በእርግጥ ላለፉት ሰባት አመታት ሀገራችን ከተመሰረች ጀምሮ ያልታየና በአይነቱ ለየት ያለ የፖለቲካ ሂደት እንዲሁም የፖለቲካ ልህቃን የእርስበርስ መነታረክ በአደባባይ የታየበት ነው። ለዘመናት የሀገር ፍቅር “ውሃ ልክ ናቸው” ተብሎ በታሪክ የሰማነውን የአንዳንዶቹን ጉድ በአደባባይ ለመታዘብ ዕድል ያገኘንበትም እንደሆነ በርካቶች ይስማሙበታል።

ይሄው ፖለቲካውን ከአውዱ ውጪ በባህላዊው መንገድ፣ ፖለቲካውን ከእውቀት፣ ከእውነት፣ ከልምድና ከሀቅ ባሻገር በብሄር ኮታነትና ደጋፊነት ብቻ በመቃኘቱ ምክንያት ለትውልድ የሚሻገር ኪሳራ አድርሰው አልፏል። አሁንም ያ መንገድ በጊዜ መስተካከል ካልተቻለ ከበፊቱ የከፋ ነገር ይዞ እየመጣ እንደሆነ ለመናገር ጠንቋይ መሆን አያስፈልግም።
አሁንም በሀገራችን በሁሉም አቅጣጫ የምንገኝ ልህቃን በሙሉ ከጥላቻ፣ ከመናናቅ፣ ከእልህ፣ ከጠልፎ መጣል እንዲሁም ከእኔ ብሄር ውጪ ከሆነ አይዋጥልኝም ባይነት መንፈስ በመውጣት ትግልን በሀቅና በእውነት ላይ ብቻ በማድረግ ለዘመናት ሁዋላቀር ፖለቲካ አካሄድ ምክንያት ስቃይ ውስጥ ያለውን ህዝብና ሀገራችንን መታደግ አለብን!!
መንግሥትም በሆደ-ሰፊነት ነገሮቹን ካለፉት ጥፋት መንገዶች በመማር ዛሬ በወሳኝ ቦታ ላይ እንዲሰሩ የሾማቸው እንደእኔ አቶ ጌታቸው ረዳ አይነት አቅም ያላቸውን ወደፊት በማውጣት በየቦታው የታጠቁ ሀይሎችን፣ የተለያዩ የፖለቲካ አቋም ልዩነት ያላቸውን፣ የተሰደዱትን፣ የሚዲያ ተቋማትን እንዲሁም በእስርቤቶች የሚገኙትንም ጭምር የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ሳይሰለች በተደጋጋሚ በቁርጠኝነት በማዳመጥ መፍትሔ በማበጀት ሀገራችን አንገት ከደፋችበት ወደ ሰላሟና ልማቷ የምትመለስበት መንገድ መጥረግ አለበት፥ ጊዜውም አሁንም አልረፈደም!!
የሀገራችን ዘላቂነት ያለው ሰላምና ልማት እንዲሁም ሁሉም ያለልዩነት በመቻቻል የሚደመጥበት ጊዜ የሚረጋገጥበት ወቅት ሁልጊዜ ይናፍቀናል❤🙏
👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏