ስራ የማቆም አድማ ለማድረግ እንደሚገደዱ በጌዴኦ ዞን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ገለፁ።

ይሄንን ዜና እያጠናቀርን ባለንበት አሁን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው ከአምስት በላይ ዶክተሮች በዚህ ምክንያት ስራቸውን ለቀው ከይርጋጨፌ ሆስፒታል መውጣታቸው ተረጋግጧል።
በጌዴኦ ዞን ቡሌ፣ ይርጋጨፈ እና ገደብ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚገኙ ከ628 በላይ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ እንደሚገደዱ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ አስታውቋል።
በመንግስት በኩል የተደረገው የደመወዝ ማሻሻያ በጌዴኦ ዞን በስሩ በሚገኙ ሆስፒታሎች ባለመክፈሉ ተስፋ ማስቆረጣቸው
ገልፀው፦ ሠራተኞች አሁን በሚከፈላቸው ደመወዝ ኑሮአቸውን በአግባቡ እንዲመሩ አለማስቻሉ ገልጿል።
ከደመወዝ በተጨማሪ የተለያዩ ለጤና ባለሙያዎ የሚከፈሉ ጥቅማጥቅሞች ለበርካታ ጊዜ ሲጠይቁ በጎ ምላሽ ከዞኑ አስተዳዳሪ ዶክተር ዝናቡ ወልደ ከመስጠት ይልቅ ወዳልተፈለገ እየተወሰደ መቆየቱን ነው የጠቆሙት።
ከጥትምት 1/2017 ዓ.ም ድምሮ እንደሚከፈል የምገልጽ ደብዳቤ ለሁሉም የሆስፒታሉ ሰራተኞች እንደደርስላቸው የሚገልጹ ቅሬታ አቅራቢዎች ከደብቤ በዘለለ ምንም አይነት ጭማሪ እና ዉዝፍ ክፍያ ያለማግኘታቸውን በመጠቆም “የመብት ጥያቂያችንን ምላሽ ፍለጋ በቅርበት የሚመለከተዉ አካላት በመጠየት ከወረዳው እስከ ዞን እስተዳደር ቢመላለሱም በጎ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ለእስር መጋለጣቸውን ነው የተናገሩት።
ለመጨረሻ ጊዜ መጋቢት 15/7/2017ዓ.ም በደብዳቤ ጽፈን በተወካዮቻችን ብንጠይቅም ለመጨረሻ ጊዜ ታገሱን በዚህ ወር ይከፈልላቸዋል እየተባለ መቆየታቸው ገልጸው እስካሁን መፍትሄ እንዳልተገኘና ለጉዳይ ትኩረት እንዲሰጥ ለክልሉ አቤቱታ ማቅረባቸውን ጠቅሰው የሞራል ካሳ ጭምር እንደሚያስፈልግ በደብዳቤ ጠይቀዋል።
በሀገሪቱ ከፍተኛ እድገት እንደመጣ መንግስት በተደጋጋሚ ይግለፅ እንጂ በተፈጠረው የዋጋ ግሽበት ምክንያት የመንግስት ሰራተኞች ቤተሰብ ማስተዳደር እንዳልቻለና የደመወዝ ማሻሻያም ትርጉም የሌለው እንደሆነ ነው የጠቆሙትም።
በተለይ በጤና ዘርፍ የዘመናት ጥያቄዎቻችን በፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ እየተሸፈኑ መጥተው አሁን ጭራሽ መኖር የማንችልበት ሁኔታ ላይ የደረስንን ሰራተኞች ላይ የተፈቀደልንን ማሻሻያ የዞኑ መንግስት መከልከል አግባብ እንዳልሆነ ለዎላይታ ታይምስ በስልክ አረጋግጠዋል።
ግባቸዉ ይሳካ ዘንድ ከዎላይታ ታይምስ ሚዲያ ሌሎች ሚዲያዎችም ድምፅ እንዲሆንላቸውም ጠይቀዋል።
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏