Wolaita Times ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በህጋዊነት ለመስራት የሚያስችል ፍቃድ አገኘ
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት የዎላይታ ታይሚስ ሚዲያን በህጋዊነት መዝግቦ የበይነ-መረብ መገናኛ ብዙኃን ውስጥ በማካተት በህጋዊነት ለመስራት የሚያስችል ፍቃድ በዛሬው ዕለት 22/2013 ዓ.ም ሰጥቷል።
WT ይሄንን በህጋዊነት ለመስራት የሚያስችለውን ፍቃድ የወሰደው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በአዲሱ አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት የሚያስፈልጉ ቅድሜ ሁኔታዎችን በማሟላት ነው።
በመሆኑም WT ፍቃድ በወሰደባቸው ማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ( Website ,Facebook ,Telegram ,YouTube) በተደራጀ እና በተቀላጠፈ መንገድ ወቅታዊ፣ ሚዛናዊ እንዲሁም ፈጣን መረጃዎችን ለአከባቢው ህብረተሰብ እና ለተቀረው ሁሉ በኃላፊነት መንፈስ ለመስራት የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቀው በቅርቡ ወደ መደበኛ ስራ እንደሚገባ ስገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።
ለገፁ ወዳጆች እና WT በሀገሪቱ ሚዲያ ዘርፍ አማራጭ የመረጃ ምንጭ እንዲሆን በሀሳብና በተለያዩ መንገድ በቅርበት ምክርና ድጋፍ ስታደርጉ ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋና አቀርባለሁ።
የWolaita Times Media and Advertising Service መስራችና ባለቤት ጋዜጠኛ ናትናኤል ጌቾ ቤታሎ
Wolaita Times, 22/10/13 E.C ,Sodo, Ethiopia🇪🇹