተማሪዎች 7 ተማሪዎች ብቻ ሲቀሩ ሁሉም ከ600 በላይ ያስመዘገቡ ሲሆን የት/ቤቱ የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤትም 657 ዝቅተኛው ደግሞ 587 ሆኖ መመዝገቡም ይታወቃል፡፡
የዎላይታ ልማት ማህበር አባላት፣ ደጋፊዎችና አጋሮች እንኳን ደስ አላችሁ🙏🙏