1000051974

ህዝብ ይጠይቃል!

በፌደራል መንግስት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እንዲገነባ የቦታ መረጣ ተጠይቆ የነበረው የእንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ጉዳይ የት ደረሰ?

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተለይም የዎላይታ ህዝብ ማህበራዊ፣ ፓለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ከየትኛውም ሀገራቱ ክፍል የተለየ መልክ ያለው ነው። በዎላይታ ሌሎች ስራአጥ ወጣቶችን ሳንቆጥር ከመንግሥት ዩንቨርስቲ ከዲግሪ የተመረቁ ከ200 ሺህ በላይ የተማሩ ስራአጥ ወጣቶች ስለመኖራቸው በቅርቡ በተደረገው ዳሰሳ ጥናት ተረጋግጧል።

በሀገሪቱ በተደረጉና እየተደረጉ ባለው ጦርነት ከየትኛውም ብሄር በበለጠ ከፊት ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው መስዋዕትነት እየከፈሉ የሚገኙት ከዎላይታ ስለመሆናቸው መከላከያ ሚኒስትር ስለቁጥራቸውና መስዋዕትነታው ምስክር ነው። በሀገሪቱ ከተሞች በየጎዳናው በአባታቸው በእናታቸው አቅፍ ሆነው ማደግና መማር የሚገባቸው ህፃናት፣ ወጣቶችና ሴቶች በአከባቢው ምንም የስራ ዕድል ባለመፈጠሩ በስደት እንዲሁም በተስፋ መቁረጥ ላይ ናቸው። ይሄ ሁሉ የህዝብ ችግር በአደባባይ እየታወቀ በመንግሥት የተሰጠ መፍትሔ ሀሳብ አይታይም።

ለመሆኑ ትናንት ከአንድ ሰው ዕድሜ በፊት ከራሱ የተደራጀ ሀገር የነበረው በኢትዮጵያ ስር ከሌሎች ጋር በእኩልነትና በፍትሀዊነት የሚገባውን ተከልክሎ የሚገባኝ ይሰጠኝ እያለ ለመንግስት በየደረጃው እየጮኸ የሚገኘው መደመጥ የለበትም ወይ❓የዚህን ህዝብ በደልና ከክብሩ ዝቅ ብለው እየኖረ ያለበት ሁኔታ ከሌላው ልዩ ያደርገዋል። የህዝብ ትግሉና የሁልጊዜ ሙግት መነሻም ለሌላው ካለው ጥላቻ የመነጨ ሳይሆን በሀገሪቱ ህግ ጥላ ስር የሚገባውን ክብርና ጥቅም ለማስጠበቅ እንደሆነ መሰመር አለበት።

ለመሆኑ ከአመት በፊት በፌደራል መንግስት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እንዲገነባ የቦታ መረጣ ተጠይቆ የነበረው የእንዱስትሪ ፓርክ ግንባታ ጉዳይ የት ደረሰ?

እስካሁን ባለን መረጃ የፌደራል መንግስት በክልሉ እንዱስትሪ ፓርክ ለመገንባት ክልሉን የጠየቀው በክልሉ ካብኔ አለመቅረቡን አረጋግጠናል።

👉🤝 እውነት፣ ሀቅ፣ ፍትህ፣ ግልፅነት፣ ሰብዓዊነት፣ ቅንነትና ሚዛናዊነት የሚንፀባረቅበት መረጃዎች🙌
👉🤝 ዘውትር በህብረተሰቡ ውስጥ ነን🙏
👉🤝 ስለዘውትር አብሮነታችሁና ድጋፍ እናመሰግናለን🤲🤜👁👀 #WolaitaTimes ሚዲያ👏

Ethiopia #southethiopia #Wolaita